በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በምትገኘው ዘይሴ ደንብሌ ቀበሌ (ቦለዴ/ጤና ጣቢያ ሰፈር)፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፀጥታ ኃይሎች 8 ሴቶችን ከቤታቸው አውጥተው እጅግ ዘግናኝ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸው ተነግሯል።
ከ3 ቀን በፊት ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ላይ የአከባቢውን ፀጥታ ለማሰሰከበር በሚል የተሰማሩ የፀጥታ ኃይሎች የተባሉት የነዋሪዎችን ቤት ሰብረው በመግባት ስምንት ሴቶችን በልጆቻቸው በባሎቻቸው ፊት በኃይል ይዘው በመሄድ እንደደፈሯቸው ተጎጂዎችና የዓይን እማኞች ለ WT Media በምሬት ገልጸዋል።

“ከምንም በላይ ሀዘኑን በጣም ከፍ የሚያደርገው በ19/04/16 ባሏዋ በእነዚህ ፖሊሶች ተገሎባት በብቸንነት ልጆችዋን የሚታሳድግ የሟች ምስትም መደፈሯ ነው” ብሏል።
WT Media የስምንቱንም ተጎጂ ሴቶች ስም ዝርዝር ያገኘ ቢሆንም፣ ለተጎጂዎቹ ደኅንነትና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ ሲባል ስማቸውን ከመጥቀስ ተቆጥቧል።
ከተጎጂዎቹ መካከል አንዷ በደረሰባት አሰቃቂ ድርጊት ሲትገልፅ፡- “ከቤተሰብና ከልጆቼ ጋር እያለን በድንገት ከቤት አውጥተው በጫካ ውስጥ ወስደው ተጫወቱብን፤ ክብራችንን አዋርደው ለቀቁን። የሆነውን ነገር ለመናገር አቅም የለንም። መንግሥት ካለ እኛን ይጠይቅ፤ ከዚህ አሳፋሪ ነገር ያውጣን።” ብላለች።
ይህ ድርጊት በተፈጸመ ማግስት በ06/04/18 ተጎጂዎች ለሚመለከተው አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳልተሰጣቸውና ድርጊቱን የፈፀሙ ፀጥታ አካላትን በህግ ቁጥጥር ለማዋል እንዳልፈለጉም አስረድታለች።
በዘይሴ አካባቢ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ከደፍሮ መደፈር ባለፈ ቀደም ብሎም የቆየና ስልታዊ ጥቃት መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። የቤተሰብ አባላት ለ WT Media እንደገለጹት፣ የፀጥታ ኃይሎቹ ከዚህ ቀደም የሚከተሉትን ወንጀሎች ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡-
በአከባቢው “የሰውን ቤት ሰብረው በመግባት ከብቶችንና ፍየሎችን አርዶ መብላትና ጭኖ መውሰድ፣ ከቤተክርስቲያንና ከጤና ጣቢያዎች ገንዘብን፣ ቁሳቁሶችንና የማገዶ እንጨትን ሳይቀር መዝረፍ፣ አርሶ አደሮች ወደ ማሳ ገብተው ሰብል እንዳይሰበስቡ መከልከላቸውና ከማሳ ውስጥ ጥራጥሬና አትክልት ዘርፎ መውሰድ፣ ሞተርሳይክሎችንና ማንኛውንም የግል ንብረት ከሰዎች እጅ በኃይል መንጠቅ” ስለመኖሩ አስረድተዋል።
በአካባቢው የሚፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋና ደፍሮ መደፈር እንዲታረም ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ለጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃው ቢደርሳቸውም፣ ተገቢውን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ በዝምታ መመልከታቸው ተገልጿል።
እንዲያውም የዘረፋ ተግባሩን አጠናቀው ሲወጡ በፖሊስ መኪና ስንቅና ትጥቅ እየቀረበላቸው መሆኑ የአካባቢው ሕዝብ በደኅንነት ስጋት ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።
WT Media በዘይሴ አካባቢ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ይህን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በጽኑ ያወግዛል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጉዳዩን እንዲመረምሩና ጥቃት ለደረሰባቸው ወገኖች ድምፅ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።
ድርጅቶቹ ሙሉ መረጃውንና የተጎጂዎችን ዝርዝር በውስጥ መስመር በመጠየቅ ከእኛ ዘንድ መቀበል የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media