GridArt_20251001_152138706

ማን ነው ጋሽ ጥሌ (ቲጣሬ ኢሌ)? ለመሆኑ የርዕሰ መስተዳድሩ የብሔር ማንነት ዝውውር እና የሴራ ፖለቲካ ዓላማ አመጣጥ ያውቃሉ ?

እኚሁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት ሰውየው በፖለቲካ ጉዞአቸው በተደጋጋሚ የብሔር ማንነታቸውን በመቀየርና የጥቅም መረብ በመዘርጋት ክልሉን እየመሩ ስለመሆናቸው WT Media ያገኘው ምርመራ ዘገባ ያመለክታል።

ከፍተኛ የፖለቲካ ተንታኞች እና በቅርበት የሚያውቋቸው ግለሰቦች ርዕሰ መስተዳድሩን “ጋሽ ጥሌ (ቲጣሬ) ኢሌ” በማለት በመጥራት፣ ዓላማቸውንና የፖለቲካ ስልታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ (ቲጣሬ ኢሌ) የትውልድ ቦታቸው የዛሬው የጎፋ ዞን፣ በቶ ወረዳ ሲሆን፣ ትምህርታቸውን እዚያው አካባቢ አጠናቀዋል።

የእሳቸው የፖለቲካ ጉዞ እና የማንነት ዝውውር እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፦

የመጀመሪያ ማንነት – አማራ: ርዕሰ መስተዳድሩ በጤና ባለሙያነት (Wound Dresser) በመጀመሪያ የሥራ ቅጥራቸው በሀዲያ ዞን ግምብቾ ወረዳ በነበሩበት ወቅት፣ በሞሉት የቀድሞ የደኢህዴን ኦርኔል ላይ ብሔራቸውን “አማራ” በማለት አስመዝግበው ነበር።

በዚህ ወቅት የሀዲያ ወዳጆቻቸው “ቀሪቾ” የሚል ቅጽል ስም ሰጥተው እንደነበር፣ ይህ ስያሜ የተሰጣቸውም “በአስመሳይነታቸው እና አዛኝ ሆነው ለመታየት በሚፈጥሩት ትወና” ምክንያት እንደሆነ በቅርበት የሚያውቋቸው ሰው ተናግረዋል።

ሁለተኛ ማንነት – ጎፋ፦ ወደ ቀድሞው ጋሞጎፋ ዞን ሲዘዋወሩና ወደ ፖለቲካው ዓለም ሲገቡ፣ በድጋሚ በሞሉት ኦርኔል ላይ ብሔራቸውን “የጎፋ” ብሔረሰብ በሚል ሞልተው የጎፋ ማንነትን ተጎናጽፈዋል።

በዚህ ማንነትም የጎፋን ህዝብ ወክለው የቀድሞውን ጋሞጎፋ ዞን በዋና አስተዳዳሪነት መርተዋል።

ሦስተኛ ማንነት ደግሞ ጋሞ፦ የጋሞ እና የጎፋ ዞኖች ለሁለት ከተከፈሉ በኋላ፣ አቶ ጥላሁን ከበደ የወከላቸውን የጎፋ ህዝብ ላይ ክህደት ፈጽመው፣ የጎፋ ማንነታቸውን ትተው “የጋሞነት” ማንነትን በመጎናፀፍ ወደ ጋሞ ዞን የሥልጣን መዋቅር ተቀላቅለዋል።

ይህን የብሔር ዝውውር የጋሞ አባቶችና ምሁራን በመቃወም “የጋሞ ብሔረሰብ ማንነት የለውም” በማለት ሕዝባዊ ፕቲሽን እስከ ማሰባሰብ የደረሰ ትግል ቢያደርጉም፣ አቶ ጥላሁን ተቃውሞውን በጥቅም፣ በማሰር፣ በማስፈራራትና በማንገላታት በማመከት የጋሞነት ማንነታቸውን አፅንተዋል።

የሴራ ፖለቲካ እና የጥቅም ዓላማ

ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን ካሉበት የክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ሥልጣን ላይ የደረሱት “የሴራ አደረጃጀት ከቤተሰብ መጀመር አለበት” በሚለው መርህ ላይ በተመሰረተ እንቅስቃሴ ነው።

ከቤተሰብ ጀምሮ በየደረጃው የሴራና የተንኮል “ሕቡዕ እኩይ ቡድን” በመጠቀም የክልሉ ህዝብ እርስ በርሱ እንዲጠራጠርና እንዲከፋፈል በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የሕዝብ ሀብት መመዝበር፦ አቶ ጥላሁን ከበደ “ቢሊየነሩ ጥሌ” የሚል ስያሜ እስከ መሰጠት የደረሱ ሲሆን፣ ክልሉን “የእሳቸው ጥቅም ተጋሪዎች አክሲዮን ማህበር” እስከሚመስል ድረስ እንደ ልብ በሴራ እንዲመዘበር እያደረጉ ነው።

የብሔር ማንነት ጥያቄዎችን ማፈን፦ በክልሉ ማንነት ጥያቄ ያላቸውን ብሔረሰቦች (እንደ ዘይሴ፣ ግዲቾ፣ ቁጫ፣ ዶርዜ ወዘተ.) በኃይል በማፈን እና ለህዝቡ ዕለት ተዕለት አጀንዳ በመፍጠር ትኩረትን እያሰቱ መሆናቸው ተገልጿል።

የፖለቲካ ዓላማ፦ ርዕሰ መስተዳድሩ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን ያስቀመጡበት ዓላማ “ፖለቲከኛ የሆንኩት በደህንነቴ ምክንያት ነው፣ ድህንነቴን የማራግፈው በፖለቲካ ነው” በሚል መርህ የተቃኘ ሲሆን፣ ይህ እቅዳቸውም ተሳክቶለታል ማለት እንደሚቻል ዘገባው ያስረዳል።

ዘገባው፦ አቶ ጥላሁን ከበደ ሥልጣን ላይ ለመድረስ የተንጠለጠሉበትን ሕዝብ መክዳት ምግባራቸው በመሆኑ፣ በቅርቡ “የጋሞ” ማንነታቸውን ጥለው የሌላ ብሔር ማንነት እንደሚጎናፀፉ መገመት አይከብድም ብሏል።

ምክንያቱም እሳቸው ለጥቅማቸው ሲሉ የአማራነት፣ የጎፋነት እና የጋሞ መለያ ለብሰው የተጫወቷቸው ጨዋታዎች ለዚህ ግልፅ ማሳያ መሆናቸው ተጠቁሟል።

አሁን አሁን የራሱን ብሄር ማንነት በመቀየር ከሁሉም ወገን ተቋውሞ የገጠማቸው ጥሌን (ቲጣሬን) በድጋሚ በየትኛው ብሄር መለያ እንጠብቅ ?