1790923127881

​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌን አዲስ የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።

​አዲሱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ የመንግስት ዋና ተጠሪ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ መሆኑ ታውቋል። ዶክተር ተስፋዬ ከዚህ ቀደም ከፌዴራል እስከ ክልል ባሉ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በሰሯቸው ሥራዎች የሚታወቁ ሲሆን ክልሉን በቅርበት የሚያውቁና በሂደቱም ላይ ልምድ ያላቸው አመራር መሆናቸው ይነገራል።

​ይህ የቀድሞውን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን መነሳት ተከትሎ የተደረገው አዲስ የሹመት ሂደት፤ ክልሉ የገባበትን ተቋማዊ ቀውስ እና አስተዳደራዊ ክፍተት ለመሙላት የሚደረግ አዲስ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

WT Media የክልሉን አዲስ አስተዳደር እና በቀጣይ የሚከናወኑ የሥራ ሂደቶች በቅርበት የሚከታተል ይሆናል።

​Voice of Marginalized Community – WT Media