GridArt_20260806_205801711

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር መብራት በመግጨቱ ምክንያት በታደሰ ተሰማ የተባለ የሀዋሳ ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ ሾፌር ላይ የተጣለው ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እና የህግ አፈፃፀም ሂደት በከተማዋ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ አወዛጋቢ ሆኖ መቀጠሉ ተገልጿል።

ከሰሞኑ በተከሰተው በዚህ ድርጊት ሾፌሩ ለስላሳ ጭኖ ወደ ከተማዋ ገብቶ በነበረበት ወቅት የኮሪደር መብራት መግጨቱ ታውቋል።

ከተፈጠረው አደጋ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ ላይ የሁለት መቶ ሺህ (200,000) ብር ቅጣት ተወስኖ የነበረ ቢሆንም የፋብሪካው ፋይናንስ ኃላፊ ቅጣቱን ለመክፈል ሲሄድ “ደረሰኝ አልቋል” በሚል ምክንያት ግለሰቡ በእስር ላይ እንዲቆይ መደረጉን WT Media ከተደበዳይ ቤተሰብ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የከተማው አስተዳደር በሰጠው ማብራሪያ በሂደት ላይ በነበሩ የህግ ማጣሪያዎች እና ቀጠሮዎች ምክንያት መቆየቱን የገለጸ ሲሆን በመጨረሻም ግለሰቡ ፩ ሚሊዮን (1,000,000) ብር በመክፈል ከእስር መፈታቱን አረጋግጧል።

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ እና በህዝብ ዘንድ በተደረጉ ውይይቶች በርካታ ጥያቄዎች እና ትችቶች መሰንዘሩን WT Media ተመልክቷል።

​ከተፈጠረው ትክክለኛ ጉዳትና አደጋ አንጻር መጀመሪያ ሁለት መቶ ሺህ ብር ተብሎ የነበረው ቅጣት በድንገት ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍ ማለት ጥያቄን የፈጠረ ሲሆን ይህ አሰራር ዜጎችንና ተቋማትን ለመቅጣት እና ለማስፈራራት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እንጂ ፍትሃዊ አይደለም የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል።

​ግለሰቡ ጥፋቱን አምኖ ቅጣቱን ለመክፈል ፈቃደኛ ሆኖ ሳለ “ደረሰኝ አልቋል” በሚል ሰበብ ብቻ ለሳምንታት በእስር እንዲቆይ መደረጉ እና ጉዳዩ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ሲወጣ ውሳኔዎች በፍጥነት መለወጣቸው የህግ ሂደቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው ተመላክቷል።

​ማንኛውም ህግ የጣሰ አካል በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳበት የሚስማሙት አስተያየት ሰጪዎች የህግ አተገባበሩ ግን ከግል ግፊት፣ ከማዋከብ እና ከማጉላት የጸዳ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
​
በአርባ ምንጭ ከተማ የተከሰተው የኮሪደር መብራት አደጋ እናይን ተከትሎ የተወሰደው የቅጣት እርምጃ እንዲሁም የሂደቱ አካሄድ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብና ስጋት ማስነሳቱ የህግ አተገባበርን ፍትሃዊነትና ግልጽነት ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል።

​ከተፈጠረው ትክክለኛ ጉዳት አንጻር መጀመሪያ ተወስኖ ከነበረው የገንዘብ ቅጣት መጠን በድንገት ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍ ማለት እንዲሁም “ደረሰኝ አልቋል” በሚል ሰበብ ብቻ ዜጎች ለሳምንታት በእስር እንዲቆዩ መደረጉ አሰራሩ አድሎአዊና ግለሰቦችን ለማዋከብ የተመቻቸ መሆኑን የሚያሳይ ስጋት ፈጥሯል።

​በአጠቃላይ ህግና ስርዓት ሲከበር ከማንኛውም ግፊት ግልጽ ከልዩነት እና ከግል ጫና የጸዳ መሆን እንዳለበት የህብረተሰቡ አስተያየት በግልጽ ያሳያል። የህግ አካላትም ሆኑ የከተማዋ አስተዳደር ፍትሕን ከማስፈን አንጻር ሚዛናዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ሊከተሉ እንደሚገባ ህዝቡ አበክሮ አሳስበዋል።