የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺ 442ኛው ኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አረሳችሁ ብለዋል።
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ከሀይማኖታዊ እሴት በተጨማሪ በህዝቦች መካከል አንድነትና አብሮነትን ከሚያጠናክሩ በዓላት ውስጥ አንዱ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።
በዓሉ የሚከበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በተጠናቀቀበት ማግስት በመሆኑ ለዚህ ድርብ ደስታ ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ እንደ ከዚህ ቀደም የተቸገሩትን በመርዳትና በመደጋገፍ በዓሉን እንዲያሳልፍ ዶክተር እንድሪያስ ጥሪ አቅርበዋል።
የቀድሞ አባቶቻችን በሐይማኖት፣ በዘር፣ በጎሳ ሳይለያዩ በክብር ያሰረከቡንን ሀገር ፈጣሪ በሠላም እንዲጠብቅልንና የአሁኑ ትውልድ ሀገር ወዳድ እንዲሆን የእምነቱ ተከታዮች ዱዋ ወይም ፀሎት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በዓሉ የሠላም የፍቅር የደስታ እና የአንድነት እንዲሆን ያላቸውን ምኞት በራሳቸውና በዞኑ አስተዳደር ስም በድጋሜ ገልጸዋል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1 በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 12/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
