1000046224

ሰበርመረጃ

ሙሹራና ሙሽሪትን በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ግለሰቦች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያደረሰው መንግስት አመራር ነፃ መለቀቁ በፍትህ ሂደት ላይ ጥያቄ ማስነሳቱ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ይርጋጨፈ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሚጁ ያለመንጃ ፈቃድ የመንግስት መኪና እያሽከረከረ ለሶስት ሰው ሞት፣ ለ8 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንዲሁም ከ20 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከወረዳው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃው ከሆነ “ዛሬ ሀገርምድር ሠላም ብለው ቤተ ዘመድ ተጠራርተው ሠርግ ላይ ሙሹራና ሙሽሪት በመጠባበቅ ላይ እያሉ ዝናብ በመዝነቡ ዱንኳን ውስጥ ተጠልሎ በነበሩ ሰዎች ላይ ልምምድ ብሎ ዋና ሾፌሩን በአጠገቡ አስቀምጦ እየተለማመደ የነበረው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ድንኳን ጥሶ በመግባት በሰው፣ በንብረት ከፍተኛና ከባድ አደጋ በማድረስ ሠርጉን ወደ ለቅሶ፣ ደስታን ወደ ሀዘንና በመቀየር ትልቅ አደጋ አድርሰዋል” ሲል አንድ የሟች ቤተሰብ አስረድተዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከሳምንት በፊት የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሚጁ በትናንትናው ዕለት ፍርድቤት ቀርበው የጥፋተኝነት ወሳኔ መተላለፉንና ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን የገለፀ ቢሆንም እንዲቀጣ መነሻ ቅጣት በመስጠት የመጨረሻ ዉሳኔ ለመስጠት የቅጣት ማክበጃ ዐቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረው የተስፋዬ ሚጁ የክስ ፋይል ከፅኑ እስራት ወደ “ነፃ ይለቀቅ” ውሳኔ መሰጠቱ መነጋገሪያ ሆኗል።

ዋና አስተዳዳሪው እና ሾፌሩ የስልጣን ትውውቅና ጥቅም ትስስር ተጠቅሞ የሟቾች ቤተሰብ ፍትህ እንዳያገኙ፣ የተጎዱት ተገቢ ካሳ እንዳያገኙ በፍርድቤት ላይ ጫና በመፍጠር በነፃ መለቀቃቸው ተናግሯል።

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ለማቅለያው ከከፍተኛ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ጫና ቤተሰቦቹ አንቃወምም ቢለው እንዲፈርሙ በማድረግ ይህንን ሂደት እንደማቅልያ መወሰዱን” ከጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዳዩ ቅርበት ያለው አካል መረጃ ለዎላይታ ታይምስ ያደረሰው።

እንደ ባለሙያው አስተያየት ከሆነ “1ኛ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 543 (3) የእስራት ቅጣት ከ5-15 ዓመት ጽኑ እስራትና ከ10-15 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጫ የምል፣
2ኛ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 559 (2) እና (3) የወንጀል ክስ ለጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተደራራቢ የወንጀል ድርጊት በመሆኑ ተደራራቢ ክስ ቀርቦበት የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩ በህግ አግባብ በማየት ከጉዳዩ ገለልተኛ በመሆን መወሰን ሲገባው ይህንን ወደ ጎን በመተው ኃላፊነት በጎደለው ስሜት ከህግ አግባቢ ውጪ ከአንድ የህግ ባለሙያና ዳኛ የማይጠበቅ ውሳኔ መስጠት ማለት በህግ የበላይነት አለማመን ብቻ ሳይሆን የህግ ጉዳይን በህግ ብቻ በማየትና በመዳኘት ከመወሰን አልፈው በፖለቲካ ጫና የፖለቲካ ሰዎችን በመፍራት የእነርሱ ተላላኪ በመሆን የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑ የጌዴኦ ህዝብ መንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ የተወሰነ ውሳኔ ነው” ብለዋል።

“የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ጠንካራ የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍንና የሞቱት የቆስሉት ህክምና ላይ የሚገኙትን ፍትህ ሳይዛባ ትክክለኛ ፍርድ እንደ ማንኛውም አካል እንደሚሰጥ እየተጠባበቀ ባለቤት የዞኑ አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልደና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ለአቶ ሳሙኤል በፍቃዱ ቀጭን ትዕዛዝ በመስጠት ፍትህ እንዲዛባ አድርጓል” በሚል ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የክሱን ህዴት በመከታተል ፍትህን በዞኑ ለማስከበር መንግስት ካስቀመጣቸው ተቋማት አንዱ በሆነው አቃቤ ህግ ውስጥ የተቋሙ ባልደረባ የሆኑት ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ህዴቱን በዚህ መልክ ለህዝብ እንዲቀርብ አጋርተውናል።

በቀድሞው የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ ተከሳሽ ተስፋዬ ሚጁ ላይ ከጌዴኦ ዞን አቃቤ- ህግ የቀረበው የወንጀል ክስ ጉዳይ አመጣጥ፣ በቀን 12/04/2017 ዓ/ም የአሁኑ ተከሳሽ የነበረው አቶ ተስፋዬ ሚጁ የጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ ይላል።

ግለሰቡ/ ተከሳሹ ምንም ዓይነት ልምድና የመኪና መንጃ ፈቃድ ሳይኖረው ከይርጋጨፌ ወረዳ ከተማ ወደሀሪ ቀበሌ በገጠር መንገድ የወረዳ መኪና ይዘው በመውጣት በአጋጣሚ በሠርግ ምክንያት መንገድ ላይ ያለውን ድንኳን መኪናው መቆጣጠር አቅቶት ድንኳኑን ጥሶ በመግባት አንድ የስምንት ወር ነፍሴ ጡርና አንድ ሴት በድምሩ የሶስት ሰው ነፍስ ከማጥፋት አልፎ በአስራ አምስት ግለሰቦች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሶ በህግ እንዳይጠየቅ የጌዴኦ ዞን አስተባባሪ አካላት ሽፋን ከማድረግም አልፈው በግልፅ የወንጀል ክስ እንዳይቀርብ፣ መዝገቡ እንዲዘጋና ከእስር እንዲለቀቅ በህግ አካላት ላይ ያልተገባ ጫናና ትዕዛዝ እየሰጡ ከቆዩ በኋላ የጌዴኦ ዞን አቃቤ ህግ እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረጉን አስታውሷል።

ግለሰቡ/ተከሳሹ ጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበው በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 128 መሰረት ማንነቱ ተረጋግጦ በራሱ ነፃ ፍቃድ የእምነት ክህደት ቃል ሲሰጥ” በተጠቀሰው አንቀጽ ላይ ምንም ተቃውሞ የለኝም። የወንጀል ድርጊት ፈጽሜያለሁ፣ ጥፋተኛ ነኝ፣ በእጄ በመኪና አደጋ የሰው ህይወት አልፏል፣ ብዙ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም አሉ” በማለት አምኖ ፍ/ቤቱም የአቃበ-ህግንና የተከሳሹን የግራና ቀኝ ክርክር ሰምቶ መነሻ ቅጣት ስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና የአስራ ሶስት (13) ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ ከወሰነ በኋላ ከሁለቱም ወገን የቅጣት አስተያየት እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዞ ዓቃቤ-ህግ ያቀረበውን የጥፋት ማክበጃ ሃሳብ ፍ/ቤቱ ሳይቀበል አልፎ የተከሳሹ ሰባት (7) የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን ተቀብለዋል።

በቀን 05/07/2017 ዓ/ም ላይ ከስምንት(8) ዓመት ጽኑ እስራትና አስራ ሶስት (13) ሺህ ብር ገንዘብ ቅጣትን ወደ ሶስት (3) ዓመት ከሳባት ወርና ሁለት (2) ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አድርገው ሥነ- ሥርዓት ህጉም ሆነ የቅጣት አወሳሰን መምሪያ 2/2006 በማይፈቅድ ሁኔታ ፍ/ቤቱ ቅጣቱን ወደ ገደብ ያመጣበት አግባብ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበትና የውሳኔ ሥርዓት የጎደለበት በመሆኑ ህግ መጣሱን ጠቅሰዋል።

ለዚህም ውሳኔ መነሻ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴና የጌ/ዞ/ብ/ፓ/ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ በጣምራ ፍርማ ለተከሳሽ ተስፋዬ ሚጁ በሚስጥር ቀድሞ እንደተሰጠ በማድረግ ተከሳሹን ከወንጀል ነፃ እንዲሆን ሰርትፍኬት አዘጋጅተው “ግለሰቡ/ተከሳሹ አሁን ላይ ካሉት የዞን አመራርም ይሁን ከወረዳ አመራር የተሻለ፣ መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ከዞን አልፎ ለሌላ ሀላፊነት የሚጠበቅ፣ ህዝብ የሚወደውና አሁን ለሥራ የሚፈለግ ነው” በማለት ሠርትፍኬት አዘጋጅተው የሰጡ ሲሆን የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንን ፎርጅድ ሠርትፍኬት እንደ ቅጣት ማቅለያ ለመውሰድ የተሰጠ ውሳኔና አሁን ላይ ሠርትፍኬት የሰጠው አካልም መረጃ እንዳይወጣ ለፍ/ቤት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ላይ ያሉ በመሆናቸው በጉዳዩ ላይ ሥልጣን ያለው የክልልና የፌዴራል የህግ አካላት በህግ አካላት በህግ አግባብ ግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እንዲጣራባቸው የጌዴኦ ህዝብ ይፈልጋል ከምል እምነት ይህንን ጥቆማ ለመስጠት መገደዳችንን እንገልፃለን” ብለዋል።

“የብዙ እናቶች፣ አባቶች፣ ለቅሶና ጩሄት በይርጋጨፌ ወረዳንና አካባቢ በፍትህ መዛባት አሁን በሀዘን ውስጥ ከቷቸዋል፥ አሁንም የሚመለከታቸው አካላት፦ ዋና አስተዳዳሪው የመንግሥትን ስልጣን ተገን በማድረግ ያለመንጃ ፈቃድ የመንግስት መኪና እያሽከረከረ ለ3 ሰዎች ሞት፣ ለ8 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንዲሁም ከ20 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኝና ዳግም ፍትህ እንዲረጋገጥ ክትትል እንዲያደርጉ” በሚል ቤተሰቦቹ ተማፅነዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Gedio