1758309922807

የዎላይታ ሕዝብ የዘመን አቆጣጠርና የጊፋታ በዓል መሠረቶች

“የዎላይታ ሕዝብ የመጀመሪያው ቀን መቆጠር የጀመረው በSeptember 23, 4004 BC እሁድ ዕለት ነው ብሎ ነው የሚያምነው። ይህም በዘፍጥረት 1:5 “ቀን አንድ” ተብሎ የተጠራው ቀን ሲሆን ፈጣሪ በዘፍጥረት 1፡3 ላይ “ብርሃን ይሁን” ባለ ዕሌት የተፈጠረ ቀን ነው ብሎ ያምናል – ሕዝበ ዎላይታ።

በዚህ የዎላይታ አቆጣጠር መሠረት የመጀመሪያው ጊፋታ 1 የዋለው ከ”ቀን አንድ” ጀምሮ እስከ 364 ቀናት ከተቆጠረ በኃላ ባለው እሁድ ማለትም በSeptember 22, 4003 BC (ከክርስቶስ ልደት በፊት) ላይ ነበር።

በነገራችን ላይ የዎላይታ ሕዝብ ምድር የተፈጠረው ከመጀመሪያው ቀን ማለትም ከSunday, September 23, 4004 BC እጅግ እጅግ በፊት ነው ብሎ ያምናል። ለዚህም መነሻው ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1-2 እና ዘፍጥረት ምዕራፍ 1:3-5 ድረስ ያለው ክፍል ነው።

በዘፍጥረት 1:1-2 ላይ “1፤ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። 2፤ ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።” ስለምል እና ይህንን አንቀጽ ከዘጋ በኃላ ሌላ አንቀጽ በመክፈት ደግሞ እንደሚከትለው ስለምነበብ፣

ዘፍጥረት 1:3-5 ባለው ክፍል ደግም “3፤ እግዚአብሔርም። ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። 4፤ እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ። 5፤ እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።” ስለሚል፣

በሁለቱ ክፍሎች ማለትም በዘፍጥረት 1:1-2 እና ዘፍጥረት 1:3-5 መካከል እጅግ በጣም ለቁጥር የሚታክቱ ዘመናት አልፏል ብሎ ያምናል – የዎላይታ ሕዝብ።

ይህም የዘመናችን ሳይንትስቶች Gap Theory ከምሉት ጋር ሳይመሳሰል አይቀርም ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ፈጣሪ “በመጀመሪያ” ምድርንና ሰማያትን ከፈጠረ በኃላ “ቀን አንድ” ን ከመፍጠሩ በፊት ባሉት ጊዜያት መካከል ባለው ሕልቆ ዘመናት ውስጥ “… ምድርም ባዶ ነበረች፣ አንዳችም አልነበረባትም …”።

(ሰጥያን ወይም ሳትናኤል ወይም የአጥቢያ ኮኮብ ወይም ሉስፈር በምድር ላይ የወደቀው በዚህ ወቅት ሲሆን ይህም አዳም ከመፈጠሩ እጂግ በፊት መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል።)

የሆነ ሆኖ አዳም የተፈጠረው ፈጣሪ “ቀን አንድ”ን ማለትም እሁድን ከፈጠረ ጀምሮ ስንቆጥር ባለው ስድስተኛው ቀን ማለትም አርብ ዕሌት ሲሆን ይህም  Gifaataa 6 Biittaa Layttaa (B.L.) ወይም Gifaataa 6, 4004 BC ተብሎ ይታወቃል።

በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ የቢቶ ዳይናስቲ ወይም ሥርዎ መንግስት በዎላይታ የነገሠው። (ስለ ቢቶ እና ቢዲንቶ ሥረዎ መንግሥት በሌላ መጣጥፍ ቢናነሳው ይሻላል።)

የB.L. እና BC ልዩነትን በተመለከተ BC ከክርስቶስ ልደት ጀምሮ ወደ ኃላ አንድ፣ ሁለት እያልን ቆጥረን የሚናገኘው ሲሆን B.L. (Biittaa Layttaa) ግን “ቀን አንድ” ተብሎ የሚጠራው እሁድ ከተፈጠረ ጀምሮ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት እያልን ወደ እኛ ዘመን ድረስ የምንቆጥረው ነው።

ይህም ዛሬ ላይ “ቀን አንድ” ከተፈጠረ 6029 ዓመታት አልፏል ተብሎ ይታሰባል። ምክንያቱም Gifaataa 1, 4004 BC ሲደመር ዛሬ Gifaataa 4, 2025 AD ሁለቱ ሲደመሩ 4004 + 2025 = 6029 ዓመት ስለሆነ ነው። በዚህ መሠረት ዛሬ ቀን Gifaataa 5, 6029 B.L. ወይም Gifaataa 5, 2025 G.C ነው የሚሆነው።

እዚህ ላይ አሁንም አንባቢው ልብ እንድለው የምፈልገው ነገር ቢኖር “ቀን አንድ” ከመፈጠሩ ወይም መቆጠር ከጀመረበት ቀን በፊት ላይ እጂግ ስፍር ቁጥር የሌለው ዘመን ያለፈ መሆኑን ነው። ይህም በጥቅሉ “በመጀመሪያ …” ተብሎ ነው በዘፍጥረት 1:1 ላይ የተጠቀሰው። ስለዚህ በ”ቀን አንድ” እና “በመጀመሪያ” መካከል ሰፊ ልዩነት አለ ማለት ነው። ይህ ነው እንግዲህ በሳይንትስቶች Gap Theory እየተባለ የሚጠራው።

ያም ሆነ ይህ በዎላይታ ሕዝብ እምነት መሠረት የመጀመሪያው ጊፋታ (Gifaataa) የተከበረው ከዛሬ 6028 ዓመታት በፊት ማለትም “ቀን አንድ” ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠር 52 ሳምንታት ካለፉ በኃላ በነበረው ወይም በዋለው በመጀመሪያው እሁድ ነበር። ይህም Gifaataa 1, 001 B.L. ወይም September 23, 4003 BC ነው የሚሆነው።

የወላይታ ጊፋታ ሁለም የሚውለው እሁድ ዕለት ሲሆን ባለፈው እና በሚቀጥለው ጊፋታ መካከል 364 ወይም 371 ቀናት ነው የሚኖሩት። ይህም በቀጥታ ከSolar System ጋር የተገናኘ ሲሆን የጊፋታ በዓል እና ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምታደርገው እሽክርክሮሽ በእጂጉ የተያያዙ ናቸው።

እንደምናውቀው ምድር በፀሐይ ዙርያ በሚታደረገው እሽክርክሮሽ ምክንያት አራቱ ወቅታት (seasons) ይፈጠራሉ። እነሱም በቅደም ተከተል Ofiintta (Spring), Boniyaa (Summer), Bal77eessa (Autumn), እና Balgguuwaa (Winter) ናቸው።

እዚህጋ Boniyaa የሚለውን Summer ብዬ የጻፍኩት ተሳስቼ ሳይሆን ይህ ወቅት በደቡባዊ ንፍቀ ክልል (Southern Hemispher) ላይ Summer ሲሆን በሰሜናዊ ንፍቀ ክፍል ላይ ደግም Winter ስለሚሆን ነው። ሰዎች በተለይ የኢትዮጵያ ጸሐፊዎች ይህንን ሳይገነዘቡ ለNorthern Hemispher Summer (ይህ ወቅት ለእነሱ በጋ ወቅት ነው) የእኛን ክረምት Summer እያሉ ይተረጉማሉ። ይህም እኛ ከፈረንጆች ጋር ባለን ንግግር ወቅት ከፍተኛ ችግር ይፈጥራል።

እኛ በሀገራችን ዝናብ እየዘነበ ነው ይህም በእኛ አገላለጽ ክረምት ነው በእንግሊዝኛ ደግሞ Summer ነው ስንላቸው Summer ማለት እኮ በእኛ በፈረንጆች አገላለጽ እልም ያለ ፀሐያማ ወቅት ነው ይሉና ይወዛገባሉ።

እነደዚህ ዓይነት አያሌ ስህተቶቾ አሉ የኛ ጸሐፊዎች የሚፈጥሯቸው። ያንን እዚሁ ትተን ወደተነሳንበት ነጥብ እንሂድ።

ጊፋታ ሁልጊዜ የሚውለው እሁድ ነው የምንልበት ምክንያት ግልጽ የሆነ ይመስለኛል። በሌላ አገላለጽ የዎላይታ ዘመን መለወጫ የሆነው ጊፋታ አንድ ሁለም እሁድ ነው የሚውለው ማለት ነው። ጊፋታ 1 እሁድ ጀምሮ የዓመቱ መጨረሻ የሚሆነው ቅዳሜ ይሆናል።

በዎላይታ አቆጣጠር ሳምንት የሚጀምረው እሁድን አንድ በማለት ሲሆን ሳምንቱ የሚያበቃው ደግሞ ቅዳሜ ላይ ነው። ይህም በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 12 ቁጥር 1 ላይ “ሰንበት ባለፈ በመጀመሪያው ቀን” ከሚለው ጋር ይመሳሰላል። ለዚህም ነው እሁድን የጌታ ትንሣኤ ቀን አድርጎ እንደ መጀመሪያ ቀን የሚወስደው – የዎላይታ ሕዝብ። ከሁሉ በላይ ግን በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 5 ላይ የተጠቀሰው “ቀን አንድ” እሁድ ነው ብሎ ነው የዎላይታ ሕዝብ የሚነሳው።

በዚህ ቱባ ባህሉ እና እምነቱ ተስማምተን ቀመሩን ከአስትሮኖሚ እና ተፈጥሮ ሕግ ጋር በሒሳብ ቀመር ስናስተሳስረው የነገሮች ሁሉ ግጥጥሞሽ ፍንትው ብለው ይታዩናል።

ለምሳሌ የዘንድሮው ጊፋታ (Gifaataa) የተከበረው በመስከረም 11፣ 2018 ዓ.ም ወይም September 21, 2025 G.C ነው። ይህ ቀን ደግሞ እሁድ ሲሆን እንዲሁ በዘልማድ የተመረጠ እሁድ ሳይሆን ምድር በፀሐይ ዙሪያ ተሽከርክራ ዙራ አምና ወደተነሳችበት የደረሰችው በዚህ ዕለት ስለሆነ ነው። ይህንን አንባቢ የ2025 September Equinox መቼ ነው የሚውለው ብሎ በGoogle search በማድረግ ማረጋገጥ ይችላል።

በእርግጥ Google እንደሚለው ከሆነ የ2025 September Equinox የዋለው በSeptember 22, 2025 ላይ ነው። የኛ በዓል የዋለው ግን በSeptember 21, 2025 ነው።

ይህ ለምን ሆነ? September Equinoxስ ምንድር ነው? ለምለው አጭር መልስ ከሰጠሁ በኃላ በየዓመቱ የጊፋታ ቀን የትኛው እሁድ ላይ ነው የሚለው ለሚለው ወሳኝ ጉዳይ ምላሹን እዳስሳለሁ።

Google እንደምለው ከሆነ የ2025 September Equinox የዋለው በSeptember 22 ሲሆን የኛ በዓል ጊፋታ የዋለው በSeptember 21 ላይ ነው። ይህ የሆነበት ትልቁ ምክንያት ጎጊል ያለበት ሀገር ቀን የሚነጋው ከእኛ አንጻር ወደ 9 ሰዓታት ዘግይቶ ስለሆነና እኛ በዓሉን የምናከብረው በዛው መሠረት ስለሆነ ነው September 21 ላይ የምናከብረው።

September Equinoxስ ምንድነው ለሚለው ጥያቄ አጭሩ መልስ በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ክረምቱ አልቆ ፀደይ የሚጀምርበት ቀን ሲሆን በዚህ ቀን ፀሐይ ቀጥታ በምድር ወገብ ላይ ታነጣጥራለች። ከዛ ቀን በፊት ግን ወደ ሰሜናው ንፍቀ ክበብ አጋድላ ነው የቆየችው ማለት ነው።

ወደ ወሳኙ ነጥብጋ ስንመለስ ደግሞ በየትኛው እሁድ ነው ጊፋታ አንድ የሚውለው ለሚለው ደግሞ ምላሹ፦

1) የመጀመሪያው ነጥብ ካለፈው ዓመት ጊፋታ መጀመሪያ ቀን እሁድ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ቀን ቅዳሜ ድረስ ያለው ጊዜ አንድ በአንድ ሲቆጠር ወይ 364 ቀን አሊያም 371 ቀን ይሆናል። ለምሳሌ የዘንድሮው ጊፋታ በመስከረም 11፣ 2018 ዓ.ም ስለተከበረ ከመስከረም 11፣ 2018 ዓ.ም እሁድ ጀምሮ እስከ መስከረም 9፣ 2019 ዓ.ም ቅዳሜ ድረስ ያለው 364 ቀናት ነው የሚሆነው።

ስለዚህ የ2019 ዓ.ም ጊፋታ የሚውለው በመስከረም 10፣ 2019 ዓ.ም ነው ማለት ነው። ለምንድ ነው ከዛ በፊት ባለው እሁድ ማለትም በመስከረም 3፣ 2019 ዓ.ም አይከበርም የሚል ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ለዚህ በቂ ምላሻ መስከረም 3 ከSeptember 23, 2026 Equinox እጂግ በጣም ስለምርቅ ነው። 

2) ሌላኛው ወሳኙ ነጥብ ደግሞ ዓመቱ ለምንድ ነው 364 ወይም 371 የሚሆነው ለምን 365 ወይም 366 አይሆንም ለሚለው ጥያቄ ደግሞ ምላሹ በዚህ አቆጣጠር ከተቆጠረ የዓመቱ መጀመሪያ September 11 ወይም 12 ላይ የሚውል ሲሆን ይህም አሁን ኢትዮጵያ እየተጠቀመች ያለችው አቆጣጠር ሲሆን ይህም ከወሳኙ ከSeptember Equinox እጂግ እርቆ (ከ11 እስከ 12 ቀናት እርቆ) ስለሚወድቅ ነው።

ይህ ደግሞ ከተፈጥሮአዊ መነሻ ሕግ የተዛነፈ ሆኖ ከአያሌ ዓመታት በኃላ ተደማምሮ በሌላ ወቅት ላይ ሊያደርስ ስለምችል ነው። ለምሳሌ በየዓመቱ 11 እስከ 12 ቀናት እየተሳሳትን ከሄድን ከተወሰነ ዓመታት በኃላ በጋ ነው የሚንለው መኸር ሆኖ ሊናገኘው እንችላለን።

3) መጨረሻ ላይ ጊፋት ከመስከረም 9-15 ባለው እሁድ እንደሚውልና ይህም የSeptember Equinox እና የእሁድን መርህ የጠበቀ መሆኑን ለማሳየት ከ2000 G.C እስከ 2100 G.C ድረስ ያለውን የመቶ ዓመታት የጊፋት ቀናት ከዚህ በታች ባለው ቦታ በፎቶ አያይዢያለሁ።” በሮቤል ዲ እጂጉ …. ይቀጥላል።