በዎላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የአሸባሪውን ህወሃት ጥቃቱን ለማወገዝ እና ለመከላከያ ሰራዊቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚገለጽ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የሰልፉ ዋና ዓላማ “ከአሸባሪው ህወሃት የተቃጣብንን ትንኮሳንና ግጭት፤ ዕድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናት ለጦርነት የመመልመሉ ተግባር ማውገዝ እና ለመከላከያ ሰራዊቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመገለጽ” እንደሆነ ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እየመከተ ላለው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ ለመገለጽ እንደሆነም ታውቋል፡፡
በዚህ ታርካዊ ሰልፉ ላይ ከዞኑ ከሁሉም ወረዳ/ከተማ አስተዳዳር የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብለው ይጠበቃል፡፡
በነገው ዕለት ታላቅ ሰልፍ ላይ ሁሉም አካላት እንድትሳተፉ የዎላይታ ዞን አስተዳደር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 13/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
