ጠያቂ ያጣው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ኢፍትሃዊነት እና የህዝብ ቅሬታ እየተባባሰ ስለመምጣቱ ተገለፀ።
አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ በክልሉ ቢሮዎች፣ ኤጀንሲዎችና ኮሚሽኖች ከበጀታቸው እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች የወር ደመወዝ ቀንሰው ለአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ ገቢ እንዲያደርጉ ቀጭን ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን WT የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ውሳኔ ፍትሃዊነት የጎደለው እና ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም እንደሆነ በርካታ አካላት ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው።
አቶ ጥላሁን ስታዲየሙን ያለምንም ጨረታ በአርባምንጭ ማስጀመራቸው ሲታወስ፣ ከተቋማት በተጨማሪ እያንዳንዱ የክልሉ ሲቪል ሰርቫንትም የወር ደመወዙን በግዴታ እንዲያዋጣ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።
ይህ ትዕዛዝ የአርባምንጭ ማዕከል የሚገኙ አንዳንድ ቢሮዎች በሩጫ እንዲያስፈጽሙት የተገደዱ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ተቋማትና ሰራተኞች ደግሞ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ ገንዘቡን እንዲያስገቡ ታዘዋል።
ይህ አሰራር በሌሎች ብሔር ተወላጅ በሆኑ ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እያነሳ ነው።
የአቶ ጥላሁን ከበደ አመራር በራሳቸው የትውልድ አካባቢ በሆነችው ጋሞ አርባምንጭ ከተማ ላይ ብቻ ለማተኮር መቁረጣቸው በክልሉ ውስጥ ውጥረቶችን እየፈጠረ ነው።
ምንም እንኳ ሶዶ ከተማ የክልሉ አስተዳደር መቀመጫ ብትሆንም፣ አቶ ጥላሁን ዋና ዋና የክልል ስብሰባዎችን እና ኢንቨስትመንት መሳብ የሚችሉ መድረኮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው እያዘዋወሩ ይገኛሉ።
በተጨማሪም፣ በዎላይታ፣ በጌዲኦ፣ በጎፋ እና በሌሎች ብሔሮች ላይ ልማት እንዳይሰራ በማድረግ የራሳቸውን አንድ ብሔር ላይ ብቻ ልማት እየሰሩ ነው የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ከዚህ ቀደምም ርዕሰ መስተዳድሩ ያለ ካቢኔ ውሳኔ ለአርባምንጭ ስታዲየም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ለብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለማክበር ተብሎ ለአርባምንጭ አስፋልት ለመስራት ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ መሰጠቱ ተዘግቧል።
ለክልሉ የሚመጣ ኢንቨስትመንት በሙሉ ወደ አርባምንጭ ብቻ በግድ እንዲሄድ ሲደረግ፣ ባለሀብቶች ወደዚያ መሄድ ካልፈለጉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደማይሰጣቸው ታውቋል።
ይህ ሁሉ ግፍ በክልሉ እየተፈጸመ እያለ ከርዕሰ መስተዳድሩ ውጪ ሁሉም አስተባባሪዎችና የካቢኔ አባላት በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ መምረጣቸው አሳሳቢ ሆኗል።
አሁን ባለው የኑሮ ውድነት ወቅት እየተፈጸመ ያለው ይህ አድራጎት በህዝቡ ላይ ሌላ ጫና እየፈጠረ ሲሆን፣ ዝርዝር መረጃዎች ወደፊት ይቀርባሉ።
#Ethiopia #Southethio