ዎላይታን ወክሎ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ውድድር ያለፈው በዲቲ ከነማ አቀባበል ተደረገ

በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ በነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ቡድኖች በተሳተፊበት ውድድር ወደ ሊጉ ዎላይታን ወክሎ ማለፉን ለቻለው ቦዲቲ ከነማ ስፓርት ቡድን በአከባቢው ማህበረሰብ፣ በመንግስት አመራሮች ደማቅ አቀባበል በዛሬው ዕለት ተደርጓል።

ሊጉን በመቀላቀል ከተማዋን ሆነ አከባቢውን ማስጠራት የቻለው በድኑ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥልና ውጤታማ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩና የአከባቢው ማህበረሰብ በቅርበት ሆኖ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተላከው መረጃ ያመለክታል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1

በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 07/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹