
|ሰበርዜና|በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ
የቀድሞ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ላይ ከ6 ዓመት በላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተፈረደበት
የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ የነበረው አቶ ተመስገን አለማየሁ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 6 ዓመት ከ 5 ወር እስር እንዲሁም የ75 ሺህ ብር ቅጣት እንደተፈረደበት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ለበርካታ ወራት ከዎላይታ ሶዶ ማረሚያ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የቀድሞ ከንቲባ አቶ ተመስገን በቀረበባቸው 7 የተለያዩ የሙስና፣ ስልጣን አለአግባብ በመጠቀም እንዲሁም ተያያዥ ክሶች ቀርበውበት በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤቱፈት ውሳኔ ማግኘቱን ምንጮቻችን አስረድቷል።
እኚሁ የቀድሞ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ ስታሰሩ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ የነበሩ ሲሆን ከዚያ በፊት የዎላይታ ዞን ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ፣ የወረዳ አስተዳዳሪ እንዲሁም ሌሎች ኃላፊነት ላይ ስለመስራታቸው ከግል ማህደራቸው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ እናቀርባለን።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏