የመንግስት አመራሮች ስብሰባ መብዛትና የተገልጋዩ ስቃይ ‼️
“ስብሰባ ላይ ነኝ”‼️
የመንግስት አመራሮች ስብሰባ መብዛትና የተገልጋዩ ስቃይ ‼️
አሁን አሁን ለብዙዎች እንደ ችግር እየሆኑ ከመጡ ነገሮች አንዱ ተገልጋዮች የተለያዩ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም ሆነ አቤቱታ ለማቅረብ ከሩቅ ቦታ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት በማባከን የሚመለከታቸውን የመንግስት አመራሮችን በስራ ሰዓት ለማግኘት ስመጡ በስብሰባ መብዛት ምክንያት እንኳን አግኝተው ማናገር ማየትም ከባድ እየሆነ እንደመጣ ከተለያዩ ተገልጋዮች ለማረጋገጥ ችለናል።
ለዚህ እንደ ማሳያ የሚቀርበው ለምሳሌ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ በየማዕኩሉ የሚገኙ አመራሮች ጉብኝት፣ መድረክ፣ ስብሰባ፣ የየቢሮ አፈፃፀምና ዕቅድ ግምገማ እየተባለ የክልሉን አገልግሎት ተቀባይ ህብረተሰቡ ክፍልን በማሰቃየት ላይ እንደሚገኙ ከየቦታው ለWT ሚዲያ የደረሰን ቅሬታ ድምፆች ያረጋግጣሉ።
በተለይም ደግሞ እንደ ዎላይታ ዞን አንድ መስሪያ ቤት የዓመት ሆነ የስድስት ወር አፈፃፀም ስብሰባ ወይም ሌላ በሶዶ ከተማ የሚያካሂድ ከሆነ ከሁሉም ወረዳ የፊት አስተባባሪ የሚባሉ አመራሮች፣ ከዞን ሁሉም መምሪያ አመራሮች ለሁለት ወይም ለሶስት ቀናት መካሄድ ከተገልጋዩ ህብረተሰብ ጉዳት አልፎ በህዝብ ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ይነገራል።
በዚህ ምክንያት የትኛውም ተገልጋይ “ስብሰባ ላይ ናቸው፣ ስብሰባ ላይ ነኝ” እየተባለ በህጉ መሠረት ተወካይ ሳይኖር አገልግሎቱን በወቅቱ የማግኘት መብት ይነጠቃል። ያ ደግሞ የባለጉዳዮች ጉዳይ በወቅቱ ባለመፈፀም የሚደርስ ገዳት ብቻ ሳይሆን ከሩቅ ወረዳዎችና ዞኖች በሚመጡት ላይ በገንዘብ፣ በጊዜ እንዲሁም በጉልበት ላይ ምን ያህል እንግልት እንደሚያደርስ ግልጽ ነው።
ከዚህ በፊት የስብሰባዎች መብዛትና መንዛዛት የመንግስት የስራ ጊዜ ላይ ተጽዕኖ በመኖሩና በስብሰባ ላይ በማይገባ ክርክርና ጭቅጭቅ የሚባክኑ ሰዓቶችን ለመቀነስ ግንቦት 7/2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዘውትር አርብ ይካሄድ የነበረው የካቢኔ ስብሰባ ወደ ቅዳሜ እንዲዛወር ማድረጋቸው ይታወሳል።
ቢያንስ የአመራሮች ስብሰባ የትኛውም መስሪያ ቤት በሚያዘጋጀው መድረክ እንዲገኙ ከሚገደዱ ለምን ከስራው ጋር ተዛማጅ የሆኑ መስሪያ ቤቶች አመራሮችና ባለሙያዎች ብቻ እንዲገኙ በማድረግ የተገልጋዩን እንግልት መቀነስ አይቻልም ?
በተገልጋዮች ላይ ብቻ የሚደርስ ከፍተኛ እንግልትና ጉዳት ብቻ ሳይሆን በስብሰባ መብዛት ምክንያት የሚባክነውን የህዘብ ገንዘብ፣ ጊዜና ንብረት መቀነስ አይቻልም ? ይህ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ትዝብትና ጥያቄ ነው።
በሌላ ዜና ከነገው ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም ጀምረው አጠቃላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራር ዎላይታ ሶዶ ከተማ ይከትማሉ! ስልክ መያዝ አይፈቀድም ተብሏል። ለWT ሚዲያ እንደ ደረሰው መረጃው ከሆነ የመድረኩ ዋናው አላማ በክልሉ ባለፉት ሁለት አመታት ጉዞ አፈፃፀም መገምገም በቀጣይ ዕቅድ ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል።
እርሶዎ በጉዳዩ ዙሪያ ምን ይላሉ?