1000056175

“አሁን ላይ እመን አትመን ተብሎ በምርመራ ወቅት ቶርች የሚደረግ የወንጀል ተጠርጣሪ የለም፣ ይህንንም በአካል ለመገምገም ሞክረን አንድም አላገኘንም” ሲል የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ገለፀ።

አቶ ኢሳ ቦሩ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አሁን ላይ እመን አትመን ተብሎ በምርመራ ወቅት ቶርች የሚደረግ የወንጀል ተጠርጣሪ የለም ብሏል፡፡

ይህንንም በአካል ለመገምገም ሞክረን አንድም አላገኘንም ያሉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም በተወካዮች ም/ቤት በትላንትናው ዕለት በተገመገመበት ወቅት ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢው አያይዘውም ሁለተኛው የፖሊስ ተልዕኮ የወንጀል ምርመራ ስራ ነው፡፡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የፎረንሲክ ምርመራ የተሰራው ሥራ አፈጻጸም በጥንካሬ የሚወሰድ ሲሆን ከዚህ አንፃር ከለውጡ ወዲህ በተቋሙ እየሰራችሁ ያላችሁት ስራ በእውነት ለመናገር ‘’መረጃና ማስረጃ መር የፖሊስ አገልግሎት” የተባለው መርህ የሪፎርሙ አካል ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃዎችን በተለያዩ የተግባቦት ዘዴዎች ለህብረሰቡ እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሽብር ሴራዎችን፤ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀልበስ እና ድርጊታቸውን የሚያጋልጡ ዶክመንተሪዎችን በማዘጋጀት ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረውን ሥራ በጥንካሬ የሚወሰድ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WT ሚዲያ👏

#Ethiopia