GridArt_20261024_233941746

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በጎርካ ወረዳ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በተከፈተ ድንገተኛ ጥቃት የሶስት ንጹሃን ዜጎች ሕይወት ማለፉን የኮሬ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

​በጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በተወጣው የሀዘን መግለጫ እንዳሰፈረው በጃሎ ቀበሌ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበረ የ14 ዓመት ታዳጊ ህጻን እና በቆሬ ቀበሌ እርሻ ማሳቸውን እያረሱ በነበሩ ሁለት አርሶ አደሮች በድምሩ በሶስት ዜጎች ላይ ሞት የደረሰ ሲሆን በሌሎች ሶስት ዜጎች ላይም የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

የዞኑ አስተዳደር በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ይህንን ተደጋጋሚ እና የህዝብ ሰላም ማናጋት ዓላማ ያደረገ እኩይ ድርጊት በጽኑ አውግዟል።

ህብረተሰቡ በክስተቱ ሳይደናገጥና ሳይዘናጋ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ የሰላም ዘብ እንዲሆን እና የዘውትር የሥራ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

​የዞኑ አስተዳደር ከክልሉ መንግሥት እና ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አካባቢው ላይ ሰላም ለማስፈንና የወገኖችን ደህንነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳደር ወንጀለኞችን በማጋለጥና ለህግ ለማቅረብ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስቧል።

​የኮሬ ዞን አስተዳደር ለመላው የኮሬ ህዝብ እና ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

ከሶስት ቀን በፊት ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ በኩል በመጡ ጽንፈኛ አካላት በተባለው በተፈጸመው ጥቃት፣ አርሶ አደሮቹ በማሳቸው ህይወት ማለፍ ባለፈ ንብረት አውድሟል፤ በርካታ ከብቶችም በአደባባይ መዘረፋቸው ተገልጾ ነበር።

​Voice of Marginalized Community – WT Media