በንቅናቄ የሚመሩ ወቅታዊ ቁልፍ ተግባራት ላይ ሁሉም አካላት ሊረባረብ እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል።
በመድረኩ የመኸር እርሻ ሥራ አፈጻጸም፤የ’’ሐ’’ ገቢና ንግድ ፈቃድ ዕድሳት ሥራ፤የድንበር የሌሽ የሠላም ወጣት ምዝገባ እና የክረምት ወራት በጎ አገልግሎት ተግባራትን ጨምሮ ሌሎች የገጠር እና ከተማ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ተገምግሟል።
ተግባራት በአግባቡ እንዳይመሩና እንዳይፈጸሙ እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮች ተለይተዉ በአጭር ጊዜ ከችግሮች ለመወጣት የተደራጀ ኃይል በመጠቀም መረባረብ እንደሚያስፈልግ የዎላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ አድማሱ አወቀ ጠይቀዋል፡፡
አቶ አድማሱ አያይዘውም ተግባራትን ቆንጥጦ ከመምራት አንጻር በአመራር እና በህዝብ ደረጃ በርካታ መሻሻሎች ቢታዩም መዋቅሮችን ከማመጣጠን አንጻር የነበረዉ ክፍተት ቀጣይ መታረም እንዳለበት አሳሰበዋል፡፡
በአንዳንድ ተግባራት ላይ የታየው የተሻለ አፈጻጸም በሌሎች ተግባራት እንዲሰፋ አመራሩ ተቢውን ትኩረት ሰጥቶ ልሰራ እንደሚገባም የዎላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፎላ አሳስበዋል።
በየተቋማቱ የሚከናወኑ የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ በየወቅቱ ተግባራትን እየተገመገመ መምራት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እንዳሉ አቶ ሳሙኤል አንስተዋል፡፡
በሁሉም ደረጃ ያለው ሕዝባችን በበልግ ያጣነውን ምርት በመኸር እርሻ ልማት ስራችን ለማካካስ በተቀመጡ ዋና ዋና ግቦች ላይ ተግባብቶ በሙሉ አቅም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ አሳስቧል።
በመኸር ወቅት የአርሶ-አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በተሟላ ፓኬጅ በመጠቀም ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተቃጣውን አደጋ በማውገዝ መላው ህብረተሰብ ክፍሎችን በማነቃነቅ ውስጣዊ የሆነ ውግና ማሳየቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።
የታክስ አከፋፈሉን በሁለም አካባቢዎች ወጥና ስኬታማ በማድረግ ግብር ከፋዩ በሕግ በተፈቀደለት የሂሳብ ጊዜ ግዴታዉን እንዲወጣ ለማስቻል የተደረገው ጥረት የተሻለ መሆኑን ተገልጿል።
ተግባራት በየቀኑና በየጊዜው እየተገመገመ መሄድ እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጦ ቀጣይ ባለው ጊዜያት ተግባራትን አጠናክረው መሥራት እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመድረኩ የዎላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ አድማሱ አወቀ፤ የዎላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፎላ፤ የዞኑ አጠቃላይ አመራርና የከተማ/ወረዳ አስተዳደር አስተባባሪ አካላት መገኘታቸውን ከዞኑ ሚዲያና ህዝብ ግንኘነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 24/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹


