ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ከክልሉ መስተዳድር ምክርቤት እውቅና ውጪ የተወሰኑ ጉዳዮችን ህጋዊ ለማስመለስ ሀሰተኛ ሰነድ የማዘጋጀት ሙከራ እየተደረገ ስለመሆኑ ተነገረ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በርዕሰ መስተዳድሩ ትዕዛዝ ብቻ ከህጋዊ አሰራርና ደንብ ባፈነገጠ መንገድ በርካታ ውሳኔዎች ተላልፈው በቢሊዮን የሚቆጠር የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ አለአግባብ መፈፀሙን ተከትሎ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቡድን እንቅስቃሴ በመጀመራቸው ተደናግጠው በክልሉ ህጋዊ በማስመሰል ህገወጥ ሰነዶች እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ መሰጠቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ከክልል ካብኔ ምክርቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረሰው መረጃ ከክልል ምስረታ ጀምሮ በክልሉ ከተወሰኑ ውሳኔዎች ከ90 በመቶ የሚሆኑ በፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ ብቻ መሆኑን ተጠቅሰው አሁን ደግሞ እነኚያን ከአሰራር ውጪ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ህጋዊ ለማስመለስ ወደኋላ አስፈርሞ ለማደራጀት መሞከር ሌላ ጥፋት እንደሆነ ጠቅሷል።
አካሄዱ ርዕሰ መስተዳድሩ ለራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት የመስተዳድር ምክርቤት ንቀው በማንአለብኝነት የፈፀሙትን ህገወጥ አሰራር ህጋዊ የማድረግ እንቅስቃሴ በመሆኑ በፍጹም በዚሁ መሳተፍ አንችልም ብለዋል።
ባለፈው ጊዜ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በምርመራ ዘገባው “ክልሉ ከህዝብ ፍትሃዊና ዕኩል ተጠቃሚነት አንፃር ምሁራንና የአከባቢው ነዋሪዎች ምን ይላሉ?” በሚለው አንድ የክልሉን ፓለቲካ በቅርበት የሚከታተል ምሁር “ፍትሀዊ እና ተመጣጣኝ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ዉክልና ባለማግኘቱ አንኳር በሆኑ ኢኮኖሚያዊ ሆነ ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማስገኘት እንዲሁም የልማት ፍትሃዊነት ለማስጠበቅ ግልፅ እና አሳታፊ የህግ ሥርዓት ተዘርግቶ እንድመራ መግባባት ተፈጥሮ መስራት ሲገባ በአሁኑ ወቅት ከዚያ እውነታ በተቃራኒው ተጨባጭ እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁሟል።
ህገመንግስት ያጎናፀፈውን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ ህጎች በህገ-መንግስት ጭምር እንዲካተት በማድረግ አዋጆች፤ ደንቦች እና መመሪያዎች ተዘጋጅተዉ እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔ ብቻ የክልል ካብኔ ምክርቤት ሳያውቅ ወደ ተግባር መገባቱን በመግለፅ ለአብነት በክልሉ በብሄረሰቦች ም/ቤት አማካይነት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የበጀት ቀመር የማዘጋጀት፤ በሰራተኞች ምደባ እና ዝዉዉር ለሁሉም ዞኖች እኩል በማድረግ በአከባቢው ኢፍትሐዊነት ሰፍኖ አደገኛ የመልካም አስተዳደርና የፓለቲካ አለመረጋጋት ምንጭ እየሆነ ስለመሆኑ ምሁሩ ስጋቱን ገልፀው ነበር።
አመራሩ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ሁሉንም ህዝቦች በቅንነትና በታማንኝነት በህጋዊነት የሚገባቸውን እንዲያገኙ በማድረግ ማገልገል የነበረባቸዉ አንዳንድ ተቋማት በተቃራኒው ናቸውና ህዝቡ በፖለቲካ ሥልጣን ድልድልና በሀብት ክፍፍልም በተለይም የክልሉ ምክር ቤት በሚያውጃቸው ሀብቶች አስተዳደር ላይም ኢፍትሐዊ አሰራር ተሰርቶ ለመልካም አስተዳደር ችግር ምንጭ እንዳይሆን ከወዲሁ ጥንቃቄና ክትትል ሊደረግ እንደሚገባም ምሁሩ በማጠቃለያ ሀሳቡ ጥሪ ማቅረቡን መዘገባችን አይዘነጋም።
ሰሞኑን በክልሉ ከህግ አሰራር ውጪ የተላለፉ በርካታ ውሳኔዎች የፌዴራል ምርመራ ቡድን ወደ አከባቢው እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ መሰማቱን ተከትሎ በርዕሰ መስተዳድሩ ትዕዛዝ ብቻ ከህጋዊ አሰራርና ደንብ ባፈነገጠ መንገድ በርካታ ውሳኔዎች ተላልፈው በቢሊዮን የሚቆጠር የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ አለአግባብ መዘረፉን ተከትሎ ህጋዊ በማስመሰል ህገወጥ ሰነዶች እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ መሰጠቱ በክልሉ ካቢኔዎች መካከል አለመግባባት መፍጠሩም ተገልጿል።
ሌላዉ ህገ-ወጥነትን ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት እንዲጠብቅና እንዲከላከል ሀላፊነትና ስልጣን የተሰጠዉ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች ራሳቸዉ ኮንተርቫንድስቶች ከመሆናቸዉ ባሻገር የሙስና እና ሙሰኞች ቅንጅት በመፍራት የሙስና ጥቆማና አቤቱታም ጭምር ያለዉን ይዞ ከመከላከል ይልቅ ሙሰኞችን “በእናንተ ላይ ጥቆማ እየመጣ ስለሆነ በጥንቃቄ ሥራችሁን ሥሩ” ብሎ መንገድ ለሙሰኞች በመስጠት መደላደልን መፍጠር በክልሉ የሙስኛ ተግባርና አድራጊዎች በቀላሉ ጠቋሚዎችን በመጉዳት ተፈርቶ እንዲኖሩ የሚያደርግ አደገኛ ሁኔታ መኖሩን ለማሳያነት እየጠቆምን በክልሉ የኮንትሮባንድ፣ የድንጋይ ከሰል እና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሚመለከታቸዉ አካላት የተጀመረዉ የምርመራ ሥራ ተጠናክሮ እንድቀጥል እና ለዛ አጋዥ መረጃዎች የማጋለጥ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏