1000085876

“ከድንጉዛ ጋር ያለው ውዝግብ እና የጥላሁን ከበደ ስውር እጅ” የ WT Media ጥልቅ ትንታኔ – ነፃ ሀሳብ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክልሉ ከተመሰረተ ማግስት ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ 32 ብሄር ብሄረሰቦችን እርስበርስ እንዲባሉ በማድረግ የተለያዩ ስውር አጀንዳዎችን በመስጠት የሚፈፀሙ ሌብነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ኢፍትሃዊነት፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች፣ የእርዳታ ገንዘብ ጭምር ዝርፍያ፣ ከህግ እና አሰራር ውጪ ተግባራት በመፈፀም ላይ እንደሚገኝ WT Media በመረጃ እና በማስረጃ በማስደገፍ እያጋለጠ እንደሚገኝ ይታወቃል። በተለይም ደግሞ ዎላይታን ለማዳከምና የስልጣን ስግብግብ ፍላጎት ለሟሟላት ዎላይታ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎችን እያነሳ ህብረተሰቡ በዋናው አጀንዳ ላይ ትኩረት እንዳያደርግ እያደረገ ይገኛል።

ለአብነትም 👇

  1. ዎላይታ ውስጥ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ማዘግየትና ህዝቡ በቁጣ ተነስቶ ከመንግስት ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ሆኖም ህዝቡ ነገሩን በጥበብ እየተከታተለ በሰለጠነ መንገድ በደሉን ለመንግስት በመግለፅ እየተከታተለ ይገኛል።
  2. ከሲዳማ ጋር የቆየ ቁርሾ እንዲቀሰቀስ በማድረግ የዎላይታን ዋና አጀንዳ አስረስቶ ወደ ተጓዳኝ አጀንዳ እንዲዞር ማድረግና የስልጣን ግዜ መግዣ በሲዳማ ፅንፈኛ ዎላይታን ድንበር ዘልቀው ገብተው ሲገድሉ ነገሩ እንዲፋፋም እንደ ክልል መንግስት መግለጫ ማውጣት ሲቻል ዝምታ መምረጥና ገለልተኛ ሆኖ መቀመጥ ይህ ጉዳይ ህዝቡ አምርሮ ወደ ለየለት ጦርነት እንዲገባ ማድረግ ይህንንም በጥበብና በበሳል አእምሮ በዝምታ ህዝቡ መከታተሉ እረፍት ነስቶታል።
  3. ከአጆራ ፏፎቴ ጋር ግልፅ ነገር እያለ በአወዛጋቢ መንገድ ዞሮው የዎላይታን ድንበር ተሻግረው ግጭት ፈልገው ሲመጡ ክልሉ ማውገዝና መግለጫ ማውጣት ሲገባው ዝምታ መምረጥና ዎላይታዊያንን ወደ ለየለት ጦርነት ለማስገባት ሌላ የተጠነሰሰ አጀንዳ መክሸፉ አሳዝኖታል።

It is list but not last ብሎ የመጨረሻው የጋሞ ህዝብ የድንጉዛ ጥያቄ የራሳቸው አለመሆኑን ስላወቁና ይህንን የእኛ እንዲሆን ወረቀት ስጡን ብሎ መጠየቅ ይህንን ደግሞ ከወንድም ጋሞ ህዝብ ጋር ወደ ግጭት ለመክተት ያሴረው ሴራ መጨረሻ ማብቂያ የሌለው ጥረቱ አሁንም ዞኑ በፃፈው ደብዳቤ ሊደናቀፍ ችሎአል። ይህ ጉዳይ በድብቅ አልቆ ቢሆን ኖሮ ለጥላሁን ስልጣን ማረዘሚያ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ይቀር ነበረ ይላሉ WT Media በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገራቸው ምሁራን።

በመጨረሻም ድንጉዛ ባለቤቱ የራሱ እንደሆነ አለምምም ስለሚያወቅ አለም የራሱን ነገር የእኔ አድርጉት የሚል ጥያቄ ዎላይታ አይጠይቅም ዳምታን የዎላይታ ነው ወረቀት ስጡኝ ብሎ እንደማይሄድ ሁሉ ድንጉዛንም እንደዛው ስለሚያወቅ ነው ዝም ያለው ጋሞ ሳይሆኑ በጋሞ ስም የተደበቁ ፅንፈኛ ፋኖዎች ይህን ለማድረግ ከአቶ ጥላሁን አጀንዳ ወስደው ቢሄዱም አልተሳካላቸውም።

የራሱ ሀብትና ቅርስ እውቅና ስጡ ብሎ ዎላይታ አይሄድ ሄዶም አያውቅም ሌቦች ግን የራሳቸው እንዳልሆነ ልባቸውም ታርካቸውም ስለሚነግራቸው “ሌላ ምስክር ወረቀት ስጡኝ አሉ” ይገርማል።

የሊቨርፑል ወይም የአርሴናል ማልያውን ከእንግሊዝ ውጪ አሜርካን ወይም ቻይና ሀገር በይበልጥ ቢለበስ ማለያው የኢንግሊዝና የሊቨርፑል ክለብ እንጂ በብዛት ስለሰሩ ስላመረጡ በብዛት ዜግቻቸው ስለለበሰ የራሳቸው አርማ አድርገው የቻይናውያን ወይም የአሜርካዊያን ማለያ ነው አለም ይወቅ ቢሉ አይቻልም።

ባያስመዘግቡትም ማለያው የኢንግሊዛዊያንና የሊቨርፑል ማለያ ወይም አርማ ነው እንዲያም የዎላይታ ድንጉዛ ጋሞ ቢሸምነውም ቢለብሰውም ታርካዊ አመጣጡን ጨምሮ አለባበሱ አጠቃቀሙም በታሪክም በሰነድና በሰው ማስረጃ የተደገፈ የዎላይታ ነው ዎላይታ የራሱ የሆነን ነገር የእኔ ነው ብላችሁ ወረቀት ስጡ አይልም!

በመሆኑም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክልሉ ከተመሰረተ ማግስት ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ 32 ብሄር ብሄረሰቦችን እርስበርስ እንዲባሉ በማድረግ የተለያዩ ስውር አጀንዳዎችን በመስጠት የሚፈፀሙ ሌብነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ኢፍትሃዊነት፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች፣ የእርዳታ ገንዘብ ጭምር ዝርፍያ፣ ከህግ እና አሰራር ውጪ ተግባራት በመፈፀም ላይ ስለመሆኑ በፌዴራል መንግስት ጭምር መረጋገጡ ተከትሎ የፖለቲካ ሜዳ ሽንፈትን ለመደበቅ በየወቅቱ የሚያመጣው አጀንዳ መሆኑን ስለሚታወቅ በዋናው ጉዳይ ትኩረት መደረግ አለበት እንላለን።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media