GridArt_20250911_175239355

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመንግሥትን ብልሹ አሠራርና ሙስና የሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰው የጅምላ እስርና ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱ ተነግሯል።

WT Media በጉዳዩ ዙሪያ በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ምስጥራዊ የዳሰሳ ምርመራ አድርገው ባጠናቀረው በዚሁ ልዩ ዘገባ በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ከ50 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና የሲቪክ ማኅበራት አባላት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታሰራቸውንና አብዛኞቹ ፍርድቤት አለመቅረባቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።

በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች የታሰሩ ግለሰቦች

በመረጃው መሠረት በክልሉ በጋሞ ዞን፣ በተለይም በምዕራብ አባያ፣ በብርብር፣ በዲታ፣ በከምባ፣ በደራማሎና በቦረዳ ወረዳዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የሚያነሱ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየደረሱ ነው።

በምዕራብ አባያና ብርብር ከተማ፦ በሙስና የሚታወቁ አመራሮች አቶ ታገል ይገዙ፣ አቶ ደፋሩ ጎቼ፣ አቶ ዓለም እሸት ዱሬሳ፣ አቶ ታምራት ጦቃ፣ አቶ ካሌብ ካሳ፣ አቶ መርክን ቦንጃ እና አቶ ወንድማገኝ መንግሥቱ ያለአግባብ ታስረዋል።

የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እንደገለጹት፣ አዲሱ ዓመትን ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በጋሞ ዞን ደረቅ ጣቢያ እንዲያሳልፉ ተደርገዋል። ምንም እንኳን ፍርድ ቤት ቀጠሮ ቢሰጣቸውም፣ ፍትህ ማግኘታቸው እንደተከለከለ ገልጸዋል።

በከምባ አካባቢ፦ በማኅበራዊ ሚዲያ የሙስናና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎችን የሚያጋልጥ የነበረው አቶ ሀብታሙ ሞገስ በጋሞ ዞን ፖሊስ በግፍ ተይዞ በአርባ ምንጭ ሼቻ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስሮ የሕክምና ዕርዳታ መከልከሉ ተጠቅሷል።

በደራማሎና ሌሎች ወረዳዎች፦ በደራማሎ ወረዳ ያለአግባብ የሰዎችን ሕይወት ያጠፉ ፖሊሶች ላይ ምስክርነት የሰጡ ግለሰቦች ቤት በሌሊት በመግባት ንብረት መዝረፍና የግድያ ሙከራ መፈጸሙን ለማወቅ ችለናል።

በጨንቻ ከተማና በቆጎታ ወረዳም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ያነሱ ግለሰቦች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በየቀበሌዎች ታስረዋል።

በጌዴኦ ዞን፣ በተለይም በዲላ ከተማና በይርጋጨፌ ወረዳ፣ ከነሐሴ ወር ጀምሮ በርካታ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስረዋል።

የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጌህዴፖ) ተወካዮች የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ያልተከተሉ እስሮች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳስበዋል።

ከታሰሩት መካከል አንዳንዶቹ ቋሚ የሕክምና ክትትል የሚፈልጉ መሆናቸውና አገልግሎቱ እንደተከለከሉ ተገልጿል።

በዲላ ከተማ፦ ቀደም ሲል የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩና ብልሹ አሠራርን ይዋጉ የነበሩ አቶ ጴጥሮስ ወቴ በዲላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሳይሆን በጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለማደር በማይመች ክፍል ውስጥ መታሰራቸው ተዘግቧል።

በይርጋጨፌ ወረዳ፦ አቶ ምትኩ ወራሳ፣ አቶ ኃይለማሪያም ጥላሁን እና አቶ አብዮት ጄቦ በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ የፓርቲና የመንግሥት ኃላፊዎች መታሰራቸው ተገልጿል።

በጎፋ ዞን፦ የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች በጅምላ ታስረዋል።

የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ

በዎላይታ ዞን፦ በመንግሥት ሚዲያ ብልሹ አሠራርና ሌብነት እንዲጋለጥ ያደረጉት ወጣቱ ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ|ን ጨምሮ ሌሎች አምስት ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል።

ወጣቱ ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ

በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞና ባስኬቶ፦ ባለፈው ሳምንት ብቻ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ያነሱ ከ12 በላይ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በየደረቅ ፖሊስ ጣቢያዎች መታሰራቸው ተገልጿል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ጋሞ ዞን፣ ዎላይታ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ሌሎች አከባቢዎችም የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በሚያነሱ ዜጎች ላይ እስር፣ ግድያ፣ የንብረት ዝርፊያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ስለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከላይ የተጠቀሱት በፖሊስና አስፈጻሚው የመንግስት አካል በዜጎች ላይ እየፈጸሟቸዉ የሚገኙት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ጥቂት ማሳያዎች ናቸዉ እንጂ ድምጻቸዉ ታፍኖ በየአካባቢው በስቃይ ዉስጥ የሚገኙ፣ ከስራ የተባረሩ፣ ህጋዊ መብታቸውን የተነፈጉ፣ በግፍ የተገደሉ እንዲሁም አካላቸው የጎደለባቸው ዜጎች በርካቶች እንደሆነ ከመረጃው ተገንዝበናል።

በዚህ በተጀመረው በክልሉ መንግስት በተጀመረው ዘመቻ የታሰሩ አብዛኞቹ ግለሰቦች ፍርድቤት አልቀረቡም።

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የዞን፣ የክልል አመራሮችን በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጡበት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

በአስፈጻሚው የመንግስት አመራሮች እና በፖሊስ ተቀናጅተዉ በደቡብ ኢትዮጵያ ብሎም በሌሎች አከባቢዎች እየፈጸሙ የሚገኙ መጠነሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ እንደሚገኙ WT Media በጉዳዩ ዙሪያ በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ምስጥራዊ የዳሰሳ ምርመራ አድርገው ባጠናቀረው በዚሁ ልዩ ዘገባ ያረጋግጣል።

በመረጃው መሰረት፣ ይህን ዘመቻ የሚመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደሆኑና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚቀርቡባቸውን የተደራጀ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን የሚያጋልጡና ትችት የሚያቀርቡ ግለሰቦችን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እያሳሰሩ፣ እያሳደዱና እያሰቃዩ እንደሆነ በዳሰሳ ምርመራ ተጠቅሷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪዎችና ወጣቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማትና የፌደራል መንግሥት በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን ኢፍትሐዊነት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጅምላ እስር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡበት ጥሪ አቅርበዋል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT MEDIA በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media

በድጋሚ መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 🙏
ፍትህ፣ እውነት፣ ሰላም፣ ልማት፣ ደስታ እንዲሁም ጥጋብ ለሀገራችን የሚሰፍንበት የሃቅ ዓመት ይሁንልን🙏

Ethiopia #southethiopia

Read more on our official