የጤና ባለሙያዎች እና የጤና ክብካቤ ሠራተኞች ሀገር አቀፍ የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም ማጠቃለያ ላይ በዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ስር የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ክብካቤ ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የኮቭድ-19 ወርሽኝ በመከላከል እንዲሁም ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስቀጠል ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእውቅና ምስክር ወረቀት እና ዋንጫ ሽልማት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ማብርከቱ ተገልጿል።
የኮቭድ-19 ወረርሽን በክልሉ ሆነ በዞኑ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች፣ ጤና ክብካቤ ሰራተኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሽታውን በመከላከል እና በመቆጣጠር ያደረጉት አስተዋጽኦ መቼም ሊዘነጋ እንደማይገባ የዞኑ ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አሳምነው አይዛ ተናግረዋል።
በቀጣይም ጤና ባለሙያዎች እና ጤና ክብካቤ ሠራተኞች ምንም ዓይነት ፈተናዎች ቢያጋጥምም እንኳ ሙያዊ ስነምግባር በተላበሰ ሁኔታ ህዝባቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉ ከዚሁ ትምህርት መወሰድ ይገባል መባሉን ከመመሪያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 18/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
