1000049612

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ

አለም አቀፍ ሞዴል እና ዲዛይነር ዶክተር ሰናይት ማሪዮ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ የፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ ተቋም በመክፈት በይፋ አስጀመረች

አለም አቀፍ ሞዴል እና ዲዛይነር ሰናይት ማሪዮ ነዋሪነቷን ጣልያን ሀገር ያደረገች ሲሆን ባለፈው አመት በአዲስ አበባ ግዙፉን የፋሽን እና ቴክኖሎጂ ተቋም ለመክፈት ለአንድ አመት በማደራጀት ቆይታ አሁን በይፋ ማስጀመሯ ተነግሯል።

ይሄው ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተሰኘው ተቋም በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋሽን፣ በስነ ዉበት (ሜካፕ)፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ሴኩሪቲ እና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ለማስተማር አልፎም ስራ አጥነትን ለመቅረፍ አስተምሮ የስራ ዕድልን በማመቻቸት የበኩሉን ለመወጣት ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ዛሬ በተቋሙ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

በዳማሪዮስ ተግባር ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ የተቋሙ መስራች ዶ/ር ሰናይት ማሪዮ የገለፀች ሲሆን በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጭ የስራ ዕድልን ለሰልጣኞቹ ይመቻቻል ተብሏል።

ከመስከረም ጀምሮ ከLevel 2 ጀምሮ ዓለም አቀፍ በሆኑ ባለሙያዎች ስልጠናዎች እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን ሰልጣኞች ስለጠናዉን ካጠናቀቁ በኋላ በተቋሙ ዓቅም መሰረት ከንብ ባንክ ጋር በመተባበር የፋይናንስ አገልግሎቶች ይመቻቻል ተብሏል።

በዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጭ ከጣሊያን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አሜሪካ የመጡ መምህራኖች ስልጠናዎችን ይሰጣሉ። በሜካፕ ትምህርት ከፍል ከMario ሜካፕ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ዉል መፈፀማቸውን ገልፀው ከቆዳ ስፔሽሊስት ዶከተሮች ጋር በጥምረት አብሮ ለመስራት ዉል መፈፀሙ ነው የተገለጸው።

አሁን ለ20 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን፣ ከRome Business School ጋር ለተማሪዎች የስኮላርሺፕ ስምምነት ተደርጓል። ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቦሌ ብራስ የሚገኝ ሲሆን በ1200 ካሬ ሜትር ላይ አርፏል፣ 24 ከፍሎች ሲኖሩት፣ ዘጠኝ የመማርያ ከፍሎች፣ አንድ ቤተ መጽሐፍት ያካተት ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

አቅም ለሌላቸው ሰልጣኞች ዳማሪዮስ ከዳሽን ባንክ ዱቤ አለ ፕሮግራም የብድር አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ተፈፅሟል። ዳማሪዮስ በቀጣይ አምስት አመታት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ እንደሚሰራ ነው የሚሰራ ሲሆን በ1300 ካሬ ላይ ያረፈው ተቋሙ ለማደረጀት አንድ አመት የፈጀ ሲሆን በርካታ ሚሊዮን ብሮች ወጪ የሆነበት በአይነቱ ለየት ያለ ተቋም ነው ተብሎለታል።

ዳማሪዮስ የሚያስተምራቸው ተማሪዎች የስራ እድል በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የስራ እድል የሚመቻችላቸው ሲሆን በፋሽን ዲዛይን፣ በአይቲ እና በሜካፕ ትምህርት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ከስድስት አመት በፊት የዚሁ ተቋም መስራች የሆነችውና አለም አቀፍ ሞዴል እና ዲዛይነር ሰናይት ማሪዮ ከአለም አቀፉ Stay Up Aviation Institutes of Technology የኢትዮጵያ ባህል በዓለም እንዲታወቅ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራች በመሆኑ የክብር ዶክትሬት ማበርከቱ ይታወቃል።

በተጨማሪም Dr ሰናይት ማሪዮ በኢትዮጵያ እና በአለምአቀፍ ፍሽን እንዱስትሪ ደረጃ ባህልን በዘመናዊ ፋሽን እንዱስትሪ እንዲታወቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያተኮሩ ሥራዎችን ለመስራት በመቻሏ በተደጋጋሚ የተለያዩ አለምአቀፋዊ እና ሀገራዊ ሽልማቶችና እውቅና ያገኘች ጠንካራ ሴት በመሆን ትታወቃለች።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia