ምርመራዘገባ #ሰበር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ ዞን አመራሮች ከክልሉ አመራሮች ጋር በመመሳጠር ከእርዳታ ድርጅት በእርዳታ የተሰጠውን ተጨማሪ 46 ሚሊዮን ብር ሕገወጥ በሆነ መንገድ ማወዳደቃቸው ተነግሯል።
በጎፋ ዞን ከንቾ አካባቢ የተከሰተውን የናዳ አደጋ ተከትሎ ለተጎጂዎች የተሰበሰበው ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የእርዳታ ገንዘብ፣ በዞን አመራሮች ተጨማሪ የ46 ሚሊዮን ብር ምዝበራ ከመፈጸሙም በላይ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በዚህ ሕገወጥ ድርጊት ውስጥ ስለመኖራቸውም ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሐምሌ 2017 ዓ.ም. በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው አሰቃቂ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ263 ሰዎችን ሕይወት ማለፉ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

ይሁን እንጂ፣ አደጋውን ተከትሎ በሕይወት የተረፉትን መልሶ ለማቋቋም ከዓለም አቀፍ ተቋማት የተሰበሰበው ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን የእርዳታ ገንዘብ በዞንና በክልል አመራሮች አማካኝነት በዘመድ አዝማድ ሴራ መመዝበሩና መጥፋቱ ታውቋል።
WT Media በሰነድና በሰው መረጃዎች በተደገፈ መረጃ፣ ከአደጋው በሕይወት የተረፈው የከንቾ ሕዝብ በራሱ “በገዛ ልጆቹ” እንደተወጋ አረጋግጧል።
በጎፋ ዞን የተከሰተው የመሬት መንሸራተት፣ መጀመሪያ ሦስት ሰዎች ሲወሰዱ ሰምተው ለእርዳታ የሄዱ 260 የመንደሩ ነዋሪዎችን በአንዴ በመዋጥ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሮ ነበር። የሟች ቤተሰቦች “አባቴን አሳዩኝ! እናቴን!” የሚል ዋይታና ጩኸት አሰምተው፣ ቤቶች ሰው አልባ ሆነው ቀርተዋል።
ይህንን ዘግናኝ ሁኔታ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ቦታውን በመጎብኘት በሕይወት ለተረፉት መልሶ ማቋቋሚያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ለግሰዋል።
ሃብታት ፎር ሂውማን (Habitat for Humanity) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሕይወት ለተረፉት 88 ግለሰቦች ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ለመገንባት 46,200,92.40 ብር መድቦ ነበር።
ውሉ የተገባው ጥቅምት 2017 እስከ ሰኔ 2018 ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ሲሆን፣ የጎፋ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ በበላይነት እንዲመራ ተስማምቶ ነበር። በተጨማሪም ዞኑ 19 ሚሊዮን ብር ማችንግ ፈንድ ለመመደብ ቃል ገብቶ ነበር።
የጎፋ ዞን አመራሮች ዞኑ መመደብ ያለበትን ገንዘብ ከመተው ባሻገር፣ ድርጅቱ በእርዳታ የሰጠውን 46 ሚሊዮን ብር ሕገወጥ በሆነ መንገድ አወዳድቀውታል ተብሏል።
አመራሮቹ በሕጋዊ መንገድ የግንባታ ግብዓት ከመግዛት ይልቅ፣ በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለተጎጂዎች መልሶ ማቋቋሚያ በእርዳታ የተሰጠ የግንባታ ግብዓት ከገዜ ጎፋ እንዲወሰድ አድርገዋል።
በዚህ ሕገወጥ አካሄድ፣ “ባልተገዛ ግዥን የተገዛ በማስመሰል” ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ አወዳድቀዋል።
አመራሮቹ እርዳታውን ለግል ጥቅም ለማዋል ቤተሰባዊ አደረጃጀት በመዘርጋት ግፍ ፈጽመዋል።
የአደጋ ስጋት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ ለክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋምአ አቤልጅ ናቸው።
የከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ የነበረው አቶ ሀብታሙ ፈተና ደግሞ ለዋና አስተዳዳሪው የክርስቲና ልጅ ነው።
ይህንን ጉዳይ በባለሙያነት የመራው አቶ ይሁን የተባለው ግለሰብ ለመምሪያ ኃላፊው የእህቱ ልጅ ሲሆን፣ ጉዳዩን እንዲያስፈጽም ከሳውላ ማዘጋጃ በውሴት ወደ ዞን የተወሰደ ነው።
WT Media ከዚህ በፊት የእርዳታ ገንዘብና ቁሳቁስ በተደራጀ መንገድ መመዝበሩን መዘገቡ ይታወሳል።
በተለይም በቅርቡ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለእርዳታ ከተሰበሰበው ገንዘብ ከባንክ ለማውጣት ሲሞክር ግለሰቡ እና ሌሎች ተባባሪ አመራሮች መታሰራቸውንም በተደጋጋሚ ዘግቧል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ሌላ አሳዛኝ ድርጊት ፈጥሮ፣ ያለ ወላጅ የቀሩ ሕፃናትና ያለ ቤተሰብ የቀሩ አረጋውያን አሁንም ቆዝመው፣ ብቻቸውንና እየተራቡ እንደሚገኙ መረጃው ያመለክታል።
የከንቾ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የተለገሰው ሀብት በዞኑ ውስጥ የጥቂት አመራሮች ሕይወት ማበልፀጊያ ሆኖ መቅረቱ ለዘላለም ላይፋቅ ታትሟል።
WT Media ከዚህ ቀደም በዘገባቸው ላይ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብና ቁሳቁስ ለተጎጂዎች ሳይደርስ በአመራሮች ተመዝብሯል እንዲሁም ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለማውጣት ሲሞክር አመራሮች መታሰራቸውን ገልጾ ነበር።
ወደ 1 ቢሊዮን ብር የሚጠጋው የእርዳታ ገንዘብ ኦዲት ሳይደረግለት ዝም መባሉ፣ እንዲሁም 46 ሚሊዮን ብር በግልጽ ከተመዘበረ በኋላ እንኳ ተገቢው እርምጃ አለመወሰዱ፣ በክልሉ የሕግ ተጠያቂነት አለመኖሩን በግልጽ ያሳያል።
የሰብአዊ ቀውሱን ለመፍታት ከሀገር ውስጥና ከውጪ ለጋሾች የተሰበሰበው ገንዘብ፣ በተደራጀ አመራር አማካኝነት ለግል ጥቅም መዋሉ የከንቾን ሕዝብ ቁስል በእንጨት እንደወጋው ነው ሲሉ የአከባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።
ሃብታት ፎር ሂውማን የተባለው ድርጅት ሊገነባ የነበረው 88 ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ሳይገነባ ቀርቷል፤ ያለ ወላጅ የቀሩ ሕፃናትና ያለ ቤተሰብ የቀሩ አረጋውያን አሁንም ቆዝመውና እየተራቡ እንደሚገኙ መረጃው ያመለክታል።
የፌዴራል መንግሥት የሚሊዮኖች ብር የእርዳታ ገንዘብ መመዝበርን እና በዚህ ሴራ ውስጥ የተሳተፉ አመራሮችን በተመለከተ አስቸኳይ እና ግልጽ ኦዲት እንዲያካሂድ፣ እንዲሁም ተጠያቂዎችን ለሕግ እንዲያቀርብ በጥብቅ ተጠይቋል።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media