GridArt_20250913_162841090

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ የሚገኘው የኦቶና ሆስፒታል መውደሙ ህብረተሰቡን ለከፍተኛ የጤና አገልግሎት እጦትና ቀውስ ከመዳረግ ባለፈ የበርካቶች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።

ከአንድ ወር በፊት “ባልታወቀ ሁኔታ በደረሰ ድንገተኛ ኢሳት ጥቃት ምክንያት ወድሟል” የተባለው ሆስፒታል መልሶ ግንባታ ባለመጀመሩ፣ የበርካታ ህሙማን ህይወት አደጋ ላይ እንደወደቀ ከስፍራው ለWT Media የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የተቃጠለውን ሆስፒታል የመንግስት አመራሮች ሲጎበኙ

በተለይም በአከባቢው የጤና መድህን ተጠቃሚ የሆኑ እና ሌላ ቦታ ለመታከም አቅም የሌላቸው አርሶአደሮች እና ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ የጤና ስቃይ ተጋልጠዋል።

በተጨማሪም ይሄው ግዙፉ ለበርካቶች ዘርፈብዙ የጤና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ እየሰጠ የነበረው ሆስፒታል ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በእሳት በመቃጠሉ በአከባቢው የግል ህክምና ተቋማት ህብረተሰቡን ከፍተኛ የአገልግሎት ክፊያ እንዲያስከፍልና ህብረተሰቡ ለከፍተኛ ላልተፈለገ ወጪ እንዲዳረግ እያስገደደ ስለመሆኑም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሆስፒታሉ ለዘመናት ለዎላይታ እና ለአጎራባች አካባቢዎች ተመራጭ የሆነ ብቸኛ የህክምና ማዕከል እንደነበር የተገለፀ ቢሆንም አሁን ላይ የሆስፒታሉ መልሶ ግንባታ መዘግየት ዋነኛ ችግር ሆኖ ቀጥሏል።

ከስፍራው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመልሶ ግንባታው ቃል የገቡትን ገንዘብ ባለመስጠታቸው ብቻ ሳይሆን እንደ የጉዳዩ ባለቤት ትኩረት በመንገፋቸው ምክንያት እንቅፋት እየፈጠሩ ነው ተብሏል።

በዚህም መነሻ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላትም አስተዋፅኦ እያደረጉ እንዳልሆነ WT Media ባደረገው መረጃ በማሰባሰብ ለማረጋገጥ ችሏል።

የዎላይታ ዞን አስተዳደርም የህዝቡን አንገብጋቢ ጉዳይ ትኩረት ባለመስጠቱ፣ ለሆስፒታሉ መልሶ ማቋቋሚያ የተሰበሰበ ገንዘብ ወደ ሥራ ሳይገባ በመቅረቱ የበርካቶች ህይወት እየጠፋ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።

Caption by WT Media

እስካሁን የአደጋው መንስኤ በግልጽ ለህዝብ ያልተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ሁኔታ የህብረተሰቡን ስጋት እንደጨመረ ተመላክቷል።

በመሆኑም ይሄንን ግዙፉ ዕደሜጠገብ ለበርካቶች ዘርፈብዙ የጤና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በመስጠት ባለውለታ የሆነውን ሆስፒታል ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚመለከታቸው አካላት፣ የህዝብ ተወካዮች እንዲሁም የዞኑ አስተዳደርም ለዚህ አንገብጋቢ ህብረተሰብ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ አፋጣኝና አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media