10 ሚሊየን ገደማ የወጣበት የጽሕፈት ቤቱ ህንጻ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የምርቃት ሥነ ስርዓቱ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ፣ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ዱባለ፣ የጋሞ ዞን አስተዳደር አቶ ብርሀኑ ዘውዴ፣ ፣ ጂ.አይ.ዜድ፣ ኤፍ.ዜድ.ኤስ፣ ኃይለማሪያም ሮማን ፋውንዴሽን በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
የምርቃት ፕሮግራም በማስመልከት በጋሞ ዞን አማካይነት በአርባምንጭ ከተማ ጉርባ ኮረብታ ላይ የችግኝ መትከያ ስፍራ ተረክቦ በአንድ ቀን 15 ሽህ ችግኞችን ተከላ የማድረግ ስርዓት በእንግዶች ተከናውነው ቀሪ ችግኞችንም የአካባቢው ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ እየተከለ ይገኛል፡፡
የፓርኮችን መሰረተ ልማት የማሟላት ሂደት በተጠናከረ ሁኔታ በሌሎቹም ብሔራዊ ፓርኮች እንደሚቀጥል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መግለፁን ከስፍራው የWT የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 24/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
