1000093809

#ሰበርዜና፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የአንድ ሰው ህይወት በማጥፋት በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኤልያስ አለሙ ያለ መንጃ ፈቃድ የዩኒቨርሲቲውን መኪና እያሽከረከሩ በፈጠሩት የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ (WT Media) ከስፍራው ያገኘውን መረጃ አመላክቷል።

አደጋው የተከሰተው ከትላንት ወዲያ በዲላ ከተማ፣ ዲላ ትምህርት ኮሌጅ ፊትለፊት ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ ነው።

የዓይን እማኞች ለ WT Media እንደገለጹት፣ ፕሬዚዳንቱ መኪናውን እያሽከረከሩ የነበረው በከተማው ውስጥ ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ነበር።

በዚህ አደጋ አቶ ወገኔ በቀለ የተባሉ ግለሰብ ህይወታቸው አልፏል።

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ አደጋውን ካደረሱ በኋላ ለሁለት ቀናት ከአካባቢው ተሰውረው የቆዩ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ ለፖሊስ እጅ መስጠታቸውን የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ አባል አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም አደጋው በደረሰበት ወቅት በስፍራው ያልነበረው የፕሬዚዳንቱ ሹፌር ሀብታሙ አለማየሁ፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ለሁለት ቀናት በእስር ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

WT Media የሟች አቶ ወገኔ በቀለን ቤተሰቦች ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካም።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media