የዎላይታ ዲቻ ዋንጫ ክርክር፣ የኦቶናውን ሆስፒታል ቃጠሎ እንዲሁም የአጆራ ፏፏቴ ውዝግብ አጀንዳ ለህዝቡ በመስጠት በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ሀብት ለመቀራመት የተደረገው ሙከራ በፌደራል መንግስት ተደርሶበት መታገዱ ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከቢሊዮን ብሮች በላይ የሚያወጡ የግንባታ ፕሮጀክቶች በፌዴራል መንግስት መታገዳቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ አመራሮች ላይ ከፍተኛ የሙስና እና የጥቅም ግጭት ክሶች እየቀረቡ ስለመሆኑ ተነግሯል።
WT ሚዲያ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እነዚህ ውዝግቦች ከጨረታ ውጪ የተሰጡ የግንባታ ኮንትራክቶች እና የተመሰረተው ክልል ገና በእግሩ ሳይቆም ሌላ አዲስ መዋቅር ለማደራጀት በሚል የወጣ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ላይ ያጠነጥናሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስድስት የማዕከላት ቢሮዎችን ለመገንባት በሚል በቢሊዮን የሚቆጠሩ ብሮች ለተወሰኑ የግንባታ ተቋራጮች ያለ ጨረታ መሰጠታቸው ተገልጿል።
እነዚህ ተቋራጮች ከክልሉ አመራሮች ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል።
ለመሆኑ ይሄ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስድስት ማዕከላት ቢሮ ለመገንባት በሚል በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያለጨረታ በጥቅም ለተሳሰሩ ግለሰቦች ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም የፌዴራል መንግስት በሂደቱ ላይ ችግር መኖሩን በማረጋገጥ ስለታገደው በርካታ አስተያየቶች እየቀረቡ ያሉት የትኞቹ ናቸው ?
1. አተም ጀነራል ኮንትራክተር ከሀዲያ የርዕሰ መስተዳድር ህንፃ በዎላይታ ሶዶ የሚገነባ
2. ኤፍኤ ጀነራል ኮንትራክተር ከጋሞ (የፍፁም ታዬ) ምክርቤት ህንፃ በአርባምንጭ
3. ድላ ትሬዲንግ ጀነራል ኮንትራክተር ከድላ የክላስተር ቢሮ በድላ ከተማ የሚገነባ
4. ኤልኢሲ እንጂኔሪንግ ጀነራል ኮንትራክተር ከሲዳማ (የፍፁም ታዬ) የክላስተር ቢሮ ግንባታ በኮንሶ ካራት የሚገነባ
5. አንጁሎ አርሻ ቡይልድንግ ኮንትራክተር ከጋሞ የክላስተር ቢሮ ግንባታ በጅንካ ከተማ የሚገነባ
6. ጉጃ ጉሌ ጀነራል ኮንትራክተር የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ፕረዚዳንት ዶክተር ጉቼ ጉሌ ወንድም ከጎፋ የክላስተር ቢሮ በሳውላ ከተማ የሚገነባ ይሆናል።
በዘገባው መሰረት፣ የፌዴራል መንግስት በግንባታው ሂደት ላይ ችግር መኖሩን በማረጋገጥ ፕሮጀክቱ እንዳይቀጥል አግዷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከተሉት ዋና ዋና ክሶች ተነስተዋል፦
የግንባታ ኮንትራክቶቹ የተሰጡት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የክልሉ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑን ጨምሮ ከበርካታ አመራሮች ጋር በትውውቅና በጥቅም ለተሳሰሩ ግለሰቦች ያለ ውድድርና በትውውቅ ብቻ መሰጠት መሆኑ ተጠቅሷል።
የዋጋ መጋነን፦ በፕሮጀክቶቹ ላይ ለፌዴራል ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቅሬታ ደርሷል ተብሏል። ለምሳሌ፣ ለዎላይታ ሶዶ ህንጻ 2.85 ቢሊዮን ብር የተባለው ዋጋ፣ ቢበዛ 2 ቢሊዮን ብር ሊሆን እንደሚችል በመገመት ብቻ 850 ሚሊዮን ብር የማትረፍ እድል እንዳለ ተገልጿል።
በተመሳሳይ የአርባምንጭ ህንጻ 2.27 ቢሊዮን ብር የተባለው ግንባታም 600 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ ያስችላል ተብሎ ተገምቷል።
በመረጃው መሰረት፣ ውድድሩ እንዲሳተፉ የተደረጉት ከክልሉ ውጪ ያሉ ትላልቅ ድርጅቶች አይደሉም። የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ባለሙያዎችም በሂደቱ ውስጥ እንዳልተካተቱ መናገራቸው ተጠቅሷል።
WT ሚዲያ ከሁለት ሳምንት በፊት በዘገበው ሌላ ዜና መሠረት፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የበርካታ መስሪያ ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለራሳቸው ተጠሪ እንዲሆኑ የሚያደርግ አዲስ አዋጅ ማፅደቃቸው ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል።
ተቃዋሚዎች ይህ አዋጅ “ከፍተኛ ሌብነቶችንና የህግ ጥሰቶችን ለመሸፈን ያለመ ስትራቴጂ” ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት እንዳሳደረ ዘገባው ያስረዳል።
በተጨማሪም፣ የፌዴራል መንግስት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በቅርቡ በተዋቀሩ አዳዲስ መስሪያ ቤቶች ላይ ሹመት እንዳይሰጡ መከልከሉ ተገልጿል።
ይህ እገዳ የመጣው አቶ ጥላሁን ከፓርቲያቸው ጋር ሳይመካከሩ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የሹመት ጥያቄ በፌዴራል መንግስት ትዕዛዝ ውድቅ ከተደረገ በኋላ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይም ምርመራ መጀመሩን WT ሚዲያ መረጋገጡ ይታወሳል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን የልማት ፕሮጀክቶች በትውልድ አካባቢያቸው ላይ ብቻ በማተኮር በሌሎች የክልሉ ብሔረሰቦች እና ከተሞች መካከል ቅሬታ እና የመገለል ስሜት እየፈጠሩ መሆኑ ተጠቁሟል።
欄 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች
欄 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን
欄 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን爐
卵 #WolaitaTimes ሚዲያ
#Ethiopia #southethiopia