በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ውዝፍ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ “አንከፍልም” በሚል የፍርድቤት ትዕዛዝ ያላከበሩ አመራሮች እርምጃ እንዲወሰድባቸው ፍርድቤቱ አዘዘ

“የፍርድቤት ትዕዛዝ የማይፈፅም ክንዶ ዲዳዮ ወረዳ አስተዳደር” በተመለከተ የሃላሌ መጀመራያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክንዶ ዲዳዮ ወረዳ የሃላሌ መጀመራያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች የሰሩት የትርፍ ስዓት ክፍያ ወረዳው መፈፀም ባለመቻሉ ሰራተኞች ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም በዎላይታ ዞን ፐብሊክ አስተዳደር ፍርድ ቤት በኩል ክስ የመስርቱ ሲሆን ፍርድቤቱም ግራ ቀኝ በመመልከት የሰራተኞች አቤቱታ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጦ የክንዶ ዲዳዮ ወረዳ ሰራተኞች የ23 ወራት ለህብረተሰቡ አግልግሎት የሰጡበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲከፍል ጥቅም ወር 2016 ዓ/ም ብይን ሰጥቶበታል።
እንደ መረጃው ከሆነ የብይን ውሳኔ እንዲያስፈፅምም ለክንዶ ድዳዬ ወረዳ ፍርድ ቤት የዎላይታ ዞን ፐብሊክ አስተዳደር ፍርድ ቤት አስተላልፏል።
ይሁን እንጅ ክንዶ ዲዳዮ ወረዳ የፍርድቤት ትዕዛዙን ከመፈፀም ይልቅ ከወረዳው አመራሮች ጋር በመመሳጠር እና የጥቅም ተጋሪ በመሆን የሰራተኞች መብት አላስፈፀመም፣ የወረዳውም መንግስትም “በማንአለብኝነት መብታችን ነፍጓል” በማለት ሰራተኞች ቅሬታ አቅርቧል።
ጉዳዩ የሚመለከተው የዎላይታ ዞን አስተዳደር ቅሬታውን በማጤን እልባት እንድሰጥ እንዲሁም የፍርድቤት ትዕዛዝ ያለከበሩ የክንዶ ዲዳዮ ወረዳ አመራር አካል ተለይቶ አስተዳዳራዊ እርምጃ እንድወስድ የዎላይታ ኢንተርሰፕሽን በሰራተኞች ስም ይጠይቃል።
ሰራተኞቹ “የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያልፈፀሙ የወረዳው ዳኞች ላይ የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ምርመራ በማድረግ እርምጃ እንድወስድም እንጠይቃለን ብለዋል። የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለማክበር ትልቅ ወንጀልም ነው። ለዎላይታ እድገትም ፀር ነው። በፍርድ ቤቱ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሽር አድርገዋል። በፍርድ ቤቶች የህዝብ እምነት እንዲሸረሽር ያደርጋል” በሚል አሰረድተዋል።
ሰራተኞቹ “ለህብረተሰቡ አግልግሎት የሰጡበትን የትርፍ ስራ ሰዓት ክፍያ የወረደው መንግሥት መክፈል ባለመፈለጉ አጠቃላይ ባለሙያዎች ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም በዞን ፐብሊክ ሀብት አስተዳደር ፍርድ ቤት ክስ መስርተው በቀን 12/02/2016 ዓ.ም የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቷቸው ለአፈፃፀም የኪንዶ ዲዳዬ ፍርድ ቤት ክፍያውን እንዲያስፈፅም ቢላክም የወረዳው ፍርድ ቤት እነዚህ ባለሙያዎች የሠሩበትንና ህግ የወሰነላቸውን ቢጠይቁም ፍርድ ቤት ከወረዳ ፖለቲካ ሰዎች ቀጥታ ትእዛዝ እየተቀበለ ባለሙያዎችንና የህግ ጠበቃ ለሁለት አመት ከስምንት ወር በማጉላላት ፍትህን በማዛባት የአከባቢው ህዝብ በፍርድ ቤቱ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሽር አድርገዋል” በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱ ቀጥታ ግኙነት ከወረዳ መንግሥት ጋር ፈጥሮ ለባለጉዳዮቹ በየቀጠሮቹ ቀናት የተለያዩ ዳኞች ጉዳዩን እንዲይዙ በማድረግ “ጉዳዩ ለኔ አዲስ ስለሆነ እንደ አድስ እንዲታይ” የሚል ምላሽ በመስጠት በማጉላላት ላይ መሆኑን ጠቅሷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏