“ሌብነትን በጋራ እንታገል!” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ሥልጠናው ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ የትውልድ የሥነ ምግባር እሴቶችን ማጠናከር ተገቢ እንደሆነ በማመን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በተማሪዎች ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ተከታታይነት ያለውን ሥልጠና ሲሰጥ መቆዩቱን ገልፀዋል፡፡
ፕሮፌሰር አክለውም ሙስና የዕድገት ፀር መሆኑን በማሳየት የሙስና ሰንሰለትን ለመበጠስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ሥራ መሰራቱንና በየሥራ እርከኑ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ከመቅረፍ አንፃርም አበረታች ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡
እንደተቋም የፀረ ሙስና ትግሉን አጠናከሮ ለማስቀጠል የተማሪዎችን ክበባትን በማቋቋም የሥነ-ምግባር ትምህርቶችን በመስጠት፣ የተቋሙ ሠራተኞች የሀብት ምዘገባ እንዲያካሂዱ በማድረግ እንዲሁም የሀብት ምዝበራ በሚስተዋልባቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ክትትል በማድረግ ሀብትን የማስመለስ ሥራ በሰፊው እንደተሰራ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደለ ያያ በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው በ2013 ዓ.ም ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና በተመለከተ በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ዩኒቨርሲቲው ተሸላሚ መሆኑን ጠቅሰው ወደፊትም ለሀገር አንድነት፣ ለሀብት ፍትሐዊ አጠቃቀም እንዲሆን ሌብነትን በፅኑ መታገል እንደሚገባ አስቀምጠዋል፡፡
ሙስናና ብልሹ ሥነ-ምግባር በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በሥነ-ልቦና ክፉኛ እንደሚጎዳ የገለፁት ዳይሬክተሩ ተመራቂ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል፡፡
እንደ ዩንቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮከቴሬት ዘገባ ኢትዮጵያ ሙስናን በመከላከል በ2020 ዓ.ም በዓለም 94ኛ በሀገር 14ኛ ደረጃ ለመያዝ እየሰራች መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ጣፋጭ መርዝ የሆነውን ሙስና በማጥፋት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመለከታቸው ሁሉ የየራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 13/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹


