የዎላይታ ሶዶ መርካቶ ገበያ ማዕከል ግንባታ በተቀመጠው ጊዜ ገደብና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
ባለፈው ህዳር ወር በድንገተኛ እሳት አደጋ የተቃጠለውን የመርካቶ ገበያ በዘመናዊ መንገድ መልሶ ለመገንባት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በግንቦታ ሂደት እየተሳተፉ ከሚገኙ ተቋራጮች መካከል አንዱ የሆነው የአንጆንዮ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ እህት ኩባንያ የሆነው የታደሰ ሮባ ጃርሳ አጠቃላይ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ
ገበያ ማዕከል ግንባታው በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
የገበያ ማዕከሉ ብዙ ዜጎች ሰርተው የሚለወጡበትና ከዕለት ተዕለት ህይወታቸው ጋር የተቆራኘ ቦታ በመሆኑ በድርብ ኃላፊነት በጥራትና በጊዜ ለመጨረስ ሙሉ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን የአንጆንዮ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ እህት ኩባንያ የሆነው የታደሰ ሮባ ጃርሳ አጠቃላይ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ሮባ ተናግረዋል።
የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የግንባታ ሂደቱን ቅኝት ባደረገበት ወቅት የሌሎች ተቋራጭ ስራም በተቀመጠው ጊዜ ገደብና በጥራት ለማጠናቀቅ እርብርብ እያደረጉ ሲሆን በርካታ የገበያ ማዕከሉን መጠናቀቅ በተስፋ የሚጠብቁ ዜጎች
በዙሪያው በመንገድ ዳር በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው የንግድ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ለመመልከት ችለናል።
የመርካቶ ገበያ መልሶ ግንባታ በየ100 ሜትር የእሳት አደጋ ለመከላከል የሚያስችል የውሃ ቋት፣ የአስፋልት መንገዶች፣ የውሃ እና የዲች መስመር፣ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያ እና የቁም እንስሳት ጊዜያዊ ማቆያ የማዕከሉ የግብይት ሂደቱን የሚያዘምን የአዲሱ የዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ማዕከል አካል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 13/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
