የህዳሴው ግድብ የውኃ ሙሌት በዓባይ የውኃ መጠን ላይ ተፅዕኖ አለመፍጠሩን ሱዳን ገለጸች

የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በዓባይ የውኃ መጠን ላይ ተፅዕኖ አለመፈጠሩን የሱዳኑ አል-ሩሳሬስ ግድብ ዋና ዳይሬክተር ሐሚድ ሞሐመድ ዓሊ አስታወቁ።

ሐሚድ ሞሐመድ ዓሊ እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ብትጀምርም በጥቁር ዓባይ የውኃ ፍሰት ላይ የጠብታ ያህል እንኳን ልዩነት አልታየም ብለዋል።

“በኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚገኘው አል-ዴይም ጣቢያ ከፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር ጀምሮ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በሚፈስሰው የውኃ መጠን ላይ አንዲትም የጠብታ መቀነስ አዝማሚያ አላገኘም” ነው ያሉት።

የግድቡ ሁለተኛ የውኃ ሙሌት እየተከናወነ ቢሆንም በየዕለቱ ወደ ሱዳን የሚፈስሰው የውኃ መጠን አለመቀነሱን ነው የገለጹት።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ የውኃ ሙሌት ብታከናውንም የግድቡን የውኃ ሙሌት እና አሠራር በተመለከተ አሁንም ቢሆን ሕጋዊ እና አስገዳጅ ስምምነት መፈረም አለበት ሲሉ መናገራቸውን ሽንዋ ጠቅሰው ኢቢሲ ዘግቧል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1 በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 12/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹