በደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ ዞን ዛይሴ ቀበሌ በተፈጠረው ጥቃት የክልሉ ፖሊስ ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ዛይሴ ቀበሌ ትላንት በደረሰ ጥቃት የአንድ የክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊስ ህይወት ማለፉን እና አምስት የፖሊስ አባላት ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው WT ሚዲያ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጉዳት የደረሰባቸው የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት በአርባምንጭ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እየተከታተሉ ሲሆን ግጭቱን ተከትሎ በአካባቢው የፀጥታ ችግር መኖሩ ተገልጿል።
አለመረጋጋትን ለመቆጣጠር የክልሉ ልዩ ኃይል ወደ ስፍራው የገባ ሲሆን የፌደራል መከላከያ ሰራዊትም በአካባቢው ተሰማርቷል።
ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለWT ሚዲያ እንደገለፀው የችግሩ መነሻ በአካባቢው የቆየው የዘይሴ ብሄረሰብ የመዋቅር ጥያቄ ጋር ተያያዘው ነው ብሏል።
ነዋሪው አክሎም በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ግጭቶችን መንግስት ሰላማዊ ዜጎች እንዳይጎዱ በዘላቂነት ሊያስቆምና ተጠያቂነት ሊያሰፊን ይገባል ብሏል።
በሌላ በኩል በቦታ የነበረው አንድ የክልሉ ልዩ ፖሊስ እንደነገረን በቀን 3 መጋቢት 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ ከአርባምንጭ ወደ ዛይሴ ግዳጅ እየገቡ በነበሩ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ያልታሰበ ጥቃት ተፈጽሟል፤ በዚህ አሳዛኝ ክስተትም የአንድ የልዩ ኃይል አባል ህይወት ሲያልፍ አምስት ሌሎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።
አክለውም ይህ ጥቃት በሀገራቸው ጀርባ አጥንት ሆነው ለሚያገለግሉት የሰራዊት አባላት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የሚያሳይ ሲሆን ህይወታቸውን ላጡት አባላት ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን እንመኛለን ብሏል።
የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስት እስካሁን በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WT ሚዲያ👏