የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ፍሬው አልታዬን ለማሰብና ለማክበር የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት በዎላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ተመርቋል።

የመታሰቢያ ሐውልቱ ግንባታ ስድስት ዓመታት ያህል የፈጀ ሲሆን፣ በተለያዩ የህዝብና የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የመታሰቢያ ሐውልት፣ እንደ መልዕክቱ አመላካችነት፣ ለወደፊት የህዝብ መሪዎች አርዓያ ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦበታል።
ይህ መታሰቢያ ሀውልት የህዝብን ስልጣን በታማኝነትና በቅንነት የሚመሩ መሪዎች ሁሌም በህዝባቸው እንደሚታሰቡና እንደሚከበሩ ያሳያል።



የፕሮጀክቱ አስጀማሪዎች፣ አቀናባሪዎች እና ግንባታው እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላት ለዚህ ስኬት ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል።
ቀጣይነት ባላቸው የህዝብ ፕሮጀክቶች ላይም ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን፤ በተለይም የተጀመሩ መሰል እንደ ካዎ ጦና እና የካዎ ሳሶ ሞቶሎሜ መታሰቢያ እንዲሁም የተጀመሩ የህዝብ አንገብጋቢ ፕሮጀክቶች በአዲሱ ዓመት ተጠናቀው ለምረቃ እንዲበቁ ተስፋ እናደርጋለን።
ሁሉም ዜጎች ባሉበት ቦታ በእውነት፣ በታማኝነት እና በሐቀኝነት ከሰሩ አንዲህ በአደባባይ ይከበራሉ፣ ይህ ደግሞ ህዝብን የሚያገለግል ማንኛውም ሰው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደሚታወስና እንደሚከበር የሚያረጋግጥ መሆኑን ያጎላል።