በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ሀንዲዳ ቀበሌ ውስጥ፣ በንጹሕ ዜጋ ላይ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸመው ተጠርጣሪ በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋሉን WT Media ከቦታው ከደረሰው መረጃ አረጋግጧል።

- የወንጀሉ ሁኔታ፦ ተጠርጣሪ ብርሃኑ በቀለ የተባለው ግለሰብ፣ ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በአንድ ግለሰብ ላይ የሰውን ልጅ ክብር በሚነካ መልኩ እጁን ወደ ኋላ በማሰር (የፊጥኝ) እና እራቁቱን በአደባባይ በመግረፍ አሰቃቂ ድርጊት መፈጸሙ ይታወሳል።
- የሕግ ሂደት፦ ተጠርጣሪው ከትናንት በስትያ የዲላ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ተጠርጣሪው ወደ ዲላ ማረሚያ ተቋም እንዲገባ አዟል።
- የሕዝብ ጥበቃ፦ ይህ አሰቃቂ ድርጊት በወቅቱ በበርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በርካቶች ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ፍትሕ እንዲሰጥና የሚሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
WT Media የዚህን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሕግ ሂደት ተከታትሎ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉን ይቀጥላል።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media
#Ethiopia #Gedeo #Dilla #HumanRights #WTMEDIA #ደቡብኢትዮጵያ #ጌዴኦ #ፍትሕ