1000081156

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፌዴራልን ከፍተኛ ፍርድቤት ትዕዛዝ በድጋሚ በመጣስ ባለሀብቱ ኢንጂነር ብርሃንመስቀል ክንፈን ወደ ችሎት እንዳይሄዱ ከልክሏል።

ትዕዛዙን ለማስፈጸም ደብደቤ ይዘው የመጡ የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት፣ የክልሉ ባለሥልጣናት “ትዕዛዝ አንቀበልም” በሚል ባሳዩት እምቢተኝነት በመከልከላቸው ባለሀብቱን ይዘው መሄድ ሳይችሉ በሳውላ ከተማ ለቀናት ከተንከራተቱ በኋላ ትዕዛዙን ሳያስፈጽሙ ወደ ፌዴራል ተመልሰዋል።

የክልሉ መንግሥት በወጣት ባለሀብቱ ኢንጂነር ብርሃንመስቀል ክንፈ ላይ የዘረጋውን የፖለቲካ ሴራ ለመሸፈን ሲል፣ ባለሀብቱን በአካል ቀርበው ሁኔታውን እንዲያስረዱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ ትዕዛዙን ይዘው የመጡ የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት ሳያስፈጽሙ ወደኋላ መመለሳቸውን WT Media ከታማኝ መረጃ ምንጮች ለማረጋገጥ ችሏል።

ይህ አሳሳቢ የሕግ የበላይነት መጣስ በክልሉ ውስጥ ያለውን የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ቀውስ ምን ያህል እንደሰፋ የሚያሳይ ሲሆን፣ የፌዴራል ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ደብዳቤ በ WT Media እጅ ደርሷል።

ከዚህ ቀደም በኢንጂነር ብርሃንመስቀል ክንፈ ጉዳይ ላይ በክርክር ሂደት ላይ ባለ የማዕድን ቦታ ላይ የጥቅም ተጋሪ ባለሀብቶችን ያስገባውን ክልል ለማገድ የፌዴራል ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ የክልሉ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ለሕግ ተገዢ ባለመሆናቸው ትዕዛዙ ሳይፈጸም ቀርቷል።

በዛሬው ዕለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኢንጂነር ብርሃንመስቀልን ከጎፋ ሳውላ ማረሚያ ቤት ወደ አዲስ አበባ ችሎት እንዲመጡ የሰጠውን ትዕዛዝ ይዘው የመጡት የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት፣ የክልሉ ባለሥልጣናት “ትዕዛዝ አንቀበልም” በሚል በመከልከላቸው ባለሀብቱን ይዘው መሄድ ሳይችሉ በሳውላ ከተማ ለቀናት ከተንከራተቱ በኋላ ትዕዛዙን ሳያስፈጽሙ ወደ ፌዴራል ተመልሰዋል።

ጉዳዩ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ሁኔታ፣ የክልሉ መንግሥት አመራሮች በአቶ ጥላሁን ከበደ መሪነት በኢንጂነር ብርሃንመስቀል ላይ ተመሳሳይ ክስ መክፈቱ፣ የሕግ አሠራርን የሚጥስና ሥልጣንን አላግባብ የመጠቀም ድርጊት መሆኑ ተደጋግሞ ተጠቁሟል።

ክልሉ ይህን ድርጊት የሚፈጽመው የባለሀብቱን የማዕድን ሥራ ሕገወጥ ለማስመሰልና ከክልሉ አመራሮች የሙስና ሰንሰለት ጋር የተያያዘውን የፖለቲካ ሴራ ለመሸፈን መሆኑን WT Media በዘገባዎቹ ሲገልጽ ቆይቷል።

የክልሉ አመራሮች በኢንጂነር ብርሃንመስቀል ላይ የተዛባ መረጃና የሐሰት ምስክርነት በማቅረብ ባለሀብቱን እያሰቃዩ ሲሆን፣ የዎላይታ ተወላጅ የነበሩ የሕግና የምርመራ አመራሮችን ከሥልጣን በማንሳት በሌሎች የስርቆት ጥቅም ተጋሪ አመራሮች መተካት የሙስናውን ሽፋን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራር በሕግ የበላይነት ላይ ያሳየው እምቢተኝነትና ተደጋጋሚ የሥልጣን ጥሰት፣ በክልሉ ያለውን የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ቀውስ በጥልቀት የሚያሳይ ነው። ፍትሕን ከፌዴራል መንግሥት የሚጠብቀው ባለሀብቱ፣ የክልሉ አመራሮች የፌዴራልን ትዕዛዝ አለመቀበል እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ፣ WT Media የፌዴራል መንግሥት በአስቸኳይ ጣልቃ በመግባት ሕገወጥ ድርጊቱን እንዲያስቆም እና የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብር በድጋሚ አበክሮ ይጠይቃል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media