GridArt_20251220_174902847

ልዩ #የምርመራዘገባ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሌሎች የክልሉ አመራሮች ከቢሮ ወደ ቢሮ፣ ከክላስተር ወደ ክላስተር ዝውውር ሲደረግላቸው የተወሰኑት አመራሮች ግን ክልሉ ከተመሰረተ ጀምሮ የርዕሰ መስተዳድሩ አይነኬ የማይሻሩ፣ የማይዘዋወሩ፣ የማይገመገሙና የማይነኩ አመራሮች ሆነው መቆየታቸው ቅሬታ አስነስቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርባምንጭ ክላስተር ማዕከል ተደርገው የተመደቡ የክልል ቢሮዎች፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደ የቅርብ ሰዎች መጠቅለላቸውንና ለክልሉ ስብጥር የማይመጥን የዘመድ አዝማድ አደረጃጀት እንደተዘረጋባቸው ከፍተኛ አመራሮችና የፖለቲካ ተንታኞች ለ WT Media አጋልጠዋል።

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ በተለይ ገቢ፣ ንግድ፣ ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም የመሬት ቢሮዎች የአንድ ብሔር የበላይነት የሰፈነባቸውና የርዕሰ መስተዳድሩ “የገቢ ምንጭ” ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

  1. “አይነኬዎቹ” እና ከአርባምንጭ የማይነቀሉት አመራሮች

ሌሎች የክልሉ አመራሮች ከቢሮ ወደ ቢሮ እንዲሁም ከክላስተር ወደ ክላስተር (ወደ ዎላይታ ሶዶ፣ ጂንካና ሀዋሳ) ዝውውር ሲደረግላቸው፣ በአርባምንጭ የተመደቡት የተወሰኑ አመራሮች ግን ክልሉ ከተመሰረተ ጀምሮ “አይነኬ” ሆነው መቆየታቸው ቅሬታ አስነስቷል።

አቶ ብርሃኑ ዘውዴ (የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ)፦ ክልሉ ከተመሠረተ ጀምሮ በቦታው ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅትም ሆነ አሁን ክልሉን “እየበጠበጡ” ይገኛሉ ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።

ወ/ሮ ዓለምነሽ ደነቀ (የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ)፦ ለአቶ ጥላሁን ከበደ ዋነኛ “የገቢ ምንጭ” በመሆን የገንዘብ ድጋፍ (ድጎማ) የሚያደርጉ በመሆናቸው፣ ክልሉ ከተመሠረተ ጀምሮ ከአርባምንጭ ሳይነሱ እንዲቆዩ ተደርጓል ተብሏል።

አቶ ሰብስቤ ቡናቤ (የመሬት ቢሮ ኃላፊ)፦ በጋሞ ዞን አሁን ለተፈጠረው የፀጥታ ችግርና አለመረጋጋት “ዋነኛ ተዋናይ” ናቸው በሚል ተከስሰዋል።

  1. የብሔር ተዋፅኦ መጣስና የቅጥር ምዝበራ

በአርባምንጭ ክላስተር የሚገኙ አራት ዋና ዋና ሴክተሮች (ንግድ፣ ገቢ፣ ከተማ ልማትና መሬት) የክልሉን ሕዝብ ስብጥር የማይወክሉና የአንድ ብሔር የበላይነት የታየባቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

የዳይሬክቶሬት ቦታዎች መያዝ፦ ምንም እንኳ እንደ ዎላይታ ሶዶና ዲላ ያሉ ከተሞች ለክልሉ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገቡ ቢሆንም፣ በገቢዎች ቢሮ ውስጥ ያሉ ቁልፍ የዳይሬክቶሬት ቦታዎች በሙሉ “ለጋሞ ተወላጆች” ብቻ እንዲሰጡ መደረጉ ተገልጿል።

ባለሙያዎችን ማግለል፦ በአርባምንጭ ክላስተር ስር ባሉ የክልል ቢሮዎች ውስጥ ከጋሞ ውጪ ያሉ ሌሎች የክልሉ ብሔር ተወላጅ ባለሙያዎች እንዳይቀጠሩ ስልታዊ በሆነ መንገድ መከልከላቸውን መረጃ ያጋሩት ባለሙያዎች ገልጸዋል።

  1. የግጭቶች ጠንሳሽና የርዕሰ መስተዳድሩ ሚና

አቶ ጥላሁን ከበደ “አምባገነንና ሌባ” በሚል በምንጮች የተገለጹ ሲሆን፣ በአርባምንጭ ያሉትን እነዚህን ቢሮዎች እንደ ግል ንብረት በመጠቀም ክልሉን ለሥልጣን ዕድሜያቸው ማራዘሚያ እያደረጉት መሆኑ ተመልክቷል።

አርባምንጭ ላይ መመሸግ፦ በዎላይታ ሶዶና ጂንካ ያሉ አመራሮች ዝውውር ሲደረግላቸው፣ እነዚህ አመራሮች ግን በዘይሴና በቁጫ ወረዳዎች ላይ አጀንዳ እየፈጠሩና ግጭት እየጠነሰሱ ክልሉን ሰላም እንደሚነሱ ተገልጿል።

የሀብት ምንጭ፦ እነዚህ ከአርባምንጭ የማይወጡ አመራሮች ለርዕሰ መስተዳድሩ ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ በመሆናቸው፣ በግፍ ቢሮዎቹን በዘመድ አዝማድ እንዲያደራጁ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።

  1. የቀረበ ጥሪ

የክልሉን የሰው ኃይል ምደባና የአመራር ስብጥር በሚመለከት፣ በተለይ በአርባምንጭ የሚገኙትን ገቢዎች፣ ንግድና ገበያ ልማት፣ ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም የመሬት ቢሮዎች በአስቸኳይ እንዲፈተሹ ተጠይቋል።

ክልሉን የሚመስል ባለሙያና አመራር እንዲመደብ፣ እንዲሁም በብሔር ተዋፅኦ ስም የተደረጉ “ሕገ-ወጥ የዘመድ ቅጥሮች” ኦዲት ተደርገው ተጠያቂነት እንዲሰፍን የፖለቲካ ተንታኞችና ከፍተኛ አመራሮች አሳስበዋል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media