በትላንትናው ዕለትም በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ የሚመ የሚመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ላይ በመነጋገር ስምምነት ተደርጓል።

ስምምነቱም በዳሞታ ተራራ ላይ የቅኝት ቴሌስፖኮችን መትከል እና አስትሮኖሚካል ሳይት ማዘጋጀት፤ የዎላይታ ዞን የቱሪዝም ሳይት ካርታ ማዘጋጀት፤ በሳታላይት የታገዘ የአንበጣ መንጋ ክስተት ቅድመ ትንበያ እና መከላከል፤ ግብርናን ማዘመን እንዲሁም የህዋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እውቀት ስርጸትን ያካተተ መሆኑን ዶ/ር ሙላቱ ገልጸዋል ሲል የዩኒቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1

በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 21/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹