በአዲስአበባ በተለያዩ በታዎች ታስሮ የነበሩ 564 የዎላይታ ድቻ ደጋፊዎች ከእስር ተፈቱ
በሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በዎላይታ ድቻ እና በሲዳማ ቡና መካከል በተደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ወቅት “ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት” በሚል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ 564 የዎላይታ ድቻ ደጋፊዎች ከእስር በዛሬው ዕለት መፈታታቸውን ተነግሯል።



እነዚህ ደጋፊዎች ክለባቸውን ለመደገፍ ከዎላይታ ወደ አዲስ አበባ የመጡ እንደነበር ይታወቃል።
የእስር ውሳኔው የመጣው በጨዋታው ዕለት ከጸጥታ ኃይሎች ጋር “ባልተገባ ግጭት ውስጥ ከተሳተፉ በኋላ ነው” በሚል እንደሆነ ተገልጿል።
የዎላይታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ዝርዝር ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ 564 የሚሆኑት ደጋፊዎች እንዲለቀቁ ማድረግ ተችሏል።
የእስረኞች መፈታት ዜና ለደጋፊዎች እና ለቤተሰቦቻቸው እፎይታን እንደሰጠ ታውቋል።