በኢትዮጵያ ካሉት የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በአመራር ብቃት እና ዩኒቨርሲቲውን በመለወጣቸው እንዲሁም በአፈፃፀም አንደኛ በመሆን በኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተሸላሚ ሆነዋል::ሽልማቱ ይፋ የተደረገው በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን ላይ ነው፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመማር ፤ማስተማር በማህብረሰብ አገልግሎት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቡ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲው ላከናወነው ታላቅ ሀገራዊ ተልዕኮን ማስፈፀም በአፕላይድ ዩኒቨርሲቲዎች ሁለተኛ በመውጣቱ እውቅና ሽልማት ሰጥቷል። በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ወርቁ እንደገለጹት፣ የሽልማቱ ዓላማ በኢትዮጵያ የሳይንስ ሂደትን ማጎልበት ሲሆን በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገበ ሳይንቲስት የሚሰጥ ነው፡፡የኢትዮጵያ ሳይንስ ሽልማት አሸናፊ አንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የወርቅ ሜዳሊያ፣ ልዩ የዕውቅና ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ሽልማቱ የኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የተሰጠው ቢሆንም በሂደት አፍሪካውያንም ጭምር ያካትታል ተብሏል፡፡

የአሁኑንን ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የላቀ ስራ ላስመዘጉ ሳይንቲስቶች እውቅና እንደሚሰጥ የገለጹት ዶ/ር ወርቁ ከስድስት የተለያዩ ተቋማትና የሙያ ማህበራት እንዲሁም ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ገለልተኛ በሆነ ቦርድ ይመራል፡፡

የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ሳይንስ ሽልማቱ ቦርዱን በሰብሳቢነት ያገለግላሉ ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ሳይንስ ሽልማት በዓመት ለአንድ የላቀ ሳይንሲስት የሚሰጥ ሲሆን የኢትዮጵያ የሳይንስ ሽልማት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በየዓመቱ በሚካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን ላይ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ ካሉት የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በአመራር ብቃት እና ዩኒቨርሲቲውን በመለወጣቸው እንዲሁም በአፈፃፀም አንደኛ በመሆን በኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተሸላሚ ሆነዋል::

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-ዌብሳይት www.wolaitatimes.com.etፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/wolaitatime/ቴሌግራም፦ https://telegram.me/Kiikiyaዩቲዩብ፦https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw… በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።Wolaita Times, 08/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia