የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ወጣቶችን በኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ ያለመ የትብብር ስምምነት ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር አደረገ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤትና የ Hailemariam & Roman Foundation ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሪቤ አስፋው መፈረማቸው ተገልጿል።
በዚሁ በትናንትናው ዕለት በአዲስአበባ በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የሥራ አመራርና የፕሮግራም ቡድኖች የተገኙ ሲሆን ይህም “ለዘላቂ ልማትና ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ያሳያል” ተብሏል።
የትብብር ስምምነቱ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና HRF ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በሚተገበረው በደቡብ ኢትዮጵያ የወጣቶች የራስ ስራ ፈጠራ ፕሮጀክት (YES) ላይ በጋራ እንደሚሰራ ከ Hailemariam & Roman Foundation ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


በዚሁ ስምምነት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ የፋይናንስ ተደራሽነት በተለይም ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ወጣት ስራ ፈጣሪዎች እንዲበለፅጉና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ቁርጠኞች ነን ብለዋል።
ወይዘሮ ሮማን በገለፃቸው አክለውም ይህ የትብብር ስምምነት ለሶስት ዓመታት የሚቆይ በማስረዳት ግቦቹ መሳካቱን ለማረጋገጥ ደግሞ ቀጣይነት ያለው ግምገማ፣ ክትትል እና የማሻሻያ እድሎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
Ethiopia #southethiopia
