የዎላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ እና የዎላይታ ዞን ስፖርት ምክር ቤት ለአከባቢው ስፖርት ሁለንተናዊ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አንጋፋ ግለሰቦችና ተቋማት ዋንጫና ምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።
የዎላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ምክትል እና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አኮዬ ጌካ ረጅም አመታትን ያስቆጠረውን የስፖርት እንቅስቃሴ በተለይ የእግርና የቮሊቦል ኳስ እንቅስቃሴ ከአከባቢው አልፎ በአገር አቀፍና በአፍርካ ደረጃ እውቅና እንዲኖረው የላቀ ሚና ያላቸውን አካላት መሸለም የቆየ ውለታቸውን ማስታወስ እና አድናቆትን መግለጽ እንደሆነ በመጠቆም ላበረከቱት አስተዋፅኦ የእውቅናና የምስከር ወረቀት መስጠታቸውን ነው የተናገሩት።
ተሸላሚዎቹ በተሰጣቸው የማበረታቻ ምስክር ወረቀትና ዋንጫ መደሰታቸውን በመግለፅ በቀጣይነትም በልዩ ልዩ ዘርፎች ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ በማድረግ አከባቢው ከሌሎች ጋር በሁሉም አኳያ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ እንዲሆን እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግሯል።
አቶ ጌታቸው ጌቡ የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው በወላይታ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የላቀ ሚና ያላቸው ወጣት ባለሃብትቶች ድርጅቶችና ተቋማት ክብር እንደሚገባቸው በመጠቆም ዛሬ ላይ በአከባቢውና በአገር አቀፍ ደረጃ በታየው አመርቂ ለውጥ ላይ አሻራቸው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።
የዋንጫና የእውቅና ምስክር ወረቀት ከተሰጣቸው መካከል ወጣት ባለሃብቶች፣ ሙሴ ጳውሎስ፣ አብዲ ራዋ፣ ተሾመ ተክለ ፣ እሸቴ ታፈሰ፣ የቀድሞ የዎላይታ ዲቻ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ፣ ረ/ፕሮፌሰር አፍወርቅ አሳሌ፣ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎችም በገንዘብ በእውቀትና በማቴሪያል የደገፉት መገኘቱን የዎላይታ ዞን ስፖርት ም/ቤት ዘግቧል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 04/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹



