በጎፋ ዞን የ3 ወር የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ገንዘብ የገባበት ባለመታወቁ በአከባቢው ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን የኦይዳ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች የ2 ወራት የ2016 ዓ.ም. እና የ1 ወር የ2017 ዓ.ም. ውዝፍ ደመወዝ ጥያቄያቸው ሦስተኛ ዓመቱን መያዙን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ( WT Media ) ገልጿል።
ሠራተኞቹ ያቀረቡት ቅሬታ እንደሚያመለክተው፣ የጠቅላላ 235% የሚሆን ውዝፍ ደመወዛቸውን “ማን እንደበላ፣ ወዴት እንደገባ ወይም ምን እንደዋጠው የሚያስረዳንን አካል” ጭምር እንዳጡ ገልጸዋል።
የኦይዳ ወረዳ መንግሥት ሠራተኞች ለሦስት ዓመታት ያህል በተደጋጋሚ የወረዳውን መንግሥት ቢጠይቁም ሆነ ቢለምኑም፣ ውዝፉን ለመክፈል ብዙ ቦታ እየተሯሯጡ እንደሆነና “እንከፍላለን” የሚል “ሰማይ ላይ ላም አለ” ዓይነት ተስፋ ብቻ ተሰጥቷቸዋል።
ወረዳው በየትኛውም መንገድ ለመክፈል ይችላል በሚል ተስፋ ሠራተኛው በዕለት ተዕለት ወደ ወረዳው አስተዳደር እየገባ ቢጠይቅም፣ እስከዛሬ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ድረስ በቂ ምላሽ እንዳላገኙና የውዝፍ ደመወዝ ጥያቄያቸው በፍጹም እንዳልተመለሰ ገልጸዋል።
በዚህ የተነሳ የኦይዳ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ውዝፍ ደመወዝ ጥያቄያቸው ሦስተኛ ዓመት በያዘበት ዕለት፣ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ለሚመለከተው አካልና በተለይም ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ አቅርበዋል።
ሠራተኞቹ “ይህ የደመወዛችን ጥያቄ ይመለከተኛል የምል የሕዝብ ኃላፊነት የሚሰማው እና ሹመቱ ከክርስቶስ የሆነ ለዜጋው የሚያስብ ካለ” በማለት፣ የኦይዳ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጥያቄ እንዲመለስላቸው በጽኑ ጠይቀዋል።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media