ከኮንሶ ወደ አርባ-ምንጭ መስመር በህገ ወጥ መንገድ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና በቁጥጥር ስር መዋሉን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።
የአርባ-ምንጭ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ተመስገን አንጁሎ እንደገለፁት በትላንትናው ዕለት በአርባምንጭ ከተማ በዶይሳ ቀበሌ አዲሱ ሪፈራል ሆስፒታል አከባቢ ከኮንሶ ወደ አርባ-ምንጭ መስመር ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ጭኖ ሲጓዝ በወንጀል መከላከል ፓትሮል ስራ ላይ ባሉ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ተናግረዋል።
ኮማንደሩ አክለውም ለመንግሥት መግባት ያለበትን ገቢ ሳያስገባ በህገ-ወጥ መንገድ 15 ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ፣ 1 ማዳበሪያ ቶርሽን ጫማ፣ 5 ማዳበሪያ ጥቃቅን የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ጭኖ ሲንቀሳቀስ በአርባምንጭ ከተማ በዶይሳ ቀበሌ በዶይሳ ቀበሌ አዲሱ ሪፈራል ሆስፒታል አከባቢ እንደተያዘ ገልጸው በቀጣይም ህብረተሰቡ ህጋዊ ግለሰቦችን በማበረታታትና ህገ-ወጦችን በመቆጣጠር ለፖሊስ ጥቆማ ማድረግ እንዳለባቸው መጠቆሙን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 14/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹