1000054251

ህንጻው በውስጡ ሶስት ዘመናዊ የስብሰባ አደራሾችን ጨምሮ አሳንሰር ጋር ያለው ሲሆን አጠቃላይ ከ6 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ላይ በ1 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ህንጻው እንደሚያርፍም ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ማስጀመሪያ ቦታ የተገኙት የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም ባስተላለፉት መልዕክት ቦታው ከዚህ በፊት ለቢሮ ግንባታ ታስቦ ታጥሮ የቆየ መሆኑን አስታውሰዋል።

ዋና አስተዳዳሪው “ለሠራተኞች ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር እና የዘመን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት እጅግ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀው ተመካክረን፣ ተነጋግረን፣ ተወያይተንና አንድነታችን አጠናክረን ህዝባችንን አስተባብረን ትልቅ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት አቅም አለንም” ብለዋል።

ደረጃውን የጠበቀ G+7 ህንጻ ግንባታ ከ613 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገነባ ሲሆን በሁለት ዓመት ውስጥ ግንባታው ተጠናቅቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ጨረታውን አሸንፎ ግንባታ ስራውን የጀመረው የዎላይታ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ፋንታ ድርጅቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረጉን ገልፀዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita