1000150805

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ​በአርባምንጭ ከተማ ከነጭ ሳር ፓርካ ጫካ “እንጨት ለቅመዋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የሰላሳ ወራት (አንድ ዓመት ከስድስት ወር) እስራትና የ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተፈርዶባቸው የነበሩ 8 ግለሰቦች እናቶች ከ40 ቀናት እስራት በኋላ በዋስ መፈታታቸውን WT Media አረጋግጧል።

​ከዚህ ቀደም ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኖ በሰፊው መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በእናቶቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎ በነበረበት ወቅት የሕግ መብቶቻቸው በተለይም ያለ ጠበቃ የመደመጥ እና በነጻ ድጋፍ የማግኘት መብታቸው ላይ ጥያቄዎች መነሳታቸው ይታወሳል።

የሕግ ባለሙያዎችና ተሟጋቾች ጉዳዩን በይግባኝ በመከታተል በሰጡት ርብርብ አዲስ ለውጥ ታይቷል።

​በዚህም መሠረት የአርባምንጭ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባካሄደው የይግባኝ ሂደት ይግባኝ ባዮች በቂ ዋስ በማቅረባቸው በእስር ላይ የነበሩት እናቶች እያንዳንዳቸው በ40 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።

የሕግ አማካሪው አቶ ቡንካሾ ሃንጌ እና ሌሎች የህግ አዋቂዎች ለእናቶቹ ዋስ በመሆን እና ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እንዲፈቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

​ምንም እንኳን እናቶቹ በዋስ ቢፈቱም ጉዳዩን በዘላቂነት ለመፍታት እና መሰል ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በዘላቂ የልማትና የድጋፍ ማዕቀፎች ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎች እያነሱ ይገኛሉ።

WT Media የዚህን ጉዳይ የመጨረሻ የፍርድ ሂደት እና የፍትህ አሰጣጥ ክትትል በቅርበት የሚከታተል ይሆናል።
​
Voice of Marginalized Community – WT Media