1000087460

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በቅርቡ አርባምንጭ አቅራቢያ ባለው ሀይቅ ለሽርሽርና ለመዝናኛ የተገዛችሁ አነስተኛ ጀልባ “በኦነግ ሼኔ” ታግታ መወሰዷን ምንጮች ለ WT Media አስረድቷል።

እንደ መረጃው ከሆነ ጀልባዋ ታግታ በምትወሰድበት ዕለት አባያ ሀይቅ ላይ ለጉብኝት በሚል ከአዞ እርባታ በላይ በኩል መሀል ባለች ደሴት በመመላለስ ከእዛ በኃላ ደሴቲቱን አልፋ ለመዞር ስትሞክር ታግታለች ተብሏል።

ጀልባዋ ታግታ በምትወሰድበት ወቅት በውስጡ የነበሩ ሰዎችም ታግተው የነበሩ ቢሆንም በድርድር ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውና ጀልባዋን ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱም ተገልጿል።

“ጉዳዩን የጋሞ ዞን እና ልማት ማህበሩ እያወቀ እስካሁን በምስጢር መያዛቸው ግራ የሚያገባ እንደሆነ አላውቅም” ሲል የWT Media መረጃ ምንጭ አስረድቷል።

የመረጃ ምንጩ ጀልባዋን ያገተው ማነው የሚል ጥያቄ ቀርቦለት “በተለይም በነጭሳር ፓርክና አከባቢው የምንቀሳቀሰው ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ሲል ገልጿል።

WT Media ጉዳዩን ለማጣራት ከጋሞ ዞን አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ሌላ ምንጭ እንደሚጠቁመው ከሆነ ዞኑ ጀልባዋን ከታጣቂዎች ለማስመለስ ድርድር መጀመሩን ለመስማት ችለናል።

ይህቺ ባይራ የተሰኘች 30 ሰው የምትይዘው አነስተኛ ጀልባ ከአዞ ራንች አባያ ሃይቅ ጀምሮ ወደ ሞጬ ደሴትና ነጭ ሳር ዜብራ መንደር እንዲሁም ወደ ከስር አንዱ የፑራ ደሴቶች ከዛም መዳረሻውን ግዲቾ ባይሶ እና ሺግማ መንደር እንዲሁም እስከ ዲላ ድረስ እንቅስቃሴ ለማድረግ የታቀደ ቢሆንም በኦነግ ታግታ ተወሳዳለች ተብሏል።