በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን በዛይሴ ብሔረሰብ ላይ የፀጥታ አካላት የዘር ማጥፋት ጥቃት እየፈጸሙ እንደሆነ ተዘገበ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩት የዛይሴ ብሔረሰብ ላይ በክልሉ ልዩ ኃይልና በጋሞ ዞን መደበኛ ፖሊሶች ከባድ ጥቃት መፈጸሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ በቀን 3/12/2017 ዓ.ም በፀጥታ አካላት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመጥቀስ፣ የሕይወት እና የንብረት ውድመት መድረሱን አስታውቀዋል።
ለWT ሚዲያ በደረሰው መረጃ መሠረት፣ የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት ሚሊዮን ገዙ እና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ፌዣ ባሰማሩት የፀጥታ አካላት አማካኝነት በዛይሴ አርሶ አደሮች እርሻ ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።

በነሐሴ ቀን 3/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 11፡30 ገደማ፣ የፀጥታ አካላት በዛይሴ እርሻ ማሳ ላይ መሣሪያ እየተኮሱ ከብት የሚያሰማሩ እረኞችን ካባረሩ በኋላ፣ ፍየሎችን አርደው መብላታቸውን አንድ የአይን እማኝ ወጣት ገልጿል።

በተጨማሪም፣ በቀን 24/11/2017 ዓ.ም በዘይሴ ኤልጎ ቀበሌ፣ ሻንካ አካባቢ የአርሶ አደሮችን በቆሎ የጫኑ 10 መኪናዎችን መንገድ ላይ በማስቆም ይዘው ለሁለት ቀናት ካቆዩ በኋላ፣ እያንዳንዱን አርሶ አደር አንድ ሺህ (1,000) ብር እንዲከፍሉ በማስገደድ በቆሎአቸውን መልቀቃቸውም ተነግሯል።
አካባቢው ነዋሪዎች፣ የክልሉ መንግስት እና የጋሞ ዞን አመራሮች በዛይሴ ሕዝብ ላይ ለሚፈጸመው ግፍ ሽፋን እየሰጡ ነው ሲሉ ይከሳሉ።
በተለይም የጋሞ አመራሮች፣ የዛይሴን ሕዝብ ዘር የማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ እንደሆነ ገልጸዋል። ከቀድሞ ወታደራዊ አባላት እና የጋሞ ሚሊሻን በመመልመል “የዛይሴን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ካጠፋችሁ፣ መሬታቸውን አካፍለን እንሰጣችኋለን” የሚል ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል።
እንደሚያመለክት ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ሕዝቡ በከፍተኛ ጭቆና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ የጋሞ አመራሮች በሕገወጥ መንገድ መሬታቸውን ለመውረስ መጣራቸውን አውስተዋል።
የዛይሴ ብሔረሰብ የፌዴራል መንግስት በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲያወርድ በአክብሮት ተማጽኗል። የሕዝቡ የሰላም እና የጥበቃ ጥያቄ በከፍተኛ ደረጃ መተላለፉን፣ መንግስትም ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።