የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ትዕዛዝ ለመፈጸም እምቢ ብለው የርዕሰ መስተዳድሩን ህገወጥ ትዕዛዝ የተቀበሉት ምክትል ኮማንደር እንዴት በማግስቱ በፕሬዝዳንቱ ኮሚሽነር ሆኑ የሚለው የህግ ጥያቄ ማስነሳቱ ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል – የቀድሞዋ የሳውላ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ የነበሩት ምክትል ኮማንደር ብርትኳን መንግስቱ በክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽነርነት የተሾሙት አቶ ጥላሁን ከበደን በማገልገልና ህገወጥ ትዕዛዛቸውን በመፈጸም እንደሆነ WT Media ተጨማሪ መረጃዎችንና ሰነዶችን ለማግኘት ችሏል።



ይህ ሹመት በተለይ ወጣቱ ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈን በማሰቃየት ሂደት ውስጥ በግልጽ የተፈጸመ የፖለቲካ ሴራ መሆኑ ተጠቁሟል።
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጣስ
ምክትል ኮማንደር ብርትኳን መንግስቱ አሁን ላገኙት ሹመት ዋናው ‘መስፈርት’ የሆነው ድርጊታቸው፣ የፌዴራሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመቀበል ነው።
በቀን 14/02/2018 ዓ.ም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት ያዘዘውን ትዕዛዝ ለመቀበል ፍቃደኛ አልሆኑም።
ከዚህም አልፈው፣ “የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የማያውቁት ትዕዛዝ ነው” በሚል ምክንያት የፌዴራሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ላለመቀበል ደብዳቤ ጽፈዋል።
ይህም ከአቶ ጥላሁን ጋር ተመሳጥራና ተመካክራ በህግ የበላይነት ላይ የተፈጸመ ሴራ መሆኑን ያመለክታል።
- የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ የማዘግየት ድራማ አቶ ጥላሁን ከበደ አስተዳደር በኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ የመሰረተው የ12 ቢሊየን ብር ክስ እንደማያዋጣቸው፣ እንዲሁም ክቡር ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪውን በነፃ እንደሚያሰናብት መረጃ ደርሷቸው ነበር። በዚህ ጊዜ አዳማ ስልጠና ላይ የነበሩት አቶ ጥላሁን ለሳውላ ማረሚያ ተቋም አዛዥ ለምክትል ኮማንደር ብርትኳን መንግስቱ ደውለው ኢንጂነር ብርሃነመስቀልን ከጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3 ሰዓት ላይ ከነበረው ችሎት እንዳታቀርበው ቀጭን ትዕዛዝ ሰጡአቸው።
ኢንጂነሩ ከችሎቱ ነፃ የወጣው ከሰዓት በኋላ 9:30 ላይ ችሎት ሲቀርብ ነበር። ይህ መዘግየት የተደረገበት ምክንያት ደግሞ፣ ሴረኛው ጥላሁን ከጋሞ ዞን በሌላ የተፈበረከ የሐሰት ክስ መጥሪያ የያዙ ፖሊሶች ከአርባምንጭ ተነስተው ሳውላ ሳይደርሱ ከማረሚያ እንዳይወጣ የተቀመረ ስለነበር ነው።

ኢንጂነሩ ነፃ እንደወጣም የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘው በመምጣት ወደ አርባምንጭ አጓጉዘውታል።
- የሹመት ዋጋ እና የፖሊስ ዶክትሪን መጣስ
ምክትል ኮማንደር ብርትኳን ያገኙት የኮሚሽነርነት ሹመት “ከጥላሁን ጋር የገቡበት ያልተቀደሰ ጋቻ” መሆኑን WT Media በቂ መረጃና ማስረጃ ደርሷል።
በአዲሱ የፖሊስ ዶክትሪን መሰረት ባለ ዝቅተኛ ማዕረግተኛ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖችን መምራትም ሆነ ማዘዝ የማይቻል ቢሆንም፣ በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ይህ ሹመት ተፈጽሟል።
“ኮሚሽነሯም ቅርብ ወራጅ ናቸው” በሚል የፖለቲካ ሴራው መጨረሻው ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ተተንብዮአል።
ይህ ሹመት የአቶ ጥላሁን ከበደ ህገ ወጥ ትዕዛዝ በመቀበላቸው የተከፈላቸው ወሮታ መሆኑ ተነግሯል።
አስተያየት ሰጪዎች፣ ምክትል ኮማንደር ብርትኳን አንድ ዓመት እንኳን የሚሞላ የአመራርነት ልምድ የሌላቸው እና ግዙፍ ተቋምን የመምራት ብቃት የላቸዉም ብለዋል።
ከፖሊስ የሥነ-ምግባር አሠራር ውጪ፣ ልምድ ያካበቱና ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸውን ኮሚሽነሮች፣ ምክትልና ረዳት ኮሚሽነሮችን ሽቅብ ተንጠራርታ እንድትመራ መፈቀዱ፣ “ከሌብነትና በጥቅም መተሳሰር የመጣ፣ የርዕሰ መስተዳድሩን ዕውቀት አልባነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
- የበቀል ሰንሰለት ቀጥሏል
ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ላይ በቅርቡ የተመሰረተው የ53 ሺህ ብር ክስ፣ ለቀድሞ የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጩቱሎ የግል ጥቅም ለማስገኘት ሞክሯል በሚል ነው።
በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የነበረው የፖሊስ አባል የዋስትና መብቱ ተከብሮለትና ክሱ ተቋርጦ በዲሲፕሊን ቅጣት አልፎ ሲበቃ፣ ኢንጂነሩ ግን ሌብነታቸውንና ዝቅጠታቸውን ስላጋለጠባቸው ከሳውላ ማረሚያ ቤት ወደ አርባምንጭ ማረሚያ ቤት ተዛውሮ እየተሰቃየ ይገኛል።
ዛሬም እንጠይቃለን፣ እውነትን ይዞ በመጋፈጡ ያለ ጥፋቱ ታስሮ ለሚሰቃየው ብርሃነመስቀል ክንፈ ፍትህ! ፍትህ! ስንል እንጮሃለን የበርካቶች ድምፅና ጥሪ ነው።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media