ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎችን እስከ ቦታው ድረስ በመላክ እንዲሁም ከአከባቢው ለሀገር ጥሪ የዘመቱ ዜጎች ቤተሰብ በመደገፍ መንግስት የጀመራቸውን ሀገር የማዳን ስራ ላይ ጎን እንደሚቆሙ ዩንቨርስቲው አረጋግጧል።
በዛሬው ዕለት ዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ የሀገሪቱን ህልውና ለማስጠበቅ እየታገለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ በተሰበሰበት ወቅት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥለው የሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ሲጠበቅ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ተናግረዋል።
ዩኒቨርስቲው ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎች እስከ ቦታው ድረስ በመላክ መንግስት የጀመራቸውን ሀገር የማዳን ስራ ላይ የበኩሉን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኑን ፕሮፌሰር ታከለ አስረድተዋል።
ከዛ ባሻገር እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ምሁራን የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና በማሳደግ ከሀገር ጎን እንዲሰለፉ ለማድረግ ድርሻ እንዲወስዱ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።
የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት በየግላቸው የወር ደሞዛቸውን ጨምሮ እንዲሁም ከዩንቨርስቲው ካዝና የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አበክረው ገልፀዋል።
ሀገር ለማፍረስ ከተነሱ ቡድኖች ጋር በመሰለፍ ከሠላማዊው ሕዝብ ስር በመሰግሰግ በስመ-ምሁርነት የተሳሳተና በውስጡ መርዝ ያመረቀዘ መረጃ ለማወናበጃነት በማሰራጨት ሰላም የሚያሳጡ የጥፋት ልክፍት ያለባቸውን በማጋለጥ ስራቸውን ለማድረቅ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት በተደረገበት ወቅት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
የሀገሪቱን ህልውና ለማስጠበቅ እየታገለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ የተሰበሰቡ የዩኒቨርስቲው ካውንስል አባላት በግቢው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 06/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
