የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አፍሪካ ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሀገር ውስጥ አቅም እንድትገነባ ጥሪ አቀረቡ

በኡጋንዳ ካምፓላ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ የኢፌዴሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የAGRA ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመልዕክታቸው የአለምአቀፉ የፋይናንስ ግቦች እንዳልተሟሉ በመጠቆም አፍሪካ የ2030 ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የራሷን አቅም እንድትገነባ አሳስበዋል።
በካምፓላ የስፔክ ሬዞርት ኮንቬንሽን ሴንተር ላይ የተለያዩ ሀገር መሪዎች በተገኙበት ባስተላለፉት መልዕክት “የእድገት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ አፍሪካ ከ2030 ዘላቂ የልማት ግብ ልዩነት እየጨመረ ነው፣ የበኩላችን፣ በምን እንደሆነ መረዳት ያስፈልገናል” ብለዋል።


የአፍሪካ ሀገራት ዘላቂ ልማትን ለማሳካት የሀገር ውስጥ አቅማቸውን ለማጎለበት “በራሳችን አቅም ላይ ማተኮር አለብን” ይህም የትብብር፣ የአገር አቀፍ ፈጠራ እና የስራ እድል አማራጮችን እንደሚከፍት አቶ ኃይለማርያም አክለው ጠቁመዋል።

እስከ ነገ የሚቆየው ይህ መድረክ አፍሪካ በ2025 በአሜሪካ በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲሁም ሌሎች የትላልቅ ዓለማአቀፍ ዝግጅቶች ላይ የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎና የጋራ ዋና አጀንዳዎችን እንዲያጠናክር እንዲሁም ተሰሚነትን ከፍ ለማድረግ ያለመ ቅድመ ዝግጅት ነውም ተብሏል።
11ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ፎረም ጉባኤ (ARFSD-11) የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የዩጋንዳ ሪፐብሊክ መንግስት ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ጋር በመተባበር በጋራ መዘጋጀቱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏