በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለው የልማት ኢፍትሐዊነትና ግልፀኝነት የጎደለው አካሄድ ክልሉን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚያመራ መሆኑን ምሁራን ተናግረዋል።
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠንክረው ከሰሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የገዥው ፓርቲ ብልጽግና በቀላሉ እንደሚሸነፍ WT ሚዲያ ያነጋገራቸው የዎላይታ ሶዶ፣ የዲላ እንዲሁም የጂንካ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ግምታቸውን አክለው አስቀምጧል።
በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም አካባቢ የህዝብ ኩርፊያ እየገጠመ የሚገኘው ብልጽግና ፓርቲ በአሁኑ ሰዓት የፓርቲ አባላትን ለመያዝ እስትራቴጂ ነድፎ እየተቀሳቄሰ እንደሚገኝና በተለይም ወጣቶችን እና ሴቶችን ለመያዝ አደረጃጀት እያጠናከረ እንደሚገኝኛ በአዲስ እያደራጀ መሆኑን ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።
አሁን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለው የርዕሰ-መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አስተዳዳር ኢፍትሃዊነት፣ ሌብነትና ለራሱ አከባቢ ብቻ ትኩረት በግልጽ ማድረጉ ያንገሸገሻቸው በክንፍ እየተደራጁ ያሉ ወጣቶች በበኩላቸው በሀገራዊ ምርጫ መላው ህዝቡ የራሱን ውሳኔ እንዲወስን የበኩላቸውን ጥረት ሁሉም እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
እየሆነ ያለውን የክልሉን የአስተዳደራዊ በደልና
መንግስት የለም እስኪባል እየተፈጸመ ያለውን ኢፍትሃዊነት የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብተው እንዲያርም ካልተደረገ የሚገጥመው ፈተና ከባድ እንደሆነ በመጥቀስ በክልሉ የአባላት ቁጥር የይስሙላ እንጂ በርካቶቹ የፕረዝዳንቱን አካሄድ በመጥላት ከፓርቲ አባልነት በገዛ ፍቃዳቸው እየወጡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ከዚህ በፊት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብቸኛው ህብረተሰቡ በአመራሮች እየደረሰ ባለው ከፍተኛ በደል የተነሳ ብልፅግና ፓርቲውን በመጥላት አብዛኞቹ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲ በመምረጥ ለክልልና ለፌደራል ፓርላማ ተወካዮቻቸውን መርጦ ካስገቡ ዞኖች አንዱ ጋሞ ዞን እንደሆነ ይታወቃል።
የዎላይታ ታይምስ (WT) ሚዲያ ባደረገው ዳሰሳ፣ የክልሉ አመራር በተለይ በዎላይታ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ፣ በአሪ፣ በደቡብ ኦሞ እና በሌሎች ብሔረሰቦች ላይ “በረቀቀ ዘዴ በደል እየፈጸመ ነው” በሚል በምሁራን፣ በወጣቶችና በገበሬዎች ዘንድ እየተነጋገረበት ይገኛል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ ሁለት አመት ቢሆንም፣ ክልሉን በሚያስተዳድሩት አካላት ላይ የቅሬታ መአት እየጎረፈ ሲሆን በተለይም ተቋማትን ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ማከፋፈላቸው፣ የዞኑን ህዝብ ፍላጎትና አቅም ያላገናዘቡ ውሳኔዎች ማሳለፋቸው፣ እንዲሁም ቀደም ሲል በክላስተር ከተሞች ተዋቅረው የነበሩ ቢሮዎችን መዝጋታቸው ህዝባዊ ተቃውሞ አስነስቷል።
በርካታ ነዋሪዎችና ምሁራን፣ ይህ አካሄድ በክልሉ ውስጥ ያለውን ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የህዝቡን እኩል የመልማት ጥያቄ ካልተመለሰና የብልጽግና ፓርቲ አመራሩ ላይ እርምጃ ካልወሰደ፣ በ2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ “በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ አደገኛ እጣ ፈንታ ይገጥመዋል” የሚል ግምትም ከወዲሁ ተሰጥቷል።

ከዚህ ቀደም በነበረው የደቡብ ክልል አስተዳደር ወቅትም ሆን ተብሎ ልማትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲገታ መደረጉ አሁንም በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እየተደገመ ነው የሚል ክስ ቀርቧል።
የተለያዩ የክልሉ ዞኖች ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ በላኳቸው መልዕክቶች፣ በጭቆና ላይ የተመሰረተ አብሮነት እንደማይቀበሉ፣ የህዝቡ የእኩል የመልማት መብት እንዲከበርላቸው፣ እንዲሁም ችግር ፈጣሪ አመራሮች የመፍትሄ አካል መሆን ስለማይችሉ የፌዴራሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባላቸው ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ከዚህ በፊት በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በቁጫ እና ዛይሴ ህዝቦች ላይ ባደረሰው ኢፍትሃዊነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ጭቆና ማድረሱን ተከትሎ ህዝቡ ገዢው ፓርቲው በአከባቢያቸው እንዳይመረጥ በማድረግ የራሳቸውን ተወካዮችን ለፓርላማ እና ለክልል ምክርቤት ማስመረጣቸው ይታወቃል።
በሌላ ዜና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባጠናቀቀው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ያፀደቀው አብዛኞቹ መስሪያ ቤቶች ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተጠሪ እንዲሆኑ መደረጉ ሰፊ ውይይትና ክርክር ያስነሳው ጉዳይ እስካሁን እልባት አለማግኘቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም፣ ርዕሰ መስተዳድሩ በምክር ቤቱ አቅርበው ለማፅደቅ የሞከሩት የሹመት ጥያቄ በፌዴራል መንግስት ትዕዛዝ ውድቅ መደረጉንና ምርመራ መጀመሩን ታማኝ ምንጮች ለWT ሚዲያ ገልጸዋል።
በሌሎች ነባር ክልሎችም ሆነ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር አብረው በተዋቀሩ ክልሎች የመዋቅር ለውጥ ሳይደረግ፣ ገና ምስረታውን ባልጨረሰበት በሁለት ዓመት ክልሉ ውስጥ አዲስ ጥናት ተካሂዶ አዲስ መዋቅር መቅረቡ በርካታዎችን እያነጋገረ ይገኛል።
ምንጮች እንደሚሉት፣ ይህ አዲስ መዋቅር በክልሉ የተፈጸሙ ከፍተኛ ሌብነቶችንና የህግ ጥሰቶችን ለመሸፈን ያለመ ስትራቴጂ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ ይላሉ።
ነገር ግን፣ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ከፓርቲ ጋር ሳይመካከሩ በክልሉ ምክር ቤት ያቀረቡት ሹመት በፌዴራል መንግስት ትዕዛዝ ውድቅ መደረጉንና ምርመራ እንዲጀመር መታዘዙን WT ሚዲያ ዘግቦ ነበር።
ይህ ድርጊት የርዕሰ መስተዳድሩ ዋነኛ ዓላማ “የግል ጥቅም ትስስርን በመጠቀም አብዛኛውን የክልሉ መስሪያ ቤቶች ተጠሪነታቸው ለእሳቸው በማድረግ የሌብነት መዋቅሩን ህግ አድርጎ ለማጽደቅ ያለመ ነው” ሲሉ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ ርዕሰ መስተዳድሩ በፌዴራል መንግስት በጀት አማካኝነት በተደራጀ ሌብነትና ዝርፊያ ከመፈጸም ባለፈ፣ በራሳቸው የትውልድ አካባቢያቸው ብቻ በርካታ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስገንባት ላይ መሆናቸው ቅሬታ አስነስቷል።
ክልሉ 32 ብሔረሰቦችን ያቀፈ ቢሆንም፣ የልማት ትኩረቱ በአንድ አካባቢ ላይ ማተኮሩ በሌሎች የክልሉ ከተሞችና ብሔረሰቦች ዘንድ የመገለል ስሜት ፈጥሮ ተቃውሞዎችን እያስነሳ ይገኛል።
WT ሚዲያ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው መደበኛ የካቢኔ ስብሰባ ላይ በርካታ አወዛጋቢ ውሳኔዎች መተላለፋቸውን አረጋግጧል።
እነዚህ ውሳኔዎች የአንዳንድ ቢሮዎችን መበተን፣ መደባለቅና ከደረጃ ዝቅ ማድረግን ያካተቱ ሲሆን፣ ከክልሉ ምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠሩ ነው።
እነዚህ ቢሮዎች መታጠፍ ወጪን ለመቆጠብና አላስፈላጊ ብክነትን ለመቀነስ ተገቢ እርምጃ ቢሆንም፣ ከወዲሁ ከፍተኛ ቅሬታና ስጋት ከሙሁራን ዘንድ እየተሰማ መሆኑን WT ሚዲያ ዘግቧል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ መንግስት እስካሁን ለህዝብ በይፋ ባልተሰራጨበት ሁኔታ የተለያዩ አዋጆችንና ደንቦችን ማፅደቅ ከህግ አንፃር ይቻላል ወይ በሚል ድርጊቱን ግልፀኝነት የጎደለው እያሉ በርካቶች እየተቹ ይገኛሉ።
የመንግስት አመራሮች መረጃ ለወራት በመደበቅ ይፋ አለማድረጋቸው ለሚመሩት ህዝብ ካለመታመን ባሻገር መሰል በርካታ ጉዳዮች በድብቅ እየተሰሩ መሆናቸውን ግልጽ ማሳያ እንደሆነ ብዙዎች ይገልጻሉ።
ከዚህ በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሶስት ወራት በላይ ተሰርቆ ተደብቆ የነበረው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ደብዳቤ ከድብቅበት መውጣቱ ይታወሳል።
ይህ አዲስ የቢሮ አደረጃጀትና አመዳደብ የክልሉን ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና የአመራር ምደባ ጉዳይ ይበልጥ የሚያወሳስበው መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙ ሲሆን ነባሩ መዋቅር ገና ተደራጅተው ሳይጠናቀቅ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት በተዋቀረው አዲስ መስሪያቤቶች ፕረዚዳንቱ ሹመት እንዳይሰጥ የፌደራል መንግስት መከልከሉ ግርምትን ጭሯል።