photo_2025-12-07_15-49-00

ይህ ጽሑፍ በዎላይታ ታይምሰ ሚዲያ (WT Media) የተዘጋጀ ሲሆን፣ በተለያዩ ምሁራዊ ጽሑፎች እና አካዳሚያዊ ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ የቀረበ ነው። ጽሑፉን ለማዘጋጀት በዋናነት ጥቅም ላይ የዋሉ የመረጃ ምንጮች የሚከተሉትን ምሁራን ስራዎች ያካትታሉ፡

በዛሬዉ ጋሞ አስተዳደር ዞን ዉስጥ በሚገኙ ተራራማ ኮረብታማ እና ረባዳማ አከባቢዎች (የጋሞ ደሬዎች) የሚኖሩ የተለያዩ ባህል፤ ቋንቋ፤ ታሪክ እና ማንነቶች የነበራቸዉን በርካታ ነባር ሕዝቦች ጨፋላቂዉና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ስትራቴጂ በመከተል የሚታወቀዉ የአብሲኖ-ኢትዮጵያ መንግስት ገዥዎች በጥቅሉ ‹‹ገሙ›› [ጋሞ] በሚባል ስቴሪዮቲፒክ ስም ይጠሩ ነበር፡፡ ከአሁኑ ጋሞ ዞን በተጨማሪ የራሳቸዉ ብሄር ማንነት ታሪክና ባህል የነበራቸዉን የጎፋ፤ የቁጫ እና ቦሮዳ ህዝቦችንና አገራቸዉን አንድ ላይ አካቶ የሚይዘዉ ክፍለሀገርም ገሙ-ጎፋ[ ጋሞ ጎፋ ] ተብሎ ይጠራ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ፡፡ 

እኤአ ከ1991 ጀምሮ በአገሪቱ ሕገመንግስታዊ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ገብራዊ ሲደረግም በአሁኑ የጋሞ ዞን ዉስጥ የሚገኙ የየራሳችን ባህል ታሪክ ቋንቋ? Varieties? አገር እና ብሔራዊ ማንነት አለን/ ጋሞ አይደለንም ብለዉ የሚያምኑ በርካታ ነባር ሕዝቦች -(ለምሳሌ ዶርዜ፤ቁጫ፤ቦሮዳ እና ኦቾሎ) በአንድ ለላይ ተጨፍልቀዉ ጋሞ የሚባል ብሄራዊ ማንነት ተሰጣቸዉ፡፡ ህገመንግስታዊ ህብረብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ከተተገበረበት ማግስት ጀምሮ እነኚህ ነባር ህዝቦች ጋሞ በሚባል አርቲፊሻል ማንነት መጨፍለቃቸዉን በመቃወም በተለይም ዶርዜ፤ቁጫ፤ ቦሮዳ በህገመንግስቱ መሰረት የብሄር ማንነታችን እና self rule እንዲከበርላቸዉ በተቀናጀና ባልተቀናጀ መልኩ ሰላማዊ ትግል ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡ 

ህብረብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ከተተገበረበት ማግስት ጀምሮ አንዳንድ Gamo-centric ጽንፈኛ ብሄረተኖች-ልህቃንና ፖለቲከኖች በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ነባር ህዝቦች የሚያነሱትን የማንነት ይታወቅልን፤ ሴልፍ ሩል መብታችን ይከበርልን ጥያቄ በማፈን/በመጨፍለቅ አንድ ወጥ የጋሞ ብሔራዊ ማንነት እና ጋሞን ማዕከል ያደረገቨ አስተዳደር ለመገንባት ተግተዉ ይሰሩ ነበር፡፡ አሁንም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Linguistics and Philology ትምህርትና ምርምር ዘርፍ ስመጥር ፕሮፈሰር እና እና ፖለቲከኛ -ቀደም ሲል የኢፌዲሪ  ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴሪ፤ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና የስራና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፈሰር ሂሩት ወልደማርያም አካዳሚክ ፊልድ ዎርክ በማድረግ በዋነኝነት ከቀዳሚ የመረጃ ምንጮች (primary sources) ሰብስበዉና International Journal of Sociology and Anthropology) በሚል ታዋቂ አካዳሚክ ጆርናል እኤአ 2013 ዓ/ም ባሳተሙት informative academic article entitled as ‘’Revisiting Gamo: Linguists’ classification versus self identification of the community’’ 

ሀ/ ከወታደራዊ መንግስት ጀምሮ የሚባል የወል መጠሪያ  ስም እየተሸሻለ የመጣ መሆኑን ከገሙ ወደ ጋሞ/Gammo በኋለም አንዳንድ Gamo-centric ብሄረተኞች/ ፖለቲከኞች መጠሪያዉን ከጋሞ-ወደ “Gaammo‟ (በጋሞሶ አንበሳ ) መቀየራቸዉን ገልጸዋል፡፡ 

ይሁን እንጂ የዞኑን ህዝብ „Gaammo -አንበሳ በሚል የወል ስም የመጥራት ፖለቲካ ፕሮጄክት ሁሉን አቀፍ ቅቡልነት ማግኘት አልቻለም ነበር፡፡ Critics of the name “Gaammo‟ argued that the word invokes ideas of a wild beast and of wildness, not something that a people should want to be associated with.

በሰሜን ኦሞ አከባቢ በሚገኙ mutually intelligible languages ለመጀመሪያ ጊዜ ሊንጉዊስቲክ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ስመጥር ምሁራን (Bender, 1976; Fleming, 1976; Bender, 2000) በአከባቢዉ ነባር ሕዝቦች የሚነገሩ የጋሞ፤ ዳዉሮ፤ኮንታ እና ዶርዜ ቋንቋዎች የዎላይታ/የዎላይታቶ ቋንቋ ዘዬዎች/ dialects ብለዉ ደምድመዋል፡፡ ይሁን እንጂ በጣም አብዛኛዎቹ Gamo-centric scholars and nationalists በጋሞ ደሬዎች የሚኖሩት ነባር ህዝቦች Gaammo እንጂ ዎላይታ አይደሉም፤ እንደዚሁም Gamotso ራሱን የቻለ ቋንቋ ነዉ፡፡ የዎላይታቶ ቋንቋ ዘዬ ወይንም variety አይደለም፡፡ብለዉ ይከራከራሉ፡፡ 

ለሊንጊዊስቲክ እና ዲሞግራፊክ አናሳዎች ቋንቋ የማንነታቸዉ ዋነኛ መገለጫ ነዉ፡፡ አነርሱ ቋንቋ ነዉ ብለዉ የሚያምኑትን vernacular የአንድ ሌላ ቋንቋ ዘዬ/ዲያሌክትስ ነዉ ብሎ መገለጽ ብሄራዊ ማንነታቸዉን እንደማሳነስ/ማዋረድ ብሎም ባህላቸዉን ቋንቋቸዉንና ማንነታቸዉን ለማጥፋት የሚደረግ በፖለቲካ የተለወሰ አካዳሚክ ትርክት ነዉ በማለት ዉድቅ ያደርጉታል፡፡ አጥብቀዉ ይቃወሙታል፡፡ Cognizant of the negative socio-political implications of using linguistic  dialect upon linguistic and ethno-linguistic minorities linguists specifically linguistic anthropologists have tended to use neutral concepts such as linguistic varieties, linguistic clusters and parental languages.

ስለሆነም Gamo-centric elites, politicians and nationalists Gamotso /ጋሞኛ ከዎላይታቶ ቋንቋ ዘዬዎች/ dialects መካከል አንዱ ነዉ ብለዉ (Bender, 1976; Fleming, 1976; Bender, 2000) መግለጻቸዉን አጥብቀዉ መቃወማቸዉ ከኤትኖ-ሊንጊዩዊስቲክ ፖለቲካ አንጻር ትክክል ነዉ፡፡  

ይሁን እንጂ የፕሮፈሰር ሂሩት ወልደማሪያም ጥናት ዉጤት በአሁኑ የጋሞ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ደሬዎች/መንደሮች የቋንቋ፤ የባህል እና የማንነት ብዝሃነት የሚስተዋል መሆኑን በጋሞ ደሬዎች/መንደሮች የሚኖሩት አብዛኞቹ ህዝቦች ለምሳሌ ዶርዜ ዳጬ ኦቾሎ ጋንታ ቁጫ ቦሮዳ ካምባ ቦንኬ ከየራሳቸዉ መኖሪያ ስፍራ/መንደር ስም ጋር የተጣጣሙ ወይንም የተናጋሪዎች/የመኖሪያ አከባቢያቸዉ መገለጫ የሆኑ አብዛኛዎቹ several mutually intelligible dialects/ዘዬዎችን የሚናገሩ መሆናቸዉን Gamotso /ጋሞኛ አይደለም ራሱን የቻለ ወጥ ቋንቋ ሊሆን ይቅርና  homogenous linguistic variety አለመሆኑ ታዉቋል፡፡

ምንም እንኳን ጋሞቶ ራሱን የቻለ ቋንቋ ባይሆንም ብሎም በጋሞ ደሬዎች የሚነገሩ በርካታ የተለያዩ ዲያሌክትስ ወላጅ ቋንቋ/ወጥ ሊንጊዩዊስቲክ ዘዬ ባይሆንም እንኳን በዞኑ ዉስጥ የጋሞ ዘዬ ለማስፋፋት እየተሞከረ ይገኛል፡፡ 

ጋሞቶ ዲያሌክት በኦቾሎ፣ ጋንታ፣ ቁጫ፣ ቦሮዳ እና ዶርዜ ከሚነገሩት Omotic linguistic varieties ጉልህ  ልዩነት አለዉ፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች, እነዚህ ሊንጊዩዊስቲክ ልዩነቶች ወደ አለመግባባቶች ሊመሩ ይችላሉ. ለዚህ አንዱ ምሳሌ የሚሆነው ጋሞ እንደ ማስተማሪያ ቋንቋ ሲጠቀም ነው። እንደ ማስተማሪያ ቋንቋ ጥቅም ላይ ሲዉል ነው። የመግባቢያ ችግሮች እና አለመግባባቶች ብዙውን ጊዜ የሚከሰቱት በመምህራን እና በተማሪዎች ዘዬ እና በመማሪያ መጽሃፉ ውስጥ ጥቅም ላይ በሚውለው ቋንቋ ልዩነት ምክንያት ነው።

በሂሩት (2007 221) ላይ እንደተገለጸው፣ የመምህሩ dialect ንግግር ጠንቅቀዉ የማያውቁ በመሆናቸዉ ተማሪዎች አንድን ትምህርት ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው። ተማሪዎቹ የሚጠቀሙትን የጋሞቶ ዲያሌክት ባለመረዳታቸው ብቻ መምህራኖች የተማሪዎችን ፈተና የቤት ስራ  በትክክል የማይገመግሙ መሆናቸዉን ቅሬታ ያሰማሉ። ከትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ተማሪዎች የተማሪዎቹን ቀበሌኛ ስላልተረዱ መምህራን ብዙውን ጊዜ የፈተና ወረቀቶቻቸውን በስህተት ደረጃ ይሰጣሉ ብለው ያስባሉ፡፡ 

በተጨማሪም አንዳንድ ተማሪዎች የሚጠቀምበት ጋሞቶ-ዲያሌክት ቃል ከጋንታ ማህበረሰብ አካባቢ ለመጣ አስተማሪ የተከለከለ taboo የሚሆንበት በርካታ ክስተቶች ተስተዉለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ መሳቅ እና መምህሩን ለታላቅ ግራ መጋባት የሚዳረጉበት፤ ምቾት ማጣትና ሀፍረት ተሰምቷቸዋል።

የሆነ ሆኖ በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች የጋሞ የተለያዩ ዘዬዎች ተናጋሪዎች ባለሁለት ብሄረሰብ ማንነትን ሪፖርት የሚያደርጉ መሆናቸዉን አንዳንድ ጥናቶች ያመላክታሉ። በሌላ አነጋገር አብዛኛዎቹ የጋሞ ደሬ/ቀበሌ ማህበረሰብ አባላት በመጀመሪያ እራሳቸውን እንደ ጋሞ ደሬ ህዝብ ቀጥሎ ራሳቸዉን ዶርዜ ፣ ኦቾሎ ፣ ዳጬ ፣ ጋንታ ፣ ወዘተ ነን ብለዉ ይገልጻሉ፡፡ በሌላ አነጋገር የጋሞ ደሬ ህዝብ ማንነታቸውን እና የትንሹን የቋንቋ ቋንቋ ቡድናቸውን እውቅና በመስጠት ድርብ የማንነት ስሜት ያሳያሉ። ሁለቱንም ማለትም የጋሞ ደሬ አከባቢ የጋርዮሽ ማንነት እና በመኖሪያ አከባቢያቸዉ/መንደራቸዉ/ታሪካዊና ባህላዊ ማንነት አጣምረዉ ይጠቀማሉ፡፡ ለአብነት የዳጬ ማህበረሰብ አባል፣ “እኔ ዳጬ ነኝ እንደዚሁም ግን ጋሞ ነኝ” ይላል።

ይሁን እንጂ ይህ ሁልጊዜ በሁሉም ቡድኖች ውስጥ ላሉ ሁሉም አባላት የሚሰራ አይደለም፡፡ የብሔር/ኤትኒክ ማንነት ምስረታ ተለዋዋጭ ሂደት እንደመሆኑ መጠን፣ አንዳንድ የጋሞ ዴሬስ (መሬቶች) አባላት ባህል ታሪክ ኤትኖጄኔሲስ ጋር የተያያዘ ነገር ግን  latent ሆኖ የቆየ ኤትኒክ ድንበር ለመገንባት /ተናጠል ethnic orientation እና ወይንም ፖለቲካዊ መንስኤዎች ወይም ስትራቴጂክ ፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት ቀዳሚዉን የቡድን ማንነታቸውን በማጉላት የጋሞ የጋራ ማንነታቸውን ውድቅ ሲያደርጉ  ይታያሉ። 

ለአብነትም ከ2000ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የጋሞ ደሬዎች ነባር ህዝቦች መካከል አንዱ የሆነዉና ማህበረሰቡ በስፋት ከሚኖርበት ደሬ መጠሪያ ስያሜ ጋር የተያያዘ ዘዬ ተናጋሪ የሆነዉ የዶርዜ ማህበረሰብ  አንዱ የሆነው ዶርዜ በህገመንግስቱ መሰረት የብሄር ማንነቱ እና ሴልፍ ሩል መብቱ እንዲከበርለት እየታገሉ/እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡ በተለይም የቁጫ  እና የቦሮዳ ማህበረሰቦች በቋንቋ፣ በታሪክ፣ በባህል በመልከዓምድራዊ አቀማመጥ ከጋሞ ዴሬ እና ጋሞ ከሚባል አርቲፊሻል ማንነት ፈጽሞ የተለዩ እንደሆኑ አጥብቀዉ ይከራከራሉ። በዚህም ምክንያት በኢፌዲሪ ህገመንግስት መሰረት ኤትኖ-ሊንጊዊስቲክ ማንነታቸዉ ተረጋግጦ ከጋሞ ጎፋ ዞን በመገንጠል ወይንም በጋሞ ዞን አስተዳደር ስር የራሳቸውን ልዩ የወረዳ አስተዳደር መዋቅር ለመመስረት ጠንካራ ሰላማዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ትግል አድርገዋል፡፡ እየታገሉም ይገኛሉ፡፡ 

ፕሮፌሰር ሂሩት በአካዳሚክ አርትክሏ የገለጸቻቸዉ መሰረታዊ ነጥቦች ቀደም ሲል Dena Freeman (2006) Who are the Gamo? And who are the D’ache?:  በሚል አካዳሚክ አርቲክል ያቀረቧቸዉን ተጨባጭ ሀሳቦች ያጠናክራል፡፡ ሁለቱ ፕሮፈሰሮች ተጨባጭ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ተንትነዉ ካቀረቡት ገለጻ የጋሞ ብሄር ማንነት በተመለከተ ሶስት  መሰረታዊ ነጥቦችን ነቅሰን ማዉጣት እንችላለን፡፡

1ኛ/ ጋሞ የሚባል የህዝብ ጋራ መጠረያ ስያሜ ከአጼዉ ዘመነ መንግስት ጀምሮ እየተቀያየረ የሚገኝ መሆኑን እና፤ Gamo-centric elites, politicians and nationalists በተለይም ከ19990ዎቹ ጀምሮ በፈበረፈኩትና በስፋት ጥቅም ላይ አየዋለ በሚገኘዉ Gaammo -አንበሳ በሚል የጋራ መጠሪያ ስያሜም ቢሆን ወደ ሁሉን አቀፍ መስማማት/መግባባት ያልተደረሰ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

2ኛ/ በዛሬዉ የጋሞ ዞን ወጥ ብሄራዊ ማንነት፤ ወጥ ቋንቋ፤ ባህልና ታሪክ የሌለ መሆኑን ይልቁንስ በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ነባር ሕዝቦች በዋኘኝነት ዶርዜ፤ ቁጫ እና ቦሮዳ በህገመንግስቱ መሰረት የተናጠል ኤትኖ-ሊንጉዊስቲክ ማንነታቸዉ እንዲታወቅላቸዉ እና ራሳቸዉን በራሳቸዉ የማስተዳደር መብታቸዉ እንዲረጋገጥላቸዉ በቀናጀና ባልተቀናጀ መልኩ እየታገሉ መሆናቸዉን እንገነዘባለን፡፡

3ኛ/ የጋሞ ሴንተግሪክ ማንነትና እና ጋሞን ማዕከል ያደረገ አስተዳደራዊ ስርዓት ግንባታ ከ1999ዎቹ ጀምሮ ማቆጥቆጥ መጀመሩን መገንዘብ እንችላለን፡፡ 

Gamo-centric elites, politicians and nationalists በጋሞ ደሬ እና በዞኑ መስተዳድር ስር መልከዓምድር ዉስጥ የሚገኙትን ነባር ህዝቦችን ባሕል ታሪክ ቋንቋ እና የተናጠል ማንነት ደፍጥጠዉ/ጨፍልቀዉ አንድ ወጥ የጋሞ ማንነት/ባህል/ቋንቋ ጋሞን ማዕከል ያደረገ የአስተዳደርና ፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ተግተዉ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢፌዲሪ ሕገመንግስት ድንጋጌዎች መሠረት የብሔር ማንነት እና self governance መብታችንና ነጻነታችን ይከበርልን የሚል-የዶርዜ፣ ቁጫ እና ቦሮዳ ሕዝቦችን ሰላማዊ ህዝባዊና ፖለቲካዊ ትግል እንቅስቃሴ የተለያዩ ጸረ ሕገመንግስታዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለማፈንና ለመደፍጠጥ ተግተዉ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ጽንፈኛ Gamo-centric elites, politicians and nationalists በዋኝነት ከጸረ ዎጋጎዳ ትግል እና የሰሜን ኦሞ ዞን ከፈረሰበት ማግስት ጀምሮ ዎላይታ-ጠል የፖለቲካ አጀንዳዎችን/ፕሮፓጋንዳዎችን ከማራገብ የተቆጠቡበት ጊዜ የለም። የዎላይታ ልህቃን ብሎም ዎላይታ እንደ ሕዝብ የጋሞ ሕዝብ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብትና ነጻነት ደንቃራ/latent enemy ናቸዉ የሚሉ የፈጠራ ትርክቶችን በየሕዝባዊ መድረኩ እና በተለያዩ ማህበራዊ እና ኢሌክትሮኒክ ሚዲያዎች አቀንቅነዋል፣ እያቀነቀኑ ይገኛሉ።

በዎላይታ ሕዝብ ላይ ክብረ ነክ ስድቦችን እና የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ማራገብ፣ ምናባዊዉንና ጨፍላቂዉን የጋሞ ብሔር ማንነት እና አስተዳደር ክልል ግንባታ ለማረጋገጥ እንደ ወሳኝ ስትራቴጂ አድርገዉ ሰርተዋል፣ እየሰሩም ይገኛሉ። በሁለቱ ሕዝቦች መካከል በመከባበር፣ በመቻቻል፣ በመተሳሰብና ትብብር ላይ የተመሰረተ ሕብረብሔራዊ አንድነት መገንባት አስፈላጊ ስለመሆኑ የዎላይታ ልህቃን ሲያንጸባርቁ የነበሩትን ምክንያታዊ አስተያየቶችን ማብጠልጠልና፣ የተሳሳተ ፖለቲካ ትርጉም መስጠት የጽንፈኛ ጋሞ ብሔረተኞች የአዘቦት ተግባር ነበር።

የዶርዜ ሕዝብ ባሕላዊ ቅርስና የማንነታቸዉ መታወቂያ ምልክት የሆኑትን የሽመና ስራ ዉጤቶችን ቀምተዉ/ሰርቀዉ የጨፍላቂዉን አንድ ወጥ ጋሞ ብሔር ማንነት መገለጫ ነዉ ብለዉ የሚለብሱና የሚያስተዋዉቁ ስግብግብ ጽንፈኛና ተንኳሽ የጋሞነት ፖለቲካ ብሔረተኞች ሰፊዉን ታሪካዊ ባሕላዊ እና አስተዳደራዊ ድንበር አልፈዉ የብሔረ ዎላይታ ባሕላዊ ቅርስ እና የብሔራዊ ማንነቱ ምልክት የሆነዉን ዱንጉዛ ሃዴ እና የዱቡሻ ባህላዊ ስርዓት ሰርቀዉና ቀምተዉ የጨፍላቂዉና አዳጊዉ ጋሞ ብሔር ባሕላዊ ቅርስና ማንነት ምልክት ለማድረግ መደበኛ ዞናዊ እየተጠቀሙ መሆናቸዉ ቸል ተብሎ ሊታለፍ የማይገባ ጉዳይ ነዉ።

እነ ሳዲቃ ስሜን የመሳሰሉ የባሕልና ቅርስ ቀበኞች  የዎላይታ ዱንጉዛ ሐዴ የአዳጊዉ ጋሞ ብሔር ማንነት መጠለጫ ቅርስ ነዉ እያሉ ዘወትር በመደበኛ እና ኢመደበኛ ፕላትፎርምስ አማካኝነት የሚያራግቡት የበሬ ወለደ ዉሸት ትርክት (አይዲኦሎጂ ) ከጊዜ ቆይታ በኋላ እዉነት ሆኖ የመታየት  ዕድል  ለማጨናገፍ ብሎም በዎላይታ ጥንታዊ አገርበቀል ሽመና እና ዱንጉዛ ሃዴ መሠረታዊ ግንዛቤ ለሌላቸዉ ወገኖች ይረዳ ዘንድ በተጨባጭ ማስረጃና ማስረጃ የተደገፈ አጭር ማብራሪያ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።

የዎላይታ ዱንጉዛ ሐዴ

ድንጉዛ ሐዴ ስለሚባለዉ ባህላዊ የዎላይታ ልብስ ከማዉራታችን በፊት ስለ ዎላይታ አገርበቀል የሽመና ቴክኖሎጂ አጭር ምልከታ ማድረግ አለብን፡፡ 

በተለያዩ ተጓዦች እና ታሪካዊ ዘገባዎች መሠረት የዎላይታ መንግሥት ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ በተለይም በግብርና ልማት ውስጥ እጅግ የላቀ የሥልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስላል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ዎላይታ የተራቀቀ ድብልቅ የሰብል-የእንስሳት እርባታ ያዳበረ ሲሆን በርካታ የተለያዩ አገርበቀል ሰብሎችን – ሥራሥሮችን እንሰትን ጨምሮ፤ ጥራጥሬዎች፣ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ ቅመማ ቅመሞች፣ ጥሩ መዓዛ ያላቸው እፅዋት (ሳውማታ)፣ ቡና እና ጥጥ  እና የተለያዩ የቤት እንስሳትን – cattle, small ruminants, equines and local species of chicken ለፈርጀ ብዙ ጠቀሜታቸዉ በስፋት ያመርትና ያራባ ነበር፡፡ 

ከ1894 በፊት የነበረው የዎላይታ ማህበረሰብ ከተደባለቀ የሰብል-የእንስሳት ምርት በተጨማሪ በንግድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሰዎች የተለያዩ ትርፍ ምርቶችን ወደ ሩቅ ቦታዎች እና ማህበረሰቦች የረጅም ርቀት የንግድ መስመሮች በመባል በሚታወቀው ስርዓት ወደ ውጭ ይላኩ ነበር። በተጨማሪም ዎላይታ ከጥንት ጀምሮ የብረት ማቅለጥ፣ የሸክላ ስራ፣ ቆዳ፣ ቅርጫት እና ሽመናን ጨምሮ የላቀ የአገሬው ተወላጅ የእጅ ጥበብ ቴክኖሎጂን አዳብረዋል ተብሏል።

የዎላይታ ህዝብ ከብዙ መቶ ዘመናት ጀምሮ የዘለቀ አገርበቀል የእጅ ሽመና ባህል አለው። ስቲግሊዝ ወላይታ ከሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች በፊት የሽመና እና የጥጥ ጨርቅ የመልበስ ጥበብን የተካነ መሆኑን ጠቁመዋል። እንደዚሁም ዎላይታ በባህላዊ እና ጥበባዊ ወጎቹ ለምሳሌ በጨርቅ ማቅለም ይታወቅ ነበር። ልክ እንደ ብዙ የምዕራብ አፍሪካውያን፣ የጨርቅ ማቅለሚያ በልዩ ችሎታ ይለማመዱ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ።

አገርበቀል ሽመና በዎላይታ ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው በባህላዊ ባለ ሁለት ፔዳል የእጅ መንሸራተቻዎች ላይ ነው። የእጅ ሥራው በዋናነት በወንዶች የሚለማመድ ሲሆን በተለምዶ ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ ሲሆን ወጣት ወንዶች ልጆች ቀስ በቀስ ከትላልቅ ሰዎች ኢመደበኛ በሆነ መንገድ ይማራሉ/ይሰለጥናሉ፡፡ በአገርበቀሉ የሽመና ስራ ወንዶች እና ሴቶች የሚሳተፉ ሲሆን አብዛኛዉን ጊዜ ወንዶች በዋናዉ ሽመና ስራ፤ የሸማ ዉጤቶችን በማቅለም እና በመስፋት ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን ሴቶች ደግሞ ጥጥ በመፍተል እና ማስጌጥ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ 

መጀመሪያ ላይ በዎላይታ ውስጥ ሽመና በዋነኛነት የተገነባው ለዕለት ተዕለት ኑሮ እና ሥነ ሥርዓቶች አስፈላጊ የሆኑ ቡሉኩና እና የተለያዩ የሃዲያ ዓይነቶችን ጨምር የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትን ለማምረት ነበር። ቡሉኮ የዎላይታ ሴቶች በየዕለቱ እና እንደ ሰርግ እና መሰል ፌስቲቫሎች የሚለብሱት ባህላዊ ልብስ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ቡሉኮ እንደ ብርድ ልብስ የሚያገለግል ባህላዊ የመኝታ  ልብስ ነዉ፡፡ 

በአገርበቀል የሽመና ቴክኖሎጂ ዉጤቶች /ምርቶች /ባህላዊ አልባሳት መካከል አንዱና ዋነኛዉ ሃዲያ ነዉ፡፡ በ13ኛዉ ክፍለዘመን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ታላቁን የዎላይታን ንጉስ ሳሶ/ሳቶ ሞቶሎሜ በዳሞታ ተራራ ላይ በሚገኘዉ የፖለቲካና አስተዳደር ማዕከላቸዉ(ጣዛ ጋሯዋ)  አሳምነዉ በሚያጠምቁበት እና ጥንታዊዉን የቅዱስ ስላሴ ቤተክርስቲያን በሚያስገነቡበት ወቅት ንጉሱ ባለሟሎቹ እና የአከባቢዉ ሕዝብ ከተፈተለ ጥጥ ተሰርቶ በደማቂ ቀለም ያሸበረቀ ባህላዊ ሱሪ /ሃዲያ ይለብሱ እንደነበር የጥናት ዉጤቶች ያመላክታሉ፡፡ 

የዎላይታ ሸማኔዎች በዕድሜ ቦታና በማህበራዊ ስታታስ አንጻር ተለይተው የሚለበሱ የብሄሩ የሚስጥር ምልክት ከሆኑ ቀይ ጫና ጥቁር ቀለማት ያሸበረቁ አምስት የተለያዩ የሃዲያ ዓይነቶችን ሴሬ ሀዲያ፤ ዱንጉዛ ሃዲያ፣ ጎሞራ ሃዲያ፣ ጉቱማ ሃዲያ፤ እና ፓታላ ሃዲያ ተብለዉ የሚጠሩትን ያመርታሉ፡፡

1ኛ/ ዱንጉዛ ሃዲያ 

ይህ ሃጁ ከአምስቱ የሃዴ አይነቶች አንዱ ሆኖ በቀይ፣በበጫ ቀለማት መካከል በሚያልፍ ጥቁር አራት ጎናዊ ዝግዛግ ሐዲድ አሸብርቆ የሚሰራ እና እንደ ዘመናዊ ሱሪ የሚለበስ አና ከላይ (xxxabbiyaa) “ጠቢያ የሚባል ማሰሪያ የሚገባበት ቀዳዳ እንዲኖረው ተደርጎ ይሰራል። ይህ ሃዱ አይነት በብሄሩ ዘንድ የብሄራዊ ክብር ማንነትና አንድነት መገለጫ ምልክት  ሆኖ ይታወቃል።

ዱንጉዛ ሃዴ ከንጉሱ ጀምሮ ታላላቅ ማዕረግየነበራቸው፡- ካም፣ በሻሻ፣ የምቤዎች፣ ዱቢያዎች፣ ጉዳች። ባልሞናዎች፣ ሚዳዎች፣ ሞጮናዎች አራሾዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ ዳናዎች እናቶቢያዎች በስልጣን የሚስተካከላቸውብቻ  የሚለብሱት የክብርና የማዕረግ ልብስ እንደሆነ ይታወቃል። 

2ኛ/ ሴሬ ሃዲያ

ሴሬ ሃዲያ በቅርጹ ካልሆነ በስተቀር በዲዛይን/ይዘት/ሳይዝ እና ቀለም ከዱንጉዛ ሃዱ ጋር ተመሳሳይ የሆነና የጦር መሪዎች፣ጀግናዎች፣ፈረሰኞች እና የአደን መሪዎች የሚለብሱት የሃዲያ ዓይነት ነው።

3ኛ/ ፓታላ ሃዲያ 

ፓታላ ሀዴ ደግሞ በሃብት ማብሰሪያ ጊዜ የሚለብሱት ”የሟ ልብስ ሲሆን ትልቅ የክብር ልብስ ሆኖ እላይ ከተጠቀሱት ዱንጉዛ ሃዴ እና ሴሬ ሀዳ ጋር በመልክ ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ሲሆን ነገር ግን ልዩነቱ ውሃ ሰማያዊ እና ነጭ በጥለቱ ላይ መጨመሩ እና የቅርጽ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አሰራሩ ከላይ እስከ ታች ወጥ ሆኖ እንደ ክብ ካባ ከላይ የሚጠልቅ ነው። 

በተጨማሪም ከሱ ጋር አብረው የሚለበሱ ምጎሩዋ-ሴቶች በጊሟዋ ሥርዓት ወቅት በራሳቸው ላይ የሚያስሩት እንደ ዘምባባ የሚቆም ጫፎች ያሉት ጌጥሞ ጉምቧ ዘንግዋ የሚባል የእግር ጌጥ ሳጋዩዋ ሻማጪያ የሚባል መደረቢያ ሎቲያ የሚባል ከዛሊያ /የዚሆን ጥርስ የሚሰራ የጆሮ ጌጥ ምግዷ የሚባል የሚባል የጣት ቀለበት ይገኙበታል።

4ኛ/ ጎሞራ ሃዲያ፡

ይህ ከአምስቱ የሃጄ ዓይነቶች አንዱ ሲሆን ወንዶች ተገርዘው ለማህበራዊ ክብር ሲበቁ የሚለብሱት የሃዴ ዓይነት ነው። ለወንዶች ግርዛት ማለትም የማህበራዊ ህይወት ሸግግር ምልክት በመሆኑ ለዚህ ከብር የመብቃት ማብሰሪያ ልብስ ደግሞ ጎመራ ዘዴ ይባላል።

5ኛ/ ጉቱማ ሐዴ፡

ጉቱማ ሃዲ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሥራ ወቅት የሚለብሰውና አምስተኛው የሃዱ ልብስ አይነት ሆኖ ዲዛይን ሳይለቅ የሚሰራ እና ለማድመቅም ብዙ ጌጣጌጥ እና ዲዛይን ያልተጨመረበት ሀዴ አይነት ነው፡፡ 

የዎላይታ ሃዲያ ከላይ ወደ ታች ዙሪያዉን ከተለያዩ የዕጽዋት ቅጠሎች ቅርፊቶችና አበቦች፤ ከቀይ አፈር እና ከሰል ተቀምመዉ በተዘጋጁ ቀይ፤ ብጫ እና ጥቁር ቀለማት ያሸበረቀና በጥንቃቄ ተሰፍቶ የተዘጋጀ woven cotton ባህላዊ ልብስ፤ የዎላይታ ሕዝብ ጀግንነት፤ብሄራዊ አንድነትና ማንነት መገለጫ ምልክት  ነዉ፡፡

በተጨማሪም የአገርበቀል ሽመና ቴክኖሎጂ/ስራ ዉጤት የሆኑትንና ከተፈተለ ጥጥ የተሰሩ በርካታ የተለያዩ ምርቶችን በዋነኝነት ቡሉኳ፤ ሻሏዋ፤ካሬታ ሲና የመሳሰሉትን ይጠቀም ነበር፡፡ ካሬታ ሲና ማረጯ የተባለ ከብረት የተሰራ መገበያያ ገንዘብ ለአገልግሎት ከመዋሉ በፊት እንደ መገበያያ ገንዘብ ያገለግል ነበር፡፡ 

በሌላ በኩል ዎላይታ በርካታ የተለያዩ የጥጥ ሽመና ስራ ዉጤቶችን buluko, shaluwa, karetta and traditional cloths of both male and female with various age groups ወደ ደቡብ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች በረጅም ርቀት ንግድ መስመር አማካኝነት ኤክስፖርት ያደርግ እንደነበር በበርካታ የተለያዩ አካዳሚክ ጥናትና ምርምር ስራዎች ተመዝግቧል፡፡

የጽሑፉ ዝግጅት ምንጭ

ይህ ጽሑፍ በደብሊውቲ ሚዲያ (WT Media) የተዘጋጀ ሲሆን፣ በተለያዩ ምሁራዊ ጽሑፎች እና አካዳሚያዊ ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ የቀረበ ነው። ጽሑፉን ለማዘጋጀት በዋናነት ጥቅም ላይ የዋሉ የመረጃ ምንጮች የሚከተሉትን ምሁራን ስራዎች ያካትታሉ፡

ስለ ጋሞ

– Hirut Woldemariam Revisiting Gamo: Linguists’ classification versus self identification of the community. International Journal of Sociology and Anthropology Vol. 5(9), pp. 373-380, December, 2013 

– Dena Freeman (2006) Who are the Gamo? And who are the D’ache?:  Confusions of Ethnicity in Ethiopia’s Southern Highlands In Uhling, Siebert (Ed). 2006. Proceedings of the 15th International Conference of Ethiopian Studies. Wiesbaden: Harrassowitz Verlag

ስለ ዎላይታ 

– Abbink (2006).Reconstructing Haberland  Reconstructing  the Wolaita: The History and Society of  A Former Ethiopian Kingdom. History in Africa. 33: 1-15

– Asela,Gujebo.(2004 E.C.). Early Wolaitta and Kafa.Addis Ababa: Artistic Pertaining Press.

– Berhanu, Bibiso.(1995). “Production Practices in Wolaita of Southern Ethiopia: The case of Damot Woide”. MA, Social Anthropology, Addis Ababa University. 

– Bisrat,  L.( 2016). “Prophets and prophecy as a response to crises:Prophet Esa in the traditional religion of Wolaitta (1920-1928)”. African Journal of  History and Culture, vol. 8(6),52-59.

– Balisky, Paul.(2009). Wolaita Evangelists: A Study of Religious Innovations in Southern 

Ethiopia, 1937-1975.Eugene,USA: Pickwick Publications.

– Chiatti, Remo.(1984). “The Politics of Divine Kingship in Wolaita (Ethiopia) in the 19th and 20th Centuries”. Ph.D. Dissertation, Pennsylvania. 

– Deresse, L.(1999). “Social History of Wolaita”. MA Thesis, Department of History,  Addis Ababa University, Addis Ababa. 

– Demisse Moja(2019) THE COUNTRY OF THREE THOUSAND YEARS OF CIVILIZATION: WOLAITA OR ETHIOPIA?. Asian Journal of Social Sciences, Arts and Humanities Vol. 7, No. 1, 

– Stigand CH (1969). Travel To Abyssinia Through An Unknown Land. NewYork: Negro University Press.

ጽሑፉ የተገኘውን መረጃ ጠቅልሎ በማደራጀትና አቀራረቡን በማስተካከል ለሕትመት እንዲበቃ በዎላይታ ታይምሰ ሚዲያ (WT Media) ተዘጋጅቷል።